Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቢድዓን መዋጋት አንድነትን ማጎልበት ነው!

ቢድዓን መዋጋት አንድነትን ማጎልበት ነው!
ቢድዓን ማውገዝ በህብረት ነው!
ምክኒያቱም፤ ቢድዓ ለልዩነዩነትና ውዝግብ መንስኤ ነው። ሰዎች ከቢድዓ ተቆጥበው ሱና ላይ በመፅናታቸው የሚፈጠር ምንም አይነት ኺላፍ የለም። ለምን ቢድዓ አልሰራችሁም የሚል ውዝግብም አይመጣም። ታላቁ አሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል፤
«البدعة مقرونة بالفرقة، كما أن السنة مقرونة بالجماعة، فيقال: أهل السنة والجماعة كما يقال: أهل البدعة والفرقة» الاستقامة 1/42
«ሱና ከአንድነት ጋር እንደተቆራኘ ሁሉ፤ ቢድዓ ደግሞ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው! ስለዚህም፤ የሱናና የጀማዓህ ሰዎች እንደሚባለው የቢድዓና የልዩነት (የፉርቃ) ሰዎች ይባላል!!» አል ኢስቲቃማ 1/42
ሰሞኑን የሚከበረው የመውሊድ በዓልም በኢስላም መሰረት የሌለው የቢድአ ተግባር ስለሆነ ሁላችንም ወዳጆቻችንን ከቢድዓ በማስጠንቀቅ አንድነትን ለመጠቅ አስተዋፅኦ እናበርክት!

Post a Comment

0 Comments