Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፍጡራን ሊመለኩ አይገባም፡፡






ፍጡራን ሊመለኩ አይገባም፡፡

ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል

أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْـًٔا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
وَلَا يَسْتَطِيعُونَ لَهُمْ نَصْرًا وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ


‹‹ምንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን በአላህ (ብቸኛው ፈጣሪ) ላይ ያጋራሉን? ለነርሱም መርዳት የማይችሉትን? ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን?››

ለምሳሌ ጂብሪልም፤ ኢሳም፤ መርየምም፤ ነብዩ ሙሃመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ አልይንም፤ ሁሴንንም፤ ፋጢማን፤ ነፊሳን፤ ዘይነብን፤ አብድል ቃድር ጀይላኔን፤ በደዊን፤ ባባ ፈሪዱ ዲን፤ ኑርሁሴንን፤ ደግዬን፤ አብሬትን፤ ቃጥባሬን፤ አልከስዬን፤ ሀሰን በቱል፤ ሰይፉ ጨንገሬን፤ ሸህ አንበሶን፤ አዳል ሞቴን፤ ጨሌን እና ሌሎች ፍጡራንን አስመልክቶ

አላህ እንዲህ አለ
ለነርሱም መርዳት የማይችሉትን? ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን? በአላህ ላይ ያጋራሉን?
ጥራቻ ይገባው ጌታችን አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ፤ ለእርሱ ተጋሪ የለውም፤ ንግስና ለእርሱ ብቻ ነው፤ ምስጋናም ለእርሱ ብቻ ነው፤ ሁሉን ነገር በማድረግ ላይ ቻይ ነው፡፡

ቅ ድ ሚ ያ ለ ተ ው ሂ ድ፡፡



Sadat Kemal Abu Nuh