Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በወንጀል ምክንያት የሚመጡ ቅጣቶችን የሚያሰርዙ አስር ምክንያቶች

በወንጀል ምክንያት የሚመጡ ቅጣቶችን የሚያሰርዙ አስር ምክንያቶች

ኢብን ተይሚያ - رحمه الله - “መጅሙዕ አል'ፈታዋ” በተባለው ኪታባቸው ጥራዝ 7 ከገጽ 487-501 የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“በወንጀል ምክንያት የሚመጣን ቅጣት በሚከተሉት አስር ምክንያቶች ማሰረዝ ይቻላል፡-
1- ከወንጀል/ከሐጢያት ጸጸት አድርጎ መመለስ ወንጀልን ሊያሰርዝ እንደሚችል ሙስሊሞች በአንድ ድምጽ ተስማምተዋል፡፡
ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡-

قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ (53) (الزمر)
“በላቸው እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ሓጢያቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሃሪው አዛኙ ነውና፡፡” (አዝ'ዙመር፡ 53)

2- ላጠፋው ጥፋት ኢስቲግፋር ማድረግ (አላህን ይቅርታ መጠየቅ)
ለዚህ ማስረጃው ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሐዲስ ነው፡-
"إذا أذنب عبد ذنبا فقال : أي رب أذنبت ذنبا فاغفر لي . فقال : علم عبدي أن له ربا يغفر الذنب ويأخذ به قد غفرت لعبدي. ثم أذنب ذنبا آخر فقال : أي رب ، أذنبت ذنبا آخر فاغفره لي . فقال ربه : علم عبدي أن له ربا يغفر الذنب ويأخذ به قد غفرت لعبدي فليفعل ما شاء ، قال ذلك في الثالثة أو الرابعة"
“ ሐጢያትን ፈጽሞ ሲያበቃ “ጌታዬ ሆይ! ይቅር በለኝ” ብሎ ለተማጸነ ሰው (የአላህ ባሪያ) አላህ የሚከተለውን ምላሽ ይሰጠዋል፡- “ወንጀልን የሚምር ጌታ እንዳለው ባሪያዬ በመገንዘቡ ሓጢያቱን ምሬዋለሁ፡" ይህ ሰው በድጋሜ ወንጀልን ፈጸመ ከዚያ “ጌታዬ ሆይ! ሌላ ወንጀል ፈጸምኩ እባክህ ምህረት አድርግልኝ፡፡” ብሎ ተማጸነ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- ““ወንጀልን የሚምር ጌታ እንዳለው ባሪያዬ በመገንዘቡ ሓጢያቱን ምሬዋለሁ፡፡ከዚህ በኋላ የፈለገውን ይስራ፡፡" ይህንን በሶስተኛው ወይም በአራተኛው ተናገረው፡፡”
3- ሐጢያት ከፈጸመ በኋላ መልካም ስራዎችን ማብዛት
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِنَ اللَّيْلِ ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ ﴿١١٤﴾
“ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ መልካም ስራዎች ሓጢያቶችን ያስወግዳሉና፡፡” (ሁድ፡ 114)
4- ሙስሊሞች እርስ በርስ የሚያደርጉት ዱዓ፡፡ ለምሳሌ በሙስሊሞች ጀናዛ ላይ የሚሰገድ ሶላት፡፡
وعن عائشة وأنس بن مالك عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه قال : "ما من ميت يصلي عليه أمة من المسلمين يبلغون مائة كلهم يشفعون إلا شفعوا فيه " روااه مسلم

አኢሻና አነስ የሚከተለውን የረሱል صلى الله عليه وسلمሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
“ቁጥራቸው መቶ የሚደርሱ ሙስሊሞች አንድን ሙስሊም ሟች አላህ እንዲምረው ሶላት ሰግደው ከአላህ ምልጃ አይጠይቁም አላህ የእነዚህን ሙስሊሞች ምልጃ የሚቀበል ቢሆን እንጅ፡፡” ሐዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል፡፡

5- በሞተው ሰው ስም ሶደቃ፣ ሐጅና የተለያዩ መልካም ስራዎችን መስራት፡፡ (¹)
6- በትንሳኤ ቀን ነብዩና ሌሎች ደጋግ የአላህ ባሮች የሚጠይቁት ምልጃ፡፡ (²)
7- በዱንያ ላይ የሚደርሱ እንግልትና መከራዎችን በጽናት መወጣት፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلمየሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"ما يصب المؤمن من وصب ، ولا نصب ، ولا هم ، ولا حزن ، ولا غم ، ولا أذى ، حتى الشوكة يشاكها إلا كفر الله بها من خطاياه"

“ሙእሚን መከራ ልፋት ሀሳብ ሀዘን ጭንቀትና ስቃይ አይደርስበትም እሾህ እንኳ አይወጋውም የፈጸመውን ወንጀል በእርሷ ምክንያት አላህ የሚሰርዝለት ቢሆን እንጅ፡፡”
8- ቀብር ውስጥ የሚኖረው ፈተና ጭንቀት እና ጫና፡፡(³)
9- የቂያማ ቀን ድንጋጤና ብርቱ መከራ፡፡(⁴)
10- የአላህ እዝነት፣ ይቅርታ እና ምህረት፡፡(⁵)

ከዚያም "በዱንያ ላይ እያለህ ይህን ወንጀልህን ደብቄልህ ነበር ዛሬ ምህረት አደርግልሃለሁ፡፡” የሚል መልስ ከጌታው ይሰጠዋል፡፡ ከዚያም ይህ አማኝ የመልካም ስራ መዝገቡን (በክብር) ይሰጠዋል፡፡ ከሀዲውና ሙናፊቁ ግን መስካሪዎቹ ሁሉ እንዲህ ይሉታል “እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹ ናቸው” ይላሉ፡፡ ንቁ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን፡፡” (ሁድ/18) ይላሉ፡፡ በማለት ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ ሰጡ (ቡኻሪ/2441‐ሙስሊም/2768)

መልክት:‐ከ1‐9 የተዘረዘሩት ነጥቦች አንድ አላህን በብቸኝነት የሚያመልክ ባሪያ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ወንጀሎች ወይም ከትዕዛዛቱ ማጓደሎች ኖረውበት ለእሳት የሚዳርጉ ሆነው ጀሐነም ከመግባቱ በፊት ወንጀሉን ሊያሰርዙለት የሚችሉ ከአዛኙ አላህ ለባሪያው የተመቻቹ እድሎች ናቸው።
* 10ኛው ግን ጀሐነም ከመግባቱ በፊትም ሆነ በኋላ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያመላክቱ በርካታ ማስረጃዎች አሉ።

"አነዚህን ሁሉ እድሎች ሳይጠቀምባቸው ቀርቶ ራሱን ለጀሐነም በዘውታሪነትም ሆነ ለተወሰነ ጊዜ የአላህን ከባድ ቅጣት ጀሐነምን የገባት ሰው ነፍሱን እንጅ ሌላን አካል መውቀስ አይገባውም"



================================

(¹) ለዚህ በርካታ ማስረጃዎች ይኖራሉ ከነዚህ መካከል

* ሰዕድ ብን ዑባዳህ (ረዲየላሁ ዓንሁ) ለረሱል ﷺ እናቴ ሞተች ለእርሷ ሰደቃ ልሰጥላት እችላለሁ? ብሎ ጠየቃቸው "አወ" አሉት የትኛው ሰደቃ ነው በላጩ አላቸው, እሳቸውም "ውሀ ማጠጣት" አሉት (ነሳኢ/3664–አህመድ/23845)

* ከበኒ ጁሐይነት ጎሳ የሆነች ሴት ወደአላህ መልእክተኛ ﷺ መጣችና እናቴ ሀጅ ለማድረግ ተስላ ሀጅ ሳታደርግ ሞተች ስለሷ ሀጅ ማድረግ እችላለሁን? አለቻቸው " አዎ ሀጁን አድርጊላት አስተውለሻል በእናትሽ ላይ እዳ ቢኖርባት ኖሮ አትከፍይላትም ነበር? " አሏት (ቡኻሪ/1852)

*እንዲሁም ዱዓ ማድረግ, ዑምራ መስራት, የሞተው ሰው ግዴታ የሆኑ ፆሞች ያሉበት ከሆነ ቢፆምለት እንደሚደርሰው የሚያመላክቱ ሐዲሶች አሉ። ነገር ግን ሰላት መስገድ ቁርአን መቅራት ማስቀራትን በሚመለከት የመጣ ትክክለኛ ማስረጃ ባለመኖሮ ዑለሞች ሊተገበሩ አይገባም ይላሉ።

(²). ከማስረጃዎች መካከል ቡኻሪ‐7439 ሙስሊም‐183 ላይ እና ሌሎቹም የዘገቡት ረዘም ያለው ሐዲስ ይገኝበታል

(³) ዓኢሻ ረዲየሏሁዓንሃ እንዳወራችሁ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል "ለቀብር እኮ ማስጨነቅ አለው, ከርሷ ነፃ መውጣት የሚችል ቢሆን ኖሮ ሰዕድ ብን ሙዓዝ ነፃ በሆነ ነበር" ብለዋል (አህመድ/24283–ሶሂሁል ጃሚዕ/2180)

ዑለሞች የማስጨነቁን ሚስጥር ሲናገሩ " የዚህ ማስጨነቅ ምክንያቱ ካለበት ነገር ለማጥራት ነው። ከፍጡራን ማንም የለም ትንሽም ብትሆን እንኳን ወንጀልን የማይፈፅም። ነብያቶችን በተመለከተ ግን በጥብቅነታቸው ምክንያት የቀብር ውስጥ ጥያቄም ሆነ ማስጨነቅን በሚመለከት በሐዲስ የመጣ ነገር የለም " ይላሉ

(⁴) የትንሳኤ ቀን የሚኖረው ድንጋጤ፣ ፀሐይ በፍጡራኑ አናት ቀርባ በላብ መዋጣቸው፣ ሲራጥ ላይ የሚያጋጥማቸው ፈተና እና ሌሎቹም ሳይማሩ የቀሩ ሐጥያቶችን ይቅር እንዲባሉ ምክንያቶች ይሆናሉ። ወላሁአዕለም

(⁵) ሶፍዋን ብን ሙህሪዝ አል`ማዚኒይ የሚከተለውን ተናግሯል፡- “የኢብን ዑመርን እጅ ይዥ እየተጓዝኩ እያለ በድንገት አንድ ሰው መጣና “ስለነጅዋ (አላህ በትንሳኤ እለት ከባሪያው ጋር ስለሚያደርገው ወሬ) ከረሱል ﷺ እንዴት ነበር የሰማህ? በማለት ጠየቃቸው፡፡ “ረሱል ﷺ የሚከተለውን ሲናገሩ ሰማሁ” “አላህ ሙዕሚንን ያቀርብና ከነፉን (መሸፈኛውን) ጣል ያደርጋል፡፡ ከሌሎች በመደበቅ “ይህን ወንጀልህን አታውቅምን? ይህን ወንጀልህን አታውቀውምን? በማለት ደጋግሞ (ባሪያውን) ይጠይቀዋል፡፡ ሙዕሚኑም ጠፋሁ ብሎ እስከሚያስብ ድረስ “ጌታዬ ሆይ አዎ(አውቃለሁ)” በማለት ዱንያ ላይ የፈጸመውን ወንጀል ሁሉ ያምናል፡፡


የባህር ዳር አህሉ ሱና መሻይኾች ገፅ

Post a Comment

0 Comments