Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የት ነው ያሉት???


ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የት ነው ያሉት???ክፍል 19‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ››፤ ‹‹አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ››፤ ‹‹ግቡልን የተንቢ››፤ ‹‹መርሃባ ነቢ መርሃባ››አገራችን ላይ የሚባሉ መንዙማዎች ውስጥ የሚከተሉት ይባላሉ ‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ››፤ ‹‹አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ››፤ ‹‹ግቡልን የተንቢ››፤ ‹‹መርሃባ ነቢ መርሃባ››አስገራሚ ነው፡፡ የአቂዳ ወይንም የእምነት ትምህርት ማህበረሰባችን በሰፊው ሊደርሰው እንደሚገባ የሚጠቁሙ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የዛሬውም ትምህርት ይህንን ያስይዛል፡፡ዝምታ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ማህበረሰቡን የህይወቱ ማማር በዚህኛውም አለም ይሁን በሚቀጥለው የሚስተካከልበትን ‹‹ተውሂድ›› በሰፊው ማድረስ ግዴታ ነው፡፡የዛሬው አርስት እንደሚያሳየው ከላይ የተባሉትን አባባሎች እያንዳንዳቸውን እንይ እና ኢስላም የሚለውንም አይተን ከዛ ሃቁን ተቀብለን እንሂድ፡፡ ለአላህ ብሎ መመካከር ኢስላም ያስቀመጠው ግዴታ ነው፡፡‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ›› የሚለው አባባል ‹‹ሀደሬኛ›› ሲሆን ሃደሬኛ መንዙማ ከሚሉት ሰዎች ውስጥ አንዱ ያለው መንዙማ ነው፡፡ እራሱ ሲተረጉመው እንዲህ ይላል ‹‹ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መጡ መጡ ለማለት ነው›› ብሎ ተረጎመው፡፡ ይህ ሰው ከእርሱ በፊት ለነበረው መንዙማ ባይን አስመልክቶ እንዲህ አለ ‹‹እንዲህ ነብያችንን እያመጧቸው ሸይኽ ሙሃመድ አወል እንደው ስማቸው እየተጠራ ሳለ ቁጭ ማለታችሁ ያሳዝናል፡፡ ስለዚህ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እሳቸውን ስናወድስ ‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ›› ‹‹ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መጡ መጡ ለማለት ነው›› ›› ብሎ ተረጎመው፡፡ከዛም ድቤ የሚደበድበው ሰው ተመልካች የነበሩ ሰዎችን ‹‹ተነሱ ብሎ በእጁ ምልክት ሰጣቸው›› እንዲነሱ፡፡በጉራግኛ ደግሞ ረመዳን ላይ ከወጣ መንዙማ ውስጥ እንዲህ ይላል ‹‹ግቡልን የተንቢ›› ነብያችንን ኑ እንደማለት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ‹‹አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ›› እየተባለ ነብያችንን ይመጣሉ ብሎ መገመት እና ማመን ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሚቀጥለው ስንኛቸው በደንብ ይብራራል፡፡‹‹መርሃባ ነቢ መርሃባ›› ሲባል ይህንን ሲሉ እነዚሁ ሰዎች ከተቀመጡበት ይቆማሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም መንገድ ከመሳታቸው ውስጥ ነጭ ምንጣፍ አስቀምጠው ‹‹ነብያችን እና ሰሃባዎች መጥተው እዚህ ይቀመጣሉ›› ይላሉ፡፡ኢስላም የሚሰጠውን መልሶች በአላህ ፈቃድ እንደሚከተሉት እንይ1) የአላህ መላክተኛን ﷺ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹አንተም ሟች ነህ፤ እነሱም ሟቾች ናቸው››፡፡ 2) የአላህ መላክተኛﷺ በህይወት በነበሩበት ግዜ ሰሃባዎችን እንዳይቆሙላቸው ከልክለዋል፡፡ ሰሃባዎችም ከእኛ በላይ የአላህ መላክተኛንﷺ በጣም የሚያከብሩት ነብያችንﷺ አደለም ሞተው በህይወት እያሉም አይቆሙላቸውም ነበር፡፡ ታድያ እነዚህ መንዙማ ባዬች ከሰሃባዎች በላይ ለነብያችን ክብር ኖሯቸው ነውን??? ወደ ቀጥተኛው መንገድ አላህ ይምራን3) እኛ እሳቸው ላይ ሰለዋት ስናወርድ ምን ብለን ነው???‹‹አላህ ሆይ! በሙሃመድ ላይ ሰላትህ እና እዝነትህ ይሁን››፡፡ እንዳየነው ተለማኙ አላህ ነው፡፡ ከአዛን በኋላ የምናደርገው ዱዓ እራሱ የአላህ መላክተኛ ﷺ እንዲህ ብላችሁ አላህን ለምኑልኝ ነበር ያሉት ‹‹….. ለሙሃመድ ወሲላ እና ፈዲላን (ጀነት ውስጥ ያሉ ደረጃዎች ናቸው ተብሏል) ስጣቸው››፡፡ አማኞች ለአላህ መላክተኛ ነው እየለመኑላቸው ያሉት፤ በህይወት ያለ ለሞቱት ዱዐ ያደርጋል፡፡4) እኛ እሳቸው ላይ ሰለዋት ስናወርድ እሳቸው በቀጥታ ያውቃሉን ??? ሃዲሱ እንዲህ ይላል‹‹የትም ሆናችሁ ሰላም (ሰለዋት ብታወርዱብኝ) ብትሉኝ፤ መላኢካዎች ያደርሱልኛል›› ሃዲሱ እንደሚያሳየው በግልፅ እሳቸው ላይ ሰለዋት ስናወርድ መላኢካዎች ያደርሱላቸዋል፤ እንጂ እመጣለሁ አላሉም፡፡5) የአላህ መላክተኛ ﷺ አደለም ሞተው በህይወት በነበሩ ግዜ የአላህን ሀቅ አንዱንም ቢሆን ለእርሳቸው አይገባቸውም፡፡ የአላህ መላክተኛ ﷺ - የሩቁን አያውቁም፤- ጥሩን ለራሳቸው ማምጣት አይችሉም፤- መጥፎን መከላከል አይችሉም አላህ ከጠቀማቸው ውጭ፤- አላህ እሳቸውን በጉዳት ቢፈልጋቸው ፍጡራን ተሰብስበው ሊያስጥሏቸው አይችሉም፤- መስጠትም፤ መንሳትም አይችሉም፤- ታላቁንም ምልጃ አላህን ተደፍተው (ሱጁድ አድርገው) ለምነው አላህ ከፈቀደላቸው በኋላ ብቻ ነው - የሚያማልዱት፤ የሚያማልዱትም አላህ ለፈቀደለት ብቻ ነው፡፡ - ስለዚህ የአላህ መልክተኛ ﷺ አካላቸው መዲና ተቀብሮ ነው ያለው ሰለዋት ስናወርድባቸው እንኳን ያሉበት ሆነው ነው፤ አላህ ሩሃቸውን መልሶላቸው መልስ የሚሰጡት፡፡ ከዛ ውጭ ‹‹መርሃባ፤ መጡ፤ ግቡልን፤ ዲጅዋ…እና የመሳሰሉትን›› ማለት ከባድ ስህተት ነው፡፡ወደ ሰለፉነ ሷሊሁን እምነት፤ ንግግር እና ተግባር አላህ ይመልሰን፡፡ አዲስ መጤ ከተባሉ ነገሮች አላህ ይጠብቀን፡፡ አላህ እውነተኛ አንድነት ይስጠን፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኞች ሁሉ ላይ ይሁን፡፡