Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የፊልም አክተሮች ሆይ! በኢስላም ስም መነገድ አይበቃም??? የአላህን ቤቶች አታቆሽሹ፡፡




የፊልም አክተሮች ሆይ!
በኢስላም ስም መነገድ አይበቃም???
የአላህን ቤቶች አታቆሽሹ፡፡ 
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኞች መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
አንድን ነገር ስሙን በመቀየር መጥፎን ጥሩ ማድረግ ይቻላልን??? ለምሳሌ አገራችን ላይ ‹‹ጠጅን›› እየጠጡ ‹‹ብርዝ›› ነው ይሉታል ስሙን፡፡ ሌላው በዚህ ወቅት እያየን ያለነው በኢስላም ስም መነገድ እና ገንዘብ ማካበትን ነው፡፡ ኢስላምን ሲነግዱበት ግን ስሙን ያሳምሩታል ‹‹ኢስላማዊ›› ብለው ይጠሩታል፡፡ እወቁ እናንተ የፊል አክተሮች ስም በመቀየር ሙስሊሙን መሸወድ አይቻላችሁም፡፡
እዛው ብሄራዊ ቲያትር ቤት፤ ሃገር ፍቅር፤ እና የመሳሰሉት ሄዳችሁ ገበያው ውስጥ ለመፎካከር ሲያቅታችሁ፤ ዛሬ ሙስሊሙን ከድራማ፤ ከፊልም እና ከሙዚቃ ሲቶብት እና ቁርዐን እና ሃዲስ ሊማር ሲል ‹‹ፊልሙን፤ ድራማውን፤ ሙዚቃውን አስልመንልሃል›› ብላችሁት ቁጭ፡፡
እንደው ትንሽ አታፍሩም??? የፈጠራችሁን ጌታ አታፍሩትም??? አትፈሩትም???
የአላህን ቤት መሳጂዶችን ወንድ እና ሴት ሆናችሁ አንድ ላይ አብራችሁ ፎቶ ተነስታችሁ የአላህን ቤቶች ስታቆሽሹ??? ተው አላህ አያያዙ የበረታ ነው፡፡
ሲሉ ሰምታ እንደሚባለው፤ እናንተም ሰው ሲያደርግ አይታችሁ ቲያትር ቤት ላይ ሪክላም ሲለጠፍ ብታዩ፤ ዛሬ ታላቁን የአላህ ቤት እናንተው በአጅነቢ ሴት እና ፋሲቅ ወንዶች እና ሴቶች ፎቶ ታበላሹት???
ፋሲቅ፡- የአላህ እና የመልክተኛውን ትእዛዝ የሚያምፅ ነው፡፡ ሴቷ ቅንድቧን የተቀነደበች፤ ለፊልም ብላም ይሁን የጥሩ ሴት ፊት የሌላት፤ ልጲስቲክ ተቀብታ፤ ከወንድ ጋር በአክሽን ፎቶ ተነስታ አላህ ቤት ላይ ስትለጠፍ፡፡ ወንዱ ደግሞ የሲጋራ አጫሽ ከንፈሩን፤ ፂሙን ላጭቶ ሱሪውን መሬት ለመሬት እየጎተተ ከሴት ጋር በአክሽን ፎቶ ተንስቶ የአላህን ቤት መስጂድ ያበላሻል፡፡
አማኞችን እና ሰጋጆችን ለምን አዛ ታደርጋላችሁ???
የአላህ መላክተኛ ‹‹ወንድም ሴትን አይመልከት፤ ሴትም ወንድን አትመልከት›› አሉ፡፡ ታድያ አክተሮቹ ምን እየሰራችሁ ነው፡፡
አኢሻ (ረድየላሁ አንሃ)
የምእመናን እናት አኢሻ (ረድየላሁ አንሃ) የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስት ከመሆኗ እና የምእመናን እናት ከመሆኗ ጋር ማንም ሊያገባት አይችልም፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ የሰሃባ ወይንም የታቢኢን ወንዶችን ስታስተምር ከመጋረጃ ጀርባ ሆና ነበር፡፡
አክተሮቹ ሴቶች በአደባባይ ፎቶዋቸውን ያውም በአስቀያሚ ሁኔታ፤ ወንዶችን ወደ ሌላ ነገር በሚጠራ መልኩ ተነስተው መስጂዶችን ያበላሻሉ፡፡
አንድ እህት እንዲህ ስትል ጠየቀች፡፡ አንዱ ፊልም ላይ የሚታየው ‹‹ቲቪ አፍሪካ ላይ ይታያል››፡፡ እኛም የሚከተለውን እንላለን፡፡ ታድያ ቲቪ አፍሪካ ላይ መታየቱ ጥፋቱን የሚሸፍንለት መሰለው??? ማንም ይሁን ማን አጥፍቶ ሲመጣ በአደባባይ ለሰራው ጥፋት በአደባባይ ህዝብ ይጠነቀቀው ዘንድ መልስ ይሰጠዋል፡፡
በተጨባጭ የደረሰን ኢንፎርሜሽን ሳምንት ለሚቀረው ታላቅ የተከበረው እንግዳ ረመዳን፤ ፊልሞች ተሰርተው ለሽያጭ ተዘጋጅተዋል፡፡ ረመዳን ታላቁ እንግዳ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቁርዐንን እየቀሩ እና እያከተሙ ነበር ያሳለፉት ሊሞቱ አመት እንዲያውም 2 ግዜ አክትመው ነበር፡፡ ወደ ኡለማዎቻችን ስንመጣ ኢማሙ ሻፊኢይ 60 ግዜ ያከትሙ ነበር፡፡ ኡለማዎች ቂርዓት እና ደርስ ትተው ነበር ረመዳን ላይ ቁርዐንን ብቻ የሚቀሩት፡፡
ዛሬ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የአላህን ቃል በረመዳን እንኳን ቢያንስ እንዳያነብ፤ ፊልም፤ ድራማ፤ መንዙማ እና የመሳሰለውን እያሉ፤ መስጂድ ድረስ መጥተዋል ህዝቡን ሊያታሉት፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ማንም ይሁን ማን ሰዎችን ከቀጥተኛው መንገድ ሊያስት፤ ሊያጠም ከመጣ መልስ ይሰጥበታል፡፡ የትም ላይ ይታይ የት መልስ ይሰጠዋል ለጥፋቱ፡፡ ዛሬ ዛሬ ሰዎች ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ኢስላምን የሚያጠፋ ነገሮች እየሰሩ ነው፡፡
ማህበረሰቡን ማስጠንቀቅ እና እነዚህን ሰዎች መጠንቀቅ ግዴታ ነው፡፡ ሼር ይደረግ፡፡