Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ እና መልክተኛውን ላለመታዘዝ በአሜሪካ፤ በእስራኤል እና መንግስታት ማሳበብ

ዛሬ ዛሬ የተለመደች አባባል አለች፡፡ ኢስላም ሙስሊሞች የጠላት መጫወቻ፤ የውርደታቸው መንስኤ፤ እርስ በእርስ አለመግባባታቸው ምን እንደሆነ በግልፅ አስቀምጧል፡፡
ከዚህም አልፎ የደህንነታቸው ዋስትና፤ ድል የሚያገኙት እርሱ የመረጠላቸውን ሃይማኖት ያለ ፍርሃት እና ስጋት ሊተገብሩ የሚችሉት አላህን በብቸኝነት እስካመለኩ ድረስ እና ከእርሱ ውጭ የሚመለኩትን በጠቅላላ ክደው፤ አምልኮን ለእርሱ ብቻ ማድረግ እንዳለባቸው እንዲህ ሲል በግልፅ ያስቀምጠዋል፡፡

ምስራና ሁሉ ለአላህ ነው የሁለት አገር ደስታን በኢማን፤ በዲን፤ አላህ እና መልክተኛውን በመታዘዝ ብቻ ያደረገ፡፡ የሚቀጥለውን አለም ምንም ጥርጥር የለውም የሚወርሷት የእምነት ባለቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ ምድራዊው አለም ላይስ ደስታ እና የተመቻቸ ህይወት፤ ስቃይ መከራ የሌለበት የተድላ ህይወት በምን ይገኝ አላህ እንዲህ ይላል

مَنْ عَمِلَ صَٰلِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡ የአላህ ቃል በግልፅ እንዳስቀመጠው፤ መልካም ኑሮ ለማግኘት አምኖ መልካም ስራ መስራት ብቻ ነው፡፡ መልካም ስራ ይሆን ዘንድ ማንኛውም ስራ ለአላህ ብቻ ተብሎ ሊሰራ እና የነብያችንን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፈለግ መከተል ግድ ይለዋል፡፡ ሀይማኖቱ እንዲመቻችለት፤ ሰላምን ማግኘት የፈለገ፤ የምድር ምትክ መሆን የፈለገ፤ በጠላት ላይ የበላይ ሆኖ ተከብሮ መኖር የፈለገ ምን ማድረግ እንዳለበት አላህ ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَيَسْتَخْلِفَنَّهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ كَمَا ٱسْتَخْلَفَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمْ دِينَهُمُ ٱلَّذِى ٱرْتَضَىٰ لَهُمْ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّنۢ بَعْدِ خَوْفِهِمْ أَمْنًا ۚ يَعْبُدُونَنِى لَا يُشْرِكُونَ بِى شَيْـًٔا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ

‹‹አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ይግገዙኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡››

አላህ በሰጠን ንፁህ አእምሮ ስናየው አንቀፁ በግልፅ እንዳስቀመጠው፤ ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ለማግኘት፤ አላህ እንደመስፈርት ያስቀመጠው ‹‹በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያምልኩኝ ይገዙኝ›› ይላል አላህ፡፡ ነገር ግን ይህ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም፤ አላህ ካዘነላቸው ባሪያዎች ውጭ፡፡ ወደ አላህ መንገድ የሚጣሩ ነብያትን እና የነሱን ተከታዬች፤ የእውቀት ባለቤቶች ኡለማዎችም ይሁን ዱዓቶች የታዘዙት ይህንን መሰረታዊ እና ግዴታ የሆነ ትምህርት ማህበረሰቡ ውስጥ እንዲያሰርፁ ነበር፡፡

ይህ ሆኖ ሳለ እውነታው፤ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ልክ ኡለማዎች አላህ እና መልክተኛው ያሉዋቸውን ይዘው የተውሂድ እና ሱና ያዙ፤ ሽርክ እና ቢድዐን ራቁ ብለው ትምህርት ሲሰጡ የሚከተሉትን መልሶች ይሰጣቸዋል

1) ‹‹አሜሪካ እና ኢስራኢል ስንት እየሰሩ ነው ሙስሊሙ ላይ፤ እነሱ ተውሂድ ሱና ይላሉ››
2) ‹‹ኡማው ቢበታተንስ ለምን ይህ አርስት አሁን ይነሳል››
ፊልም፤ ድራማ፤ ዘፈን፤ ሽርክ ያለባቸው ‹‹ለሺዳ›› ተብለው የሚጠሩትን፤ ሴት ልጅ አለባበሷን ታስተካክል፤ ወንድ ልጅ ሱሬውን መሬት ለመሬት አይጎትት፤ ፂሙን አይላጭ (መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መቃረን ነው)፤ ወንድ እና ሴት አይደባለቁ እና የመሰለውን ብለው ኡለማዎች ካስጠነቀቁ የሚከተለውን ይባላሉ
3) ‹‹የአለምን ተጨባጭ እና ነባራዊ እውነታ አያዩምን››

ከዚህ ሁሉ በላይ ገርሞ የሚገርመው እነ አሜሪካ እንደዚህ ከሚሉ ሙስሊሞች በላይ አውቀው በተዘዋዋሪ ሙስሊም ነን ለሚሉ ሰዎች ዘላለም አለም ሁለት አገር እሳት ውስጥ የሚከታቸውን ስራ በስጦታ መልክ ሲሰጧቸው በደስታ እና በዝምታ ይቀበላሉ፡፡ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ በግልፅ ላስቀምጥላችሁ የአላህ ባርያዎች ሆይ!
‹‹የኑር ሁሴን›› ቀብር ዩኔስኮ ውስጥ እንዲካተት፤ ከዛም አልፎ እድሳት አድርጋ ያበረከተችው አሜሪካ ናት፡፡ እንደሚታወቀው ኑር ሁሴን ቀብር ላይ ታላላቅ የሽርክ ተግባራት ይሰራሉ፡፡

ታድያ እኛ ምንድን ነው ልንሰራ የምንችለው አላህ እያንዳንዱን ነፍስ ከአቅሟ በላይ አያስገድዳትም፤ አሜሪካን እና እስራኤልን በፌስቡክ እና በየሚድያው ሲሰድቡ መዋል እና አላህ ግዴታ ያደረገብንን በእኛ አቅም በአላህ እገዛ ልንሰራው የምንችለውን ተውሂድ መማር እና ማስተማር ትተን፤ አሜሪካ እና እስራኤል እንዲህ አደረጉ እያሉ ሰዎች በሽርክ ሲቆሉ እያዩ መዋል????
መጀመሪያውኑስ አሜሬካና ኢስራኢል ሙስሊሙ አለም ላይ እንዲህ እንዲጫወቱበት ያደረጋቸው ሙስሊሞች ሰሃባዎች ከነበሩበት ትክክለኛ እምነት አፈንግጦ መውጣት እና የሽርክ እና ቢድዐ መዓትን መከተል አይደለምን????

አላህ እያንዳንዱን ነፍስ ከአቅሙ በላይ አያስገድደውም፤ እኛ አላህ በሰጠን አቅም አላህ ይቀደም ያለበትን የተውሂድ እና ሱና አጀንዳ፤ ከሽርክ እና ቢድዐ በነፍስ ወከፍ፤ ከዛም ቤተሰብ፤ ከዛም ማህበረሰቡን ማስጠንቀቅ እንስራ አላህም ከዛ በእርሱ ፍቃድ ሁሉን ፊትና ሲያበርደው እና አላህ እንዳለው ‹‹የመረጠልንን ኢስላም በሰላም ያለ ፍርሃት›› እንድንተገብረው ያደርገናል፡፡

አላህ በሰማነው የምንጠቀም ያድርገን፡፡

ምስራና ሁሉ ለአላህ ነው የሁለት አገር ደስታን በኢማን፤ በዲን፤ አላህ እና መልክተኛውን በመታዘዝ ብቻ ያደረገ፡፡ የሚቀጥለውን አለም ምንም ጥርጥር የለውም የሚወርሷት የእምነት ባለቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ ምድራዊው አለም ላይስ ደስታ እና የተመቻቸ ህይወት፤ ስቃይ መከራ የሌለበት የተድላ ህይወት በምን ይገኝ አላህ እንዲህ ይላል
مَنْ عَمِلَ صَٰلِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡ የአላህ ቃል በግልፅ እንዳስቀመጠው፤ መልካም ኑሮ ለማግኘት አምኖ መልካም ስራ መስራት ብቻ ነው፡፡ መልካም ስራ ይሆን ዘንድ ማንኛውም ስራ ለአላህ ብቻ ተብሎ ሊሰራ እና የነብያችንን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፈለግ መከተል ግድ ይለዋል፡፡ ሀይማኖቱ እንዲመቻችለት፤ ሰላምን ማግኘት የፈለገ፤ የምድር ምትክ መሆን የፈለገ፤ በጠላት ላይ የበላይ ሆኖ ተከብሮ መኖር የፈለገ ምን ማድረግ እንዳለበት አላህ ሲናገር እንዲህ ይላል፡፡
وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَيَسْتَخْلِفَنَّهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ كَمَا ٱسْتَخْلَفَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمْ دِينَهُمُ ٱلَّذِى ٱرْتَضَىٰ لَهُمْ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّنۢ بَعْدِ خَوْفِهِمْ أَمْنًا ۚ يَعْبُدُونَنِى لَا يُشْرِكُونَ بِى شَيْـًٔا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
‹‹አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ይግገዙኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡››
አላህ በሰጠን ንፁህ አእምሮ ስናየው አንቀፁ በግልፅ እንዳስቀመጠው፤ ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ለማግኘት፤ አላህ እንደመስፈርት ያስቀመጠው ‹‹በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያምልኩኝ ይገዙኝ›› ይላል አላህ፡፡ ነገር ግን ይህ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም፤ አላህ ካዘነላቸው ባሪያዎች ውጭ፡፡ ወደ አላህ መንገድ የሚጣሩ ነብያትን እና የነሱን ተከታዬች፤ የእውቀት ባለቤቶች ኡለማዎችም ይሁን ዱዓቶች የታዘዙት ይህንን መሰረታዊ እና ግዴታ የሆነ ትምህርት ማህበረሰቡ ውስጥ እንዲያሰርፁ ነበር፡፡
ይህ ሆኖ ሳለ እውነታው፤ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ልክ ኡለማዎች አላህ እና መልክተኛው ያሉዋቸውን ይዘው የተውሂድ እና ሱና ያዙ፤ ሽርክ እና ቢድዐን ራቁ ብለው ትምህርት ሲሰጡ የሚከተሉትን መልሶች ይሰጣቸዋል
1) ‹‹አሜሪካ እና ኢስራኢል ስንት እየሰሩ ነው ሙስሊሙ ላይ፤ እነሱ ተውሂድ ሱና ይላሉ››2) ‹‹ኡማው ቢበታተንስ ለምን ይህ አርስት አሁን ይነሳል››ፊልም፤ ድራማ፤ ዘፈን፤ ሽርክ ያለባቸው ‹‹ለሺዳ›› ተብለው የሚጠሩትን፤ ሴት ልጅ አለባበሷን ታስተካክል፤ ወንድ ልጅ ሱሬውን መሬት ለመሬት አይጎትት፤ ፂሙን አይላጭ (መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መቃረን ነው)፤ ወንድ እና ሴት አይደባለቁ እና የመሰለውን ብለው ኡለማዎች ካስጠነቀቁ የሚከተለውን ይባላሉ3) ‹‹የአለምን ተጨባጭ እና ነባራዊ እውነታ አያዩምን››
ከዚህ ሁሉ በላይ ገርሞ የሚገርመው እነ አሜሪካ እንደዚህ ከሚሉ ሙስሊሞች በላይ አውቀው በተዘዋዋሪ ሙስሊም ነን ለሚሉ ሰዎች ዘላለም አለም ሁለት አገር እሳት ውስጥ የሚከታቸውን ስራ በስጦታ መልክ ሲሰጧቸው በደስታ እና በዝምታ ይቀበላሉ፡፡ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ በግልፅ ላስቀምጥላችሁ የአላህ ባርያዎች ሆይ!‹‹የኑር ሁሴን›› ቀብር ዩኔስኮ ውስጥ እንዲካተት፤ ከዛም አልፎ እድሳት አድርጋ ያበረከተችው አሜሪካ ናት፡፡ እንደሚታወቀው ኑር ሁሴን ቀብር ላይ ታላላቅ የሽርክ ተግባራት ይሰራሉ፡፡
ታድያ እኛ ምንድን ነው ልንሰራ የምንችለው አላህ እያንዳንዱን ነፍስ ከአቅሟ በላይ አያስገድዳትም፤ አሜሪካን እና እስራኤልን በፌስቡክ እና በየሚድያው ሲሰድቡ መዋል እና አላህ ግዴታ ያደረገብንን በእኛ አቅም በአላህ እገዛ ልንሰራው የምንችለውን ተውሂድ መማር እና ማስተማር ትተን፤ አሜሪካ እና እስራኤል እንዲህ አደረጉ እያሉ ሰዎች በሽርክ ሲቆሉ እያዩ መዋል????መጀመሪያውኑስ አሜሬካና ኢስራኢል ሙስሊሙ አለም ላይ እንዲህ እንዲጫወቱበት ያደረጋቸው ሙስሊሞች ሰሃባዎች ከነበሩበት ትክክለኛ እምነት አፈንግጦ መውጣት እና የሽርክ እና ቢድዐ መዓትን መከተል አይደለምን????