Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“የቀበሮ ባህታዊ ከበግ መሀል ይፀልያል”(ለዐብዱልመጂድ ሑሴን ዘለፋና ዝርጠጣ የተሰጠ ምላሽ)

“የቀበሮ ባህታዊ ከበግ መሀል ይፀልያል”(ለዐብዱልመጂድ ሑሴን ዘለፋና ዝርጠጣ የተሰጠ ምላሽ)ዐብዱልመጂድ የሚባል አፍሪካ ቲቪ ላይ “የሚያስተምር” “ዳዒያህ” ለወንድም ሳዳት ከማል “ሰጠሁት” ባለው መልስ ላይ ሰለፍዮችን በጅምላ እጅግ አፀያፊ በሆኑ ውንጀላዎች ወንጅሏል፣ ሰቅጣጭ የሆኑ ውሸቶችን ዋሽቷል፡፡ እሱ ላነሳው ሁሉ መልስ መስጠት ባልችልም ጥቂት ማለት ግን ወደድኩኝ፡፡ ሃሳቦቹን እየመዘዝኩ መልስ ለመስጠት ከመሞከሬ በፊት አንድ ነገር ልበል፡፡ ልክ እንደሌሎች ኢኽዋኖችና ኢኽዋን ማይንድድ ሮቦቶች ዐብዱልመጂድም ሰለፍዮችን ለማንቋሸሽ ካነሳቸው ነጥቦች ቀዳሚው “ሰው ትዘልፋላችሁ፣ ሒክማ የላችሁም” የሚል ነው፡፡ ታዲያ እሱም ልክ እንደዘመዶቹ ምን ያህል ከዘለፋና ከስድብ የፀዳ፣ በሒክማ የሚጣራ ትሁት እንደሆነ ይታይ ዘንድ ከሱው ንግግር የሰበሰብኳቸውን የጥበብ ቃላት መግቢያ ማድረግ ፈለግኩኝ፡፡ አዲስ መስመር ላይ
((በጣት የሚቆጠሩ በጥባጮች ፣ ያልበሰሉ፣ እውቀቱ ሰርፆ ያልገባ፣ ወደ ጥመት የሚጣራ ሴንተር አላቸው፣ ወደደክም ጠላህም የሙስሊሙ አንድነት ይጠበቃል፣ እያቃጠለህ ነው፣ ከበስተጀርባችሁ አይሁድ አለ፣ የመሀይማን ጥርቅሞች፣ እሾካማ፣ መርዛማ፣ ታውረዋል፡ የውስጥ ማያዎቻቸው ታውረው፣ ቢያንቅህም ይነቅህ እንጂ ይሄ ነው ሀቁ፣ እንደቅዱሳን የሚይዟቸው እውቅና የሰጣቸው አሊሞች አሉ፣ መሀይምነት፣ ኒስፈል ዒልም፣ ከባህር በመርፌ መውሰድ ማለት ነው፣ ሳያውቁ አውቀናል የሚሉ፣ ጃሂሎች ተውሒድንና ሱናን ያውቃሉ እንዴ?፣ ገደል ማሚቶ፣ የነሱ ጀማዐ ካልሆነ ሙስሊም ሙስሊም አይመስላቸውም፡፡ ውሻ ሲጮህ ሀይ ካልከው ይብስበታል፣ ዝም በል ሲለው ዝም የሚለው ባለቤቱ ሲሆን ነው፡፡ ውስጣቸውን የሚያውቀው ነው፡፡ የሙስሊሙ አንድነት ሲመጣ ቀናችሁ፣ ተንገበገባችሁ፣ ስም መለጠፍ ጀመራችሁ፣ ብጥቅጣቂ መፅሀፎችን እያነበበ፣ እከሌ ላይ ቀራ የማይባል፣ የሱ ሸይኽ ሸይጣን ይሁን...፣ ከእውቀት በቂ እውቀት የለለው፣ ከብስለት ብስለት የለለው፣ አንተ አይገባህም፣ አታውቀውም፣ አያዎቹ ይገቡህ ይሆን?፣ አማርኛውን አንብብ፣ ሐዲሡንም አታውቀውም፣ እሱ የውስጥ አይኑ ታውሯል ይመስለኛል፣ ኡሱሉል ፊቅህ፣ ...ሲባል እንኳን ሰምታሃል?፣ ባንተ አጠገብ አልፈዋል አፍላ እድሜ ላይ ያሉ፣ ኡሱል የሚባል ነገር የሚገባህ አይመስለኝም፣...))
ቃር ቃር ብሏችሁ ከሆነ ንግግሩን በመንቀሌ ይቅርታ፡፡ ለእንዲህ አይነቱ እየዘለፈን እንድናንቆለጳጵሰው ለሚመኝ ባተሌ ለስላሳ ብእር መጠቀም ወደላይ መተኮስ ነው በከንቱ ጥይት ማባከን፡፡ አሁን ከቅጥፈቶቹ የተወሰኑትን እየቀነጨብኩ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡
1. ((በህይወቴ እኔ ከረሱል ያገኘሁት ሐቅን ሲያስተላልፉ ስድብን አንድም ቀን የተጠቀሙበት ቀን የለም፡፡ ዛቻ አዘል የሰጡበት አጋጣሚ አላውቅም፡፡))
መልስ፡- “ኧረ ይህን ሁሉ የተሳደበ ሰው እንዲህ አይልም” ብትሉ አይፈረድባችሁም፡፡ የሆነው ግን እንደዚያ ነው፡፡ በመጀመሪያ ዐብዱየ ስድብ የምትለው ምኑን ነው? ሙብተዲዑን ሙብተዲዕ፣ አጥፊን አጥፊ፣ ጠማማን ጠማማ፣ ውሸታምን ውሸታም፣... ማለት ስድብ ነው? ሰሐባን የሚሳደበውን ማጋለጥ ስድብ ነው? ይሄ ስድብ ከሆነ ቁርኣኑም ሐዲሡም የሰለፎች ንግግርም በዚህ የታጨቀ ነው፡፡ “ታሪክ አገላብጥ” እያልክ ስታንጓጥጥ የነበረው እንዲሁ በከንቱ ነው እንዴ? እሺ ይሁን በቁርኣን በሐዲሥ በታሪክም እንዲህ ካልሰማህ ታዲያ ይህን ሁሉ የስድብ ናዳ ከየት አመጣሃው? በአፍሪካ ቲቪ መዛቱንስ ምን እንበለው? “እኔ እበቃችኋለሁ” እያሉ ማቅራራቱንስ ምን ይሉታል? ሱብሐነረቢ! የሰው ልጅ እስከዚህ ይወርዳል ማለት ነው? የአላህ ተዐምር እኮ እሩቅ አይደለም የሚያገናዝብ ጠፍቶ ነው እንጂ!! እያንዳንዱን የምትገነባውን የምትወነጅልበትን ነጥብ ስታፈርስ 5 ደቂቃ አትቆይም፡፡ እስኪ ይህን የቁም ቅዠት ተመልከቱ፡፡ ለመሆኑ በህልም ነው እንዴ የተቀረፅከው?
2. ((በመሳደብ በመዘርጠጥ አይደለም፣ በሒክማ ነው)) ይላችኋል:: ስላቅ አትሉም?!! ((ይህን ቁርኣን አልቀሩትም እንዴ)) ሲል አያ አንብቧል፡፡
- መልስ፡- ግን ምናለ ምላስህን እና ጭንቅላትህን ብታስተዋውቅልን? ለመሆኑ ምን አይነት ቫይረስ ቢገባባችሁ ነው ሌሎችን በምትወነጅሉበት ጥፋት ከፍታችሁ የምትገኙት? ሌሎችን በምትተቹበት ጥፋት እናንተ ብሳችሁ መገኘታችሁ ትንሽ አይሰቀጥጣችሁም? (እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ታወራላችሁ? የማትሰሩትን ማውራታችሁ አላህ ዘንድ አስቆጪነቱ ከፋ!!) የምትለዋን አያ አልቀራሃትም እንዴ? (መፅሀፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በመልካም እያዘዛችሁ እራሳችሁን ትረሳላችሁን?? አታገናዝቡምን?!) የምትለዋ አያስ እናንተ ዘንድ ከአገልግሎት መስጫ ውጭ ናት ወይስ ጊዜ አልፎባታል?
ነዑዙ ቢላህ ሚነልኹዝላን!! ይሄ ነው እንግዲህ ህዝብ ሊያስተምር በቲቪ ድቅን የሚለው!! ይሄ ነው እንግዲህ “በሒክማ ተጣሩ” እያለ የሚሰብከው፡፡ ይብላኝ አንተን ኡስታዝ ብለው ለሚያዳምጡህ!! ይብላኝ ፊጥ ለምትልበት መድረክ፡፡
- እኔን ድንቅ ያለኝ ይህን ሁሉ ከቀባጠርክ በኋላ “እቺ የተናገርካት ምላስህ ነገ ትያዛለች” እያልክ በአላህ ማስፈራራትህ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ካልክ በኋላ ዐብዱልመጂድ?!!! ማፈር ይህን ያክል ገደደ ማለት ነው? እውነት ይቺ ካንተ ነው የወጣችው?!! እውነትም “ቀድ የስዱቁል ከዙቡ!!” እስኪ ይህን የቀበሮ ባህታዊ ተመልከቱ፡፡ ለ 45 ደቂቃ ሙሉ የስድብና የዘለፋ ናዳ ሲያዘንብ ቆይቶ “አላህን ፍሩ” ማለት ምን ማለት ነው? “የቀበሮ ባህታዊ ከበግ መሀል ይፀልያል!!!” አሉ፡፡
3. ((አንድ አሊም ኢኽዋኖች ካፊር ናቸው የሚል ካለ አምጣልኝ)) እያለ ደጋግሞ ፎክሯል፡፡
መልስ፡- ኧረ ህሊናህን አክብር ሸህ አብዱ?! ባዶ ሜዳ ላይ ማቅራራት ምን የሚሉት አማርኛ ነው? አውሬው ያለው ከጫካ አንተ የምትፎክረው ከሰፈር !! እውነት ተክፊርን የምታስጠነቅቅ ከሆነ ኡማውን በጅምላ ስለሚያከፍረው ሰይድ ቁጥብ ምነው አንድ ነገር አላልክም? ኪታቡ እኮ በሀገራችን ሞልቷል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማጥመድ የእንግሊዝኛ ቅጂው በየካፓሱ ሲከፋፈል የት ነበርክ? ካሰኘህ “ሀሰት ነው አያከፍርም” በልና ሙግቱን ማስቀጠል ትችላለህ፡፡ ያኔ የበለጠ የሚመርህን ታገኛለህ፡፡ ከዚያ በተረፈ “ኢኽዋኖች ካፊሮች ናቸው” የሚል አንድም ሰለፊ የለም፡፡ መልካችሁ ብዙ አይነት ቢሆንም አንድ የጋራ ባህሪ ግን አላችሁ፡፡ ውሸት!!! “እፍ” ያላችሁ ውሸታሞች ናችሁ!! ውሸታም ዳዒያህ ምን ያስተምራል? ውሸት ካልሆነ በቀር? ትምህርታችሁ ውሸት! ደሊላችሁ ውሸት! አጃቢያችሁ ውሸት! ትግላችሁ የውሸት! ማህበረ-ሀሳውያን!!
4. ((ዝም ብሎ አማርኛ ስለቻሉ አይደለም፡፡ ዐረብኛ ስላነበነቡ አይደለም)) ብለሃል፡፡
መልስ፡- 45 ደቂቃ ሙሉ ስትዘበዝብ ከተናገርካቸው ጥቂት እውነቶች አንዱ ይሄ ነው፡፡ ኦሪጅናሉ ቢቀር የንግግርህ የመጀመሪያ ኮፒ ላንተ አለመድረሱ ግን ደንቆኛል፡፡ ምናለ ጭንቅላትህን ትዝብት ላይ ባትጥል? ደግሞም አብረህ ያዝልን የቲቪ መድረክ ስለተገኘም ዝም ብሎ አይወራም፡፡
5. ((እኛ የምናውቀው ምን ደርሶብሃል? ሀቅን አስተምረህ ከሆንክ ምን ደርሶብሃል?)) ብለሃል፡፡
መልስ፡- “እኛ” ስትል እናንተ እነማን ናችሁ? እስከዛሬ እንዲህ እያላችሁ ትጠይቁ ነበርና እስኪ አሁን ተጠየቅ፡፡ ደግሞስ የደረሰብንን እናንተ ካላወቃችሁት በቃ የመንግስት ተባባሪ ነን ማለት ነው? ወላሂ ቃላትህ ቀለም ካሸተተ ሰው የሚወጡ አይመስሉም፡፡ እስኪ እኛስ የምናወቀው አንተ ምን ደርሶብሃል? “ለናንተ ሪፖርት ማቅረብ የለብኝም” ትል ይሆናል፡፡ እኛስ ለናንተ ማቅረብ ነበረብን? ስለ አሕባሽ “ይህን ሰርተናል፣ ይህን አርገናል” እያልን ለናንተ ሪፖርት ካላቀረብን በቃ ከአሕባሽ ጎን ነው ያለነው ማለት ነው? ኧረ ማኖ ሊቃነ-ፍልስፍና!!
6. ((ቀልቡን ሰንጥቀህ አይተኸዋልን?)) ብለሃል፡፡
መልስ፡- ቀልባችንን ሰንጥቀህ አይተህ ነው (ከበስተጀርባችሁ አይሁድ አለ፣ ለመበታተን የመጡ ይመስላሉ፣ የመንግስት ተልእኮ እንዳይኖራቸው)? ያልከው፡፡ ጭንቅላታችሁ በምን አይነት የማገናዘብ ድርቅ ቢመታ ነው እየገነባችሁ የምታፈርሱት? እየካባችሁ የምትንዱት? እንዲህ አይነት ትርምሱ የወጣ ሂሳባችሁን ያየ አንድ ወንድም “ግን እንዴት ነው ትምህርት የሚገባችሁ?” ያለው አይረሳኝም፡፡ ግን ምናለ በጭንቅላታችሁ ላይ ሰዎችን ባታስቁ?!
7. ((መንግስት የነሱን ሴንተር ግን አልነካም፡፡ ስንት ዱዓቶች እየተለቀሙ ሲታሰሩ እነሱ ግን በጎሪጥ አይን እንኳን አልታዩም፡፡))
መልስ፡- ከሰለፍዮች ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው በመንግስት ምንም ያልተነኩ እጅግ በርካታ የመሰሎችህም የሌሎችም ተቋሞች አሉ፡፡ በቅርቡ እንኳን ፈቃድ ያደሱ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ወይ በማታውቀው እየቀባጠርክ ነው፣ ወይ ደግሞ የጥላቻ ዳፍንት በጠራራ ፀሀይ ዐይንህን ጋርዶሀል፡፡ ከዚያ በተረፈ ግን ላንተ ሪፖርት ስላልተላከ ነው እንጂ ሰለፍዮችም በተለያየ ቦታ የተለያየ ነገር ደርሶባቸዋል፡፡
- ደግሞም በምትደነፋበት የአፍሪካ ቲቪ ላይ የሚቀርቡ ከመጅሊሱ ጋር እጅና ጓንት ሆነው የሚሰሩ አሉ፡፡ ሳዑዲ ድረስ ሄደው “ሰው ዝም ብሎ ነው የሚጮኸው ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ችግር የለም” ሲሉ የነበሩ አውቃለሁ፡፡ አወልያ እንዲወሰድ አመቻችተው ያቀረቡም አሉ፡፡ አይኔን ግንባር ያርገው ልትል ትችላለህ፡፡ የማውቀውን ነው ያወራሁት፡፡
8. (ለኢኽዋኒ ተቆርቋሪም አይደለሁም) ብለሃል፡፡
መልስ፡- እና ካልሆንክ ምን አንጨረጨረህ?! ቀድሞ ነገር ምን ጥልቅ አደረገህ? ነው “ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም” ነው ነገሩ? ቀጠልክና “ብሆንም ችግር የለም” አልከን፡፡ የምን ያዝ ለቀቅ ነው ኢኽዋኒ ነህ!! “ኢኽዋን ነህ” ለማለት የነሙርሲን ፓርቲ መታወቂያ እስከምትይዝ አንጠብቅህም!! ኢኽዋን በዐሊሞች አንደበት ሙብተዲዕ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ለሙብተዲዕ የሚሟገተው ወይ ከፋታቸውን የማያውቅ መሀይም ነው፡፡ ካልሆነ የጥፋታቸው ተጋሪ የሆነ ሙብተዲዕ ነው፡፡ ያሻህን ማንሳት ትችላለህ፡፡
9. ((ኢኽዋኒ ነኝ ብየ አላወጅኩልህ?)) ብለህ ኢኽዋኒ እንዳልሆንክ ልትነግረን ሞክረሃል፡፡
መልስ፡- እኛስ “ከጀርባችን አይሁድ አለ” ብለን አውጀን ነው እንዲያ የምትለን?
- ካልታወጀ አንድ ሰው ወደ ቢድዐ ቡድኖች ተጠግቶ አይጠራም ማለት ነው? ሁሉም ለማለት በሚቀርብ መልኩ አሕባሾች “አሕባሽ ነን” አይሉም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ውስጥ አሕባሽ የለም እንበል? ይሄ ሌሎችን በማናናቅ ዘየ የምትጎረርለት እውቀትህ ጣራው ይሄው ነው ማለት ነው?
- ቢገባህ ሙብተዲዕ “ሙብተዲዕ ነኝ” ብሎም አያውቅም፡፡ ቢድዐው ሲገኝበት ግን በቢድዐው ይጠራል፡፡ ይቺ እኮ ቀላል ሂሳብ ነበረች፡፡ እናም እልሃለሁ ኢኽዋንኛ ከተነፍስክ፣ ኢኽዋንኛ ካስነጠስክ፣ ኢኽዋንኛ ካላዘንክ ኢኽዋን ነኝ እስከምትል አንጠብቅህም፡፡ ኢኽዋን ዛሬ የፖለቲካ ፓርቲ ብቻ አይደለም፣ አመለካከትም ነው እንጂ- ከፉ ነቀርሳ!! እየዋሸ የሚወነጅል፣ እያለ የለሁም የሚል፣ እንደ እስስት የሚቀያየር፣ ደም መጣጭ መዥገር ነው!!
- ደግሞ “ታሪክ አገላብጥ” እያልክ ስትጎረር አልነበር? ሌሎችን ከመምከርህ በፊት እራስህን ምከርልን እንጂ፡፡ ሰለፎች ሙብተዲዕን በስም እየጠሩ ሲያጋልጡ ነበር፡፡ ሰዎቹ “ሙብተዲዕ ነን” ብለው ነው እንዴ ኻሪጂ፣ ሙርጂኢ፣ ጀህሚ፣ ራፊዲ፣ ቀደሪ፣ ሲሏቸው የነበረው? ያኔ እንዲህ እንዳንተ ዳር ድንበር በሌለው ስፋት ተንቦርቅቆ “የአንድነት ጠላት”፣ “ታፔላ ለጣፊ”፣ “የአይሁድ ተላላኪ” አልተባሉም፡፡ ዛሬ ግን ኢኽዋን መጥቶ ሁሉም አንድ ነው አለ፡፡ በጉንም፣ ቀበሮውንም፣ ፍየሉንም፣ ተኩላውንም፣... ከአንድ ጉረኖ ውስጥ ሊያጭቅ በከንቱ ይባዝን ይዟል!!! የሙስሊሙ አንድነት ደግሞ ለቢድዐና ለሙብተዲዕ ከለላ እየሰጡ እንዲሁ በቀረርቶ የሚሳካ እንዳይመስልህ!! ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንደሚለው “ቢድዐ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው”
10. ((እኛ ሁሉንም ዐሊም እናከብራለን፡፡ አሊም አናብጠለጥልም)) ብለሃል፡፡
መልስ፡- አላህ የእውነት ያርገው፡፡ እንግዲያው ከምታከብራቸው ዓሊሞች ውስጥ ኢኽዋንን “ፀረ- ሱና”፣ “ለዐቂዳ ደንታ የሌለው”፣ “ከአይሁድ በከፋ ለኢስላም የሚያሰጋ”፣ “ከ72ቱ ጠፊ አንጃዎች ውስጥ አንዱ የሆነ”፣ “በአይሁድ የሚረዳ” “የተክፊር ወላጅ”፣ ወዘተ ብለውታል፡፡ ሀሰት የምትል ከሆነ የዐሊሞቹን ስም ዝርዝር ከነማስረጃው እጠቅሳለሁ፡፡ እነኝህን አንተ የምታከብራቸውን ዓሊሞች ተከትለው ኢኽዋንን የሚተቹትን “ከፋፋይ”፣ “መርዝ”፣ “የአይሁድ ተላላኪ” ወዘተ ማለት ከአንድ ጭንቅላት የሚወጣ ነገር ነው? ምናለ ግን ምላስህንና ጭንቅላትህን ብታስተዋውቅልን?
11. ((ብጥቅጣቂ ኪታቦችን፣ ወረቀቶችን እያነበቡ፣ ጥራዝ-ነጠቆች፣...)) ብለሃል
መልስ፡- አሁን ይሄ ወረቀት ገልጦ ከሚያነብ ሰው የሚወጣ ትችት ነው? “እኔ ትልልቅ ኪታቦችን አንብቢያለሁ” ልትለን ነው አይደል? ይሄ አባባልህ እውነትን በብዛት የሚለካ ሸውራራ እይታችሁ አንድ ነፀብራቅ ነው፡፡ እንጂማ ከቢድዐ ዶሴ አንዲት የሱና አረፍተነገር እንደምትበልጥ ሳይታለም ተፈታ ነው፡፡
12. ((ሁሌ “ቅድሚያ ለተውሒድ” “ቅድሚያ ለሱና” ይላሉ ሌላው ለሺርክ ነው የሚያስተምረው ነው ወይስ ውስጦቻቸው ታውረዋል)) ስትል ጠይቀሃል፡፡
መልስ፡- በቃ እንዲህ ነው የምትረዳው? ይህን ያክል “ቅድሚያ ለተውሒድ” ማለት የሚያስነውር ሆነ? አሁን ይሄ የተውሒድ ደዕዋ እንዳበገነህ አያሳይምን? ከመስጂድ ስታባሩ በማህበራዊ ድረ-ገፅ ማስተማራቸው እርር ድብን እንዳረገህ አያሳይምን? እኔ እንኳን ባቅሜ ቃል በቃል “ቅድሚያ ለተውሒድ” በሚል ርእስ የተፃፉ ከትንሽ እስከ ትልቅ አራት ኪታቦችን አስታውሳለሁ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ባለ ሶስት ሙጀለድ ነው፡፡ “ብጥቅጣቂ ኪታቦችን እያነበቡ” ስላልክ ነው ሙጀለድ መጥቀሴ፡፡ እንደ አቶ አብዱልመጂድ ግንዛቤ ግን እነኚህ ዐሊሞች “ቅድሚያ ለተውሒድ” ሲሉ ሌላውን “ቅድሚያ ለሺርክ” ይላሉ ማለት ነው፡፡ እስኪ ይህን ግንዛቤ ታዘቡ፡፡ በዚህ መልኩ “ከዝሙት እንጠበቅ” የሚል ሁሉ ሌሎችን “ወደዝሙት ትጣራላችሁ” ማለቱ ነው፣ “አላህን እንፋራ” የሚለው ደግሞ ሌሎችን “አላህን አትፍሩ” እያለ ያስተምራል ማለት ነው፡፡ አልሐምዱ ሊላህ ዐላ ኒዕመቲል ዐቅል!!
13. ((አክፍራቸውና ይለይልህ ባንድ ፊቱ ተክፊር አትሆኑም)) እያልክ ተሳልቀሃል፣ ጎትጉተሃል፡፡
መልስ፡- እስኪ ይህን የፍንዳታ ደዕዋ ተመልከቱ!! “ከእውቀት በቂ እውቀት የለለው፣ ከብስለት ብስለት የለለው” ማለትህን ታስታውስ ይሆን? አሁን ይሄን እውቀት እንበለው ብስለት? ጭራሽ የሰፈር ጥል አደረግከው እኮ! ወይ ጉድ!! “የቤትሽን አመል እዚያው” አለ ባለታክሲው፡፡ ((እውቀት ሲጨምር አደብም አብሮ ያድጋል)) ብለህ ነበር እኮ? አሁን ይሄ አደብ ነው አቶ ዐብዱልመጂድ?
14. ((የራሱንና የምርጡን ትውልድ ወጣትነት የሚያነፃፅር... አለ፡፡ አላህን አትፈራም ከወጣት ሰሐቦች ጋር እራስህን ስታነፃፅር)) ብለሃል፡፡
መልስ፡- ደጋግመህ “አፍላ ወጣቶች” እያልክ በጭፍን ስትወነጅል እኮ ነው ወጣትነት በራሱ የሚያስተች አይደለም በሚል ወጣት ሰሐቦችን የዘረዘረልህ፡፡ አሁን ይቺ ከባድ ሂሳብ ሆና ነው ወይስ የዘመዶችህ በሽታ ተጋብቶብህ ነው? ደግሞስ አንተ “በጣት የሚቆጠሩ ናቸው” ፣ “ኢምንት ናቸው” ያልካቸው ሰለፍዮች ውስጥ አንተን የሚወልዱ ሽማግሌዎች አሉ፡፡ ምናለ ውሸትህንም ድፍረትህንም በልክ ብታደርገው? ጆሮም፣ አይንም፣ ልብም ሁሉም እንደሚያስጠይቁ የምታስገነዝበዋን አንቀፅ ስታነብ እራስህን አትርሳ እንጂ፡፡
15. ((ሰላማዊ ሰልፍ ለመከልከል አንድ ማስረጃ የላቸውም)) ብለሃል፡፡
መልስ፡- ማስረጃ እኮ የሚጠየቀው ከልካዩ አይደለም፡፡ እያነጠርክ ስትጎርርበት የነበርከው የኡሱል እውቀት የት ገባ?!! ደግሞ አታጭበርብር ሰልፍ የከለከሉት የሳውዲ ዓሊሞች ብቻ አይደሉም፡፡ እኔ ግን ከርካሽ ስድቦቹ በከፋ እየደነቀኝ ያለው ገደብ ያጣሁለት ውሸቱ ነው፡፡ ቆይ ግን “ዋሽ” እያለ ጥይት የደቀነብህ አል እንዴ? ኧረ “ሙስሊም አይዋሽም” የሚል ህፃን አዋቂው የማይስተው ሐዲሥ አለ አጎቴ?
16. ((ኢስላም የማይቀበላቸውን ስሞች ከየት እንዳመጡት አይታወቅም)) ብለሃል፡፡
መልስ፡- ኢኽዋን፣ ተብሊግ፣ ኸዋሪጅ፣... ከየት እንደመጡ የማታውቀው አንተ ነህ፣ በራስህ ምስክርነት፡፡ ወይ ደግሞ በጠራራ ፀሀይ እየካድክ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ሌላ ቦታ “ኢኽዋኑን ኢኽዋን ይላሉ፣ ተብሊጉን ተብሊግ ይላሉ” እያለ ማውራቱ ነው፡፡ ይሄ ማለት እኮ እየለጠፍን ሳይሆን በተጨባጭ አረጋግጠን ነው የምንለው ማለት ነው፡፡ ሳታስበው የሚወጣብህ ቃል አለ ልበል?
17. ((ያለበለዚያ፣ ማንነታችሁን ከነስም ዝርዝራችሁ አወጣችኋለሁ፣ ከነአካውንታችሁ፣ እኔ እበቃችኋለሁ፣ በአፍሪካ ቲቪ አጋልጣችኋለሁ፣ ሁሉም ነገር በጃችን ነው፡፡...)) እያለ እየማለ ዝቶብናል፡፡
መልስ፡- ወይኔ የት እንግባi ዓጂብ እኮ ነው!! እስከዛሬስ መች አርፋችሁ ነው እንዲህ የምትደነፋው? በየመስጂዱ ስትሰሩት የነበረው ይሄው አልነበር? “ተክፊር ናቸው፣ ጴንጤ ናቸው፣ አይሁድ ናቸው” ማለቱን እኮ ዚክር ካረጋችሁ አመታት ተቆጠሩ፡፡ “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” አይነት አካሄዳችሁ ተፅእኖ አሳድሮባቸው በጥርጣሬ የሚያዩን ብዙ እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ ይሄ ቀረርቶህ “እምቢ ካለ እያንዳንዱን እስከ ድንበር እየተከተልን ... ...ን ነው በጩቤ የምንወጋው” የሚለውን የመንግስቱ ሃ/ማርያምን ዛቻ አስታወሰኝ፡፡ ለምን አስታወስክ እንዳትለኝ እንጂ፡፡ ((አንዳንዴ መናገር ሳልፈልግ እንድናገር የሚያደርጉኝ፣..)) ይለናል፡፡ እስኪ በራስህ ቃል ልጠይቅህ፡፡ አንተ ማን ሆነህ ነው እንዲህ የምታቅራራው? እዚች ጋ አንድ ወንድሜ ለነዚህ ሰዎች የተናገራትን ልዋስማ፡፡ “እኛ እኮ ታኮ ብናረግላቸው እየዘለሉ አስቸገሩን!!” ሁሌ ቁልቁል ይወርዳሉ!! መጨረሻቸው የት እንደሆነ አናውቅም!! ለማንኛውም አደራህን ኒኩለር እንዳትተኩስብንi ምን ይታወቃል? “ሁሉም በእጃችን ነው” ስትል ጊዜ እኮ...፡፡ ከዚያ ውጭ እንኳን ያለው ብዙ አይጨንቀንም፡፡ አፍሪካ ቲቪንም፣ በእጃችሁ ያለውን ሁሉንም ተጠቅማችሁ፣ አይደለም የኢትዮጵያን ህዝብ፣ አለም ጋር ብታጣሉን አይሞቀን አይበርደን፡፡ ”አላህ ለኛ የፃፈለን እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ ይላል ጌታችን፡፡ “እወቅ! ህዝቦች በሙሉ ሊጎዱህ ቢሰበሰቡ አላህ በወሰነብህ ካልሆነ በቀር በምንም አይጎዱህም፡፡” “ያገኘህ ነገር የሚስትህ አልነበረም፡፡ የሳተህም ነገር የሚያገኝህ አልነበረም፡፡ ብእሮቹ ተነስተዋል፡፡ መዝገቦቹ ደርቀዋል፡፡” ይላሉ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
18. ጥቂት የዐብዱልመጂድን ውሸቶች ልቀንጭብላችሁማ፡፡ (((በሀገራችን ያሉ ሰለፍዮችን) በጣት የሚቆጠሩ፣ ኢምንት ናቸው))፣ ((ኢህአዴግን የሚቃወሙትን “የኢኽዋኒ ስብስብ ናቸው” ይላሉ))፣ ((የሙስሊሙ አንድነት ሲመጣ ጊዜ ቀኑ፣ ተንገበገቡ! ስም መለጠፍ ጀመሩ)) ((“የምናባቱ ወልይ ነው” እያሉ ደዕዋ ያደርጋሉ...፣ ((“አንድ ሁኑ” ሲባል “ሙስሊምና ሙሽሪክ አንድ አይሆንም” ይላሉ)) ((ከበስተጀርባቸው አይሁድ አለ)) ቱቱቱ...
መልስ፡- እስኪ ይህን የውሸት ጋጋታ ተመልከቱ፡፡ “ካላፈርክ ያሻህን ስራ” ይላሉ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡ “ኧረ አላህን ፍራ!” ልልህ ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው? ይሄ ቋንቋ አይገባህ? “መሳጂድ ስታፍኑባቸው የነበሩ ሰዎች በማህበራዊ ድረ-ገፆች ስለተውሒድ ስላስተማሩ ቆጫችሁ፣ አቃጠላችሁ ለሺርክ አለቀሳችሁ!!” ብንል ደስ ይልሃልን? ከፊል እውነት ከመያዙም ጋር፡፡ መቼም አንተ ስትዘረጥጥ አፋቸውን ለጉመው ይቀመጣሉ ብለህ የምታስብ ቂል አትመስለኝም፣ እርግጠኛም ባልሆን፡፡ (እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጥፉ ሰዎች አይድኑም) የሚለውን አንቀፅ እኮ መግቢያህ ላይ ቀርተኸው ነበር፡፡ አንተ ጋ ትርጉሙ ሌላ ነው እንዴ? እንዳውም ያንተኑ አማርኛ ልጠቀምማ “ዐረብኛው ከሌለህ ለምን አማርኛውን አታነብም?” ችግሩ እዚያም ይከትልህ እንደሁ አላውቅም እንጂ፡፡ ሰውየው ውሸት የመተንፈስ ያክል የቀለለው ቅልል ያለ ጉድ ነው!! ቢላሂ ዐለይኩም አለመግባባት ቢኖርስ ከቻሉ “አይተናል” የሚሉትን ጥፋት ማጋለጥ እንጂ ውሸቱን ምን አመጣው? እድሜ ለኢኽዋን ውሸታም ዳዒዎችን አፈራልን፡፡ ገና ብዙ እንጠብቃለን፡፡ ሙዚቀኛ ሸይኾች አርቲስት ኸጢቦች!!! ኡስታዙ እንዲህ ከዋሸ ከተማሪዎቹ ምን ይጠበቃል? “አስተማሪ ከፈሳ ተማሪ ይቀዝናል” አሉ፡፡
እኔ ግን አድንቄሃለሁ፡፡ በ45 ደቂቃ ብቻ ይህን ሁሉ ቅጥፈት፣ ዘለፋ፣ ልጠፋ፣ ዝርጠጣ ማውጣት ከቻልክ ወደ ፊት ጥሩ የስድብ መዝገበ-ቃላት የማውጣት ብቃቱ አለህ፡፡ ጅምሩንም በአፍሪካ ቲቪ እንጠብቃለን፡፡ ብራቮ ኢኽዋን!!
ዐብዱልመጂድ! እኛም እንደናንተ ሰዎችን የሚያስደስት ርእስ እየመረጥን ማውራት፣ ሁሉን እንደስሜቱ ማስተናገድ፣ ብሎም ደጋፊና አድናቂ ማፍራት አላቃተንም፡፡ ወተላሂ እናንተ እንደምትገምቱትም እንደምታላዝኑትም ሙስሊሙን የመበታተን አባዜ የለብንም!! ገና ሰው እንዳይቀየመን በሚል ህዝብ የተነከረበትን ጥፋት ገሸሽ አድርገን ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ ማውራቱን ግን ሃላፊነት የጎደለው፣ ነገ ፀፀት ላይ የሚጥል፣ ከንቱ ሽወዳ እንደሆነ አምነን ትተነዋል፡፡ የሰውን ስሜት እየተከተሉ መፍሰስ የኢኽዋን ልዩ መታወቂያ ነው፡፡ ልክ አንተ በአፍሪካ ቲቪ ልታስፈራራ እንደሞከርከው በደሊል ሳይሆን በመሀይማን ቲፎዞ ሌሎችን ማስፈራራት የሙብተዲዖች ነባር መገለጫ ነው፡፡ አላማህ “አፍሪካ ቲቪን ተጠቅሜ መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ እከፍታለሁ” ነው፡፡ እስካሁንስ ምን ላይ ሆናችሁ? መድረክ ላይ ፊጥ ባልክ ቁጥር እንደማስቲካ ማኘክ ካማረክ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ፡፡ ከዚያ “አፍሪካ ቲቪን ሲቃወሙ ሰው ሁሉ ይነሳባቸዋል” ነው፡፡ የዋህ! እንዲህ አይነቱን ማስፈራሪያ ዋጋ ብንሰጠውማ ቀድመንም መንገዳችሁን መንገዳችን ባደረግን ነበር፡፡ ብታሾፉም ብትሳለቁም በማስረጃ ሳይሆን እንደፓርላማ በእጅ ብልጫ ነገሮችን ለሚለካ አሉባልተኛ ቅንጣት ታክል ጆሮ አንሰጠውም፡፡
ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ነበር፡፡ ትንሽ ህሊናን ማሰራት እንጂ ሌላ አይጠይቅምና፡፡ ይሁን እንጂ ለወላእና ለበራእ ይህ ነው የሚባል ቦታ የሌለው፣ በሐቅና በባጢል መሀል የማያወላዳ መለያ ያላስቀመጠ፤ ለአላህ ብሎ የመውደድንና ለአላህ ብሎ የመጥላትን አርኪ ጣእም ያላጣጣመ፤ በሐቅ ሒሳብ መላው ሁለት እግራን ለማስደሰት የሚጥር፤... ከሰለፎቹ በላይ ዲን አዋቂ፣ ለኡማው ተቆርቋሪ መስሎ የሚቀርብ ጥራዝ-ነጠቅ ነጭና ጥቁር አይለይም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ህሊና ዲስኮ ሰዐት ማለት ነው- የተበላሸ ዲስኮ፡፡ የተበላሸ ዲስኮ አንዱን ቁጥር ከሌላው ሳይለይ ሁሉንም ስምንት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ቀኑ 88፡፡ሌቱ 88፡፡ ትላንትም 88፡፡ ዛሬም 88፡፡ ጧትም 88፡፡ ማታም 88፡፡ ክፉ ህመም!! ይህም እንደዚያው ነው፡፡ ሰባ ሁለቱም ጠማማ አንጃዎች ቢደረደሩ ከእውነተኛው ቡድን ለይቶ አያያቸውም፡፡ እሱ ዘንድ በኢስላም ስም እስከተንቀሳቀሱ ድረስ ሁሉም ለኢስላም እየሰሩ ነው፡፡ “አንዳንድ ችግሮች ቢኖሩም በውይይት ይፈታል” ይላችኋል፡፡ ሰለፎች “እከሌ ጀህሚ ነው”፣ “እከሌ ኻሪጂ ነው”፣ “እከሌ ቀደሪ ነው”፣ “እከሌ ጠማማ ነው”፣... ሲሉ የነበረውን ልዩነት በውይይት መፍታት አቅቷቸው ኖሯልን? እነ ዐብዱልመጂድ ግን ሙብተዲዖቹን ጥለው “እናንተ ብቻ ሱኒ ሌላው ሙብተዲዕ” እያሉ ይሳለቃሉ፡፡ ሁሉን ሱኒ ሊያደርግ በጠራራ ይጮሃል፡፡ ለኢኽዋኒው ይጮሃል፣ ለተብሊጉ ይጮሃል፣ ለሱፊው ይጮሃል፣ ለአሽዐሪው ይጮሃል፣ ለአልቃኢዳው (ለኸዋሪጁ) ይጮሃል፣ ለሺዐው ይጮሃል፣ ሰሐባን ለሚሳደበው ለሰይድ ቁጥብ ይጮሃል፣... ምን አለፋችሁ በሆነ መስመር ላይ ከተላተማቸው ሙብተዲዖች ውጭ ለሁሉም ይጮሃል፡፡ ልብ በሉ ጩኸቱ “በአንድነት” ስም ነው፡፡ “ሀሰት” እንደምትል እጠብቃለሁ፡፡ እንግዲያው እስኪ ይህን የምትፎክርበትን የምታስፈራራበትን አፍሪካ ቲቪ ተጠቅመህ ሰለ ኢኽዋን፣ ስለ ተብሊግ፣ ስለሱፊያህ፣ ስለ አሽዐርያህ፣ ተናግረሃልን? በኢስላም ስም በስሜት እየተነዳ የኢስላምን አንፀባራቂ ውበት ጥላሸት እየቀባ ስላለው አልቃኢዳስ አፍረጥርጠህ አውጥታሃልን? ነው እነሱ ጀግኖችህ ናቸው? ሽንጡን ገትሮ ስለሙዚቃ ስለሚሰብከው ሐሰን ታጁ በአፍሪካ ቲቪ አውርተሃልን? ይሄን ሁሉ ያደረገው ሰለፍዩ ቢሆን ስንት በቀባጠራችሁ ነበር?! አመት ብታወሩት አይሰለቻችሁም ነበር፡፡ ለተውሒድ ሲሆን ዶማ ናችሁ ለነገር ሲሆን ግን ሹል ናችሁ ከመርፌ የሾላችሁ፡፡ ከነዚህ ይልቅ የሰለፍዩ አደጋ ስለከፋ ነው በአፍሪካ ቲቪ የምትዝተው? በነ አልባኒ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ኢብኑ ባዝ ስም ባደባባይ ትነግዳላችሁ፡፡ ይሄው እነኚህ ዓሊሞች እነዚህን ጠማማ አንጃዎችና ድርጊቶቻቸውን አንዴ አይደለም ደግመው ደጋግመው አውግዘዋል፡፡ እናንተ ግን መንታ ፊት ሆናችሁ በስማቸው ተከልላችሁ አካሄዳቸውን ትወጋላችሁ፡፡
በመጨረሻም ወላሂ ከንቱ ውንጀላዎችህን እንደ አጥጋቢ ደሊል የሚመለከቱ መሳኪን ባይኖሩ ኖሮ ዝብርቅርቅ ያለ አማርኛህን፣ አሁንም አሁንም የምትደጋግመው ባዶ ዛቻህን፣ እጅ እጅ የሚል እንቶፈንቶህን ጨርሼ ለማዳመጥ፣ አልፎም መልስ ለመስጠት ትእግስቱም አልነበረኝ፡፡ “መልስ መስጠት አለብኝ” ብየ ስለተነሳሁ ብቻ ረጃጂምና አሰልቺ የሆኑ 45 ደቂቃዎችን ተሰቃይቻለሁ፡፡ ስጨርስ እንዴት እንዳንቀጠቀጠኝ ብነግርህ...፡፡ እንግዲህ አንተንም ዳዒያህ ብሎ አፉን ከፍቶ የሚያዳምጥ አለ ማለት ነው፡፡ “ቅል ግጥሙን አያጣም” አለ ያገሬ ሰው፡፡ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!
((በጣት የሚቆጠሩ በጥባጮች ፣ ያልበሰሉ፣ እውቀቱ ሰርፆ ያልገባ፣ ወደ ጥመት የሚጣራ ሴንተር አላቸው፣ ወደደክም ጠላህም የሙስሊሙ አንድነት ይጠበቃል፣ እያቃጠለህ ነው፣ ከበስተጀርባችሁ አይሁድ አለ፣ የመሀይማን ጥርቅሞች፣ እሾካማ፣ መርዛማ፣ ታውረዋል፡ የውስጥ ማያዎቻቸው ታውረው፣ ቢያንቅህም ይነቅህ እንጂ ይሄ ነው ሀቁ፣ እንደቅዱሳን የሚይዟቸው እውቅና የሰጣቸው አሊሞች አሉ፣ መሀይምነት፣ ኒስፈል ዒልም፣ ከባህር በመርፌ መውሰድ ማለት ነው፣ ሳያውቁ አውቀናል የሚሉ፣ ጃሂሎች ተውሒድንና ሱናን ያውቃሉ እንዴ?፣ ገደል ማሚቶ፣ የነሱ ጀማዐ ካልሆነ ሙስሊም ሙስሊም አይመስላቸውም፡፡ ውሻ ሲጮህ ሀይ ካልከው ይብስበታል፣ ዝም በል ሲለው ዝም የሚለው ባለቤቱ ሲሆን ነው፡፡ ውስጣቸውን የሚያውቀው ነው፡፡ የሙስሊሙ አንድነት ሲመጣ ቀናችሁ፣ ተንገበገባችሁ፣ ስም መለጠፍ ጀመራችሁ፣ ብጥቅጣቂ መፅሀፎችን እያነበበ፣ እከሌ ላይ ቀራ የማይባል፣ የሱ ሸይኽ ሸይጣን ይሁን...፣ ከእውቀት በቂ እውቀት የለለው፣ ከብስለት ብስለት የለለው፣ አንተ አይገባህም፣ አታውቀውም፣ አያዎቹ ይገቡህ ይሆን?፣ አማርኛውን አንብብ፣ ሐዲሡንም አታውቀውም፣ እሱ የውስጥ አይኑ ታውሯል ይመስለኛል፣ ኡሱሉል ፊቅህ፣ ...ሲባል እንኳን ሰምታሃል?፣ ባንተ አጠገብ አልፈዋል አፍላ እድሜ ላይ ያሉ፣ ኡሱል የሚባል ነገር የሚገባህ አይመስለኝም፣...)) ቃር ቃር ብሏችሁ ከሆነ ንግግሩን በመንቀሌ ይቅርታ፡፡ ለእንዲህ አይነቱ እየዘለፈን እንድናንቆለጳጵሰው ለሚመኝ ባተሌ ለስላሳ ብእር መጠቀም ወደላይ መተኮስ ነው በከንቱ ጥይት ማባከን፡፡ አሁን ከቅጥፈቶቹ የተወሰኑትን እየቀነጨብኩ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡1. ((በህይወቴ እኔ ከረሱል ያገኘሁት ሐቅን ሲያስተላልፉ ስድብን አንድም ቀን የተጠቀሙበት ቀን የለም፡፡ ዛቻ አዘል የሰጡበት አጋጣሚ አላውቅም፡፡))መልስ፡- “ኧረ ይህን ሁሉ የተሳደበ ሰው እንዲህ አይልም” ብትሉ አይፈረድባችሁም፡፡ የሆነው ግን እንደዚያ ነው፡፡ በመጀመሪያ ዐብዱየ ስድብ የምትለው ምኑን ነው? ሙብተዲዑን ሙብተዲዕ፣ አጥፊን አጥፊ፣ ጠማማን ጠማማ፣ ውሸታምን ውሸታም፣... ማለት ስድብ ነው? ሰሐባን የሚሳደበውን ማጋለጥ ስድብ ነው? ይሄ ስድብ ከሆነ ቁርኣኑም ሐዲሡም የሰለፎች ንግግርም በዚህ የታጨቀ ነው፡፡ “ታሪክ አገላብጥ” እያልክ ስታንጓጥጥ የነበረው እንዲሁ በከንቱ ነው እንዴ? እሺ ይሁን በቁርኣን በሐዲሥ በታሪክም እንዲህ ካልሰማህ ታዲያ ይህን ሁሉ የስድብ ናዳ ከየት አመጣሃው? በአፍሪካ ቲቪ መዛቱንስ ምን እንበለው? “እኔ እበቃችኋለሁ” እያሉ ማቅራራቱንስ ምን ይሉታል? ሱብሐነረቢ! የሰው ልጅ እስከዚህ ይወርዳል ማለት ነው? የአላህ ተዐምር እኮ እሩቅ አይደለም የሚያገናዝብ ጠፍቶ ነው እንጂ!! እያንዳንዱን የምትገነባውን የምትወነጅልበትን ነጥብ ስታፈርስ 5 ደቂቃ አትቆይም፡፡ እስኪ ይህን የቁም ቅዠት ተመልከቱ፡፡ ለመሆኑ በህልም ነው እንዴ የተቀረፅከው?2. ((በመሳደብ በመዘርጠጥ አይደለም፣ በሒክማ ነው)) ይላችኋል:: ስላቅ አትሉም?!! ((ይህን ቁርኣን አልቀሩትም እንዴ)) ሲል አያ አንብቧል፡፡- መልስ፡- ግን ምናለ ምላስህን እና ጭንቅላትህን ብታስተዋውቅልን? ለመሆኑ ምን አይነት ቫይረስ ቢገባባችሁ ነው ሌሎችን በምትወነጅሉበት ጥፋት ከፍታችሁ የምትገኙት? ሌሎችን በምትተቹበት ጥፋት እናንተ ብሳችሁ መገኘታችሁ ትንሽ አይሰቀጥጣችሁም? (እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ታወራላችሁ? የማትሰሩትን ማውራታችሁ አላህ ዘንድ አስቆጪነቱ ከፋ!!) የምትለዋን አያ አልቀራሃትም እንዴ? (መፅሀፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በመልካም እያዘዛችሁ እራሳችሁን ትረሳላችሁን?? አታገናዝቡምን?!) የምትለዋ አያስ እናንተ ዘንድ ከአገልግሎት መስጫ ውጭ ናት ወይስ ጊዜ አልፎባታል?ነዑዙ ቢላህ ሚነልኹዝላን!! ይሄ ነው እንግዲህ ህዝብ ሊያስተምር በቲቪ ድቅን የሚለው!! ይሄ ነው እንግዲህ “በሒክማ ተጣሩ” እያለ የሚሰብከው፡፡ ይብላኝ አንተን ኡስታዝ ብለው ለሚያዳምጡህ!! ይብላኝ ፊጥ ለምትልበት መድረክ፡፡ - እኔን ድንቅ ያለኝ ይህን ሁሉ ከቀባጠርክ በኋላ “እቺ የተናገርካት ምላስህ ነገ ትያዛለች” እያልክ በአላህ ማስፈራራትህ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ካልክ በኋላ ዐብዱልመጂድ?!!! ማፈር ይህን ያክል ገደደ ማለት ነው? እውነት ይቺ ካንተ ነው የወጣችው?!! እውነትም “ቀድ የስዱቁል ከዙቡ!!” እስኪ ይህን የቀበሮ ባህታዊ ተመልከቱ፡፡ ለ 45 ደቂቃ ሙሉ የስድብና የዘለፋ ናዳ ሲያዘንብ ቆይቶ “አላህን ፍሩ” ማለት ምን ማለት ነው? “የቀበሮ ባህታዊ ከበግ መሀል ይፀልያል!!!” አሉ፡፡3. ((አንድ አሊም ኢኽዋኖች ካፊር ናቸው የሚል ካለ አምጣልኝ)) እያለ ደጋግሞ ፎክሯል፡፡መልስ፡- ኧረ ህሊናህን አክብር ሸህ አብዱ?! ባዶ ሜዳ ላይ ማቅራራት ምን የሚሉት አማርኛ ነው? አውሬው ያለው ከጫካ አንተ የምትፎክረው ከሰፈር !! እውነት ተክፊርን የምታስጠነቅቅ ከሆነ ኡማውን በጅምላ ስለሚያከፍረው ሰይድ ቁጥብ ምነው አንድ ነገር አላልክም? ኪታቡ እኮ በሀገራችን ሞልቷል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማጥመድ የእንግሊዝኛ ቅጂው በየካፓሱ ሲከፋፈል የት ነበርክ? ካሰኘህ “ሀሰት ነው አያከፍርም” በልና ሙግቱን ማስቀጠል ትችላለህ፡፡ ያኔ የበለጠ የሚመርህን ታገኛለህ፡፡ ከዚያ በተረፈ “ኢኽዋኖች ካፊሮች ናቸው” የሚል አንድም ሰለፊ የለም፡፡ መልካችሁ ብዙ አይነት ቢሆንም አንድ የጋራ ባህሪ ግን አላችሁ፡፡ ውሸት!!! “እፍ” ያላችሁ ውሸታሞች ናችሁ!! ውሸታም ዳዒያህ ምን ያስተምራል? ውሸት ካልሆነ በቀር? ትምህርታችሁ ውሸት! ደሊላችሁ ውሸት! አጃቢያችሁ ውሸት! ትግላችሁ የውሸት! ማህበረ-ሀሳውያን!!4. ((ዝም ብሎ አማርኛ ስለቻሉ አይደለም፡፡ ዐረብኛ ስላነበነቡ አይደለም)) ብለሃል፡፡መልስ፡- 45 ደቂቃ ሙሉ ስትዘበዝብ ከተናገርካቸው ጥቂት እውነቶች አንዱ ይሄ ነው፡፡ ኦሪጅናሉ ቢቀር የንግግርህ የመጀመሪያ ኮፒ ላንተ አለመድረሱ ግን ደንቆኛል፡፡ ምናለ ጭንቅላትህን ትዝብት ላይ ባትጥል? ደግሞም አብረህ ያዝልን የቲቪ መድረክ ስለተገኘም ዝም ብሎ አይወራም፡፡ 5. ((እኛ የምናውቀው ምን ደርሶብሃል? ሀቅን አስተምረህ ከሆንክ ምን ደርሶብሃል?)) ብለሃል፡፡መልስ፡- “እኛ” ስትል እናንተ እነማን ናችሁ? እስከዛሬ እንዲህ እያላችሁ ትጠይቁ ነበርና እስኪ አሁን ተጠየቅ፡፡ ደግሞስ የደረሰብንን እናንተ ካላወቃችሁት በቃ የመንግስት ተባባሪ ነን ማለት ነው? ወላሂ ቃላትህ ቀለም ካሸተተ ሰው የሚወጡ አይመስሉም፡፡ እስኪ እኛስ የምናወቀው አንተ ምን ደርሶብሃል? “ለናንተ ሪፖርት ማቅረብ የለብኝም” ትል ይሆናል፡፡ እኛስ ለናንተ ማቅረብ ነበረብን? ስለ አሕባሽ “ይህን ሰርተናል፣ ይህን አርገናል” እያልን ለናንተ ሪፖርት ካላቀረብን በቃ ከአሕባሽ ጎን ነው ያለነው ማለት ነው? ኧረ ማኖ ሊቃነ-ፍልስፍና!!6. ((ቀልቡን ሰንጥቀህ አይተኸዋልን?)) ብለሃል፡፡መልስ፡- ቀልባችንን ሰንጥቀህ አይተህ ነው (ከበስተጀርባችሁ አይሁድ አለ፣ ለመበታተን የመጡ ይመስላሉ፣ የመንግስት ተልእኮ እንዳይኖራቸው)? ያልከው፡፡ ጭንቅላታችሁ በምን አይነት የማገናዘብ ድርቅ ቢመታ ነው እየገነባችሁ የምታፈርሱት? እየካባችሁ የምትንዱት? እንዲህ አይነት ትርምሱ የወጣ ሂሳባችሁን ያየ አንድ ወንድም “ግን እንዴት ነው ትምህርት የሚገባችሁ?” ያለው አይረሳኝም፡፡ ግን ምናለ በጭንቅላታችሁ ላይ ሰዎችን ባታስቁ?!7. ((መንግስት የነሱን ሴንተር ግን አልነካም፡፡ ስንት ዱዓቶች እየተለቀሙ ሲታሰሩ እነሱ ግን በጎሪጥ አይን እንኳን አልታዩም፡፡))መልስ፡- ከሰለፍዮች ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው በመንግስት ምንም ያልተነኩ እጅግ በርካታ የመሰሎችህም የሌሎችም ተቋሞች አሉ፡፡ በቅርቡ እንኳን ፈቃድ ያደሱ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ወይ በማታውቀው እየቀባጠርክ ነው፣ ወይ ደግሞ የጥላቻ ዳፍንት በጠራራ ፀሀይ ዐይንህን ጋርዶሀል፡፡ ከዚያ በተረፈ ግን ላንተ ሪፖርት ስላልተላከ ነው እንጂ ሰለፍዮችም በተለያየ ቦታ የተለያየ ነገር ደርሶባቸዋል፡፡- ደግሞም በምትደነፋበት የአፍሪካ ቲቪ ላይ የሚቀርቡ ከመጅሊሱ ጋር እጅና ጓንት ሆነው የሚሰሩ አሉ፡፡ ሳዑዲ ድረስ ሄደው “ሰው ዝም ብሎ ነው የሚጮኸው ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ችግር የለም” ሲሉ የነበሩ አውቃለሁ፡፡ አወልያ እንዲወሰድ አመቻችተው ያቀረቡም አሉ፡፡ አይኔን ግንባር ያርገው ልትል ትችላለህ፡፡ የማውቀውን ነው ያወራሁት፡፡8. (ለኢኽዋኒ ተቆርቋሪም አይደለሁም) ብለሃል፡፡መልስ፡- እና ካልሆንክ ምን አንጨረጨረህ?! ቀድሞ ነገር ምን ጥልቅ አደረገህ? ነው “ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም” ነው ነገሩ? ቀጠልክና “ብሆንም ችግር የለም” አልከን፡፡ የምን ያዝ ለቀቅ ነው ኢኽዋኒ ነህ!! “ኢኽዋን ነህ” ለማለት የነሙርሲን ፓርቲ መታወቂያ እስከምትይዝ አንጠብቅህም!! ኢኽዋን በዐሊሞች አንደበት ሙብተዲዕ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ለሙብተዲዕ የሚሟገተው ወይ ከፋታቸውን የማያውቅ መሀይም ነው፡፡ ካልሆነ የጥፋታቸው ተጋሪ የሆነ ሙብተዲዕ ነው፡፡ ያሻህን ማንሳት ትችላለህ፡፡ 9. ((ኢኽዋኒ ነኝ ብየ አላወጅኩልህ?)) ብለህ ኢኽዋኒ እንዳልሆንክ ልትነግረን ሞክረሃል፡፡መልስ፡- እኛስ “ከጀርባችን አይሁድ አለ” ብለን አውጀን ነው እንዲያ የምትለን? - ካልታወጀ አንድ ሰው ወደ ቢድዐ ቡድኖች ተጠግቶ አይጠራም ማለት ነው? ሁሉም ለማለት በሚቀርብ መልኩ አሕባሾች “አሕባሽ ነን” አይሉም፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ውስጥ አሕባሽ የለም እንበል? ይሄ ሌሎችን በማናናቅ ዘየ የምትጎረርለት እውቀትህ ጣራው ይሄው ነው ማለት ነው?- ቢገባህ ሙብተዲዕ “ሙብተዲዕ ነኝ” ብሎም አያውቅም፡፡ ቢድዐው ሲገኝበት ግን በቢድዐው ይጠራል፡፡ ይቺ እኮ ቀላል ሂሳብ ነበረች፡፡ እናም እልሃለሁ ኢኽዋንኛ ከተነፍስክ፣ ኢኽዋንኛ ካስነጠስክ፣ ኢኽዋንኛ ካላዘንክ ኢኽዋን ነኝ እስከምትል አንጠብቅህም፡፡ ኢኽዋን ዛሬ የፖለቲካ ፓርቲ ብቻ አይደለም፣ አመለካከትም ነው እንጂ- ከፉ ነቀርሳ!! እየዋሸ የሚወነጅል፣ እያለ የለሁም የሚል፣ እንደ እስስት የሚቀያየር፣ ደም መጣጭ መዥገር ነው!!- ደግሞ “ታሪክ አገላብጥ” እያልክ ስትጎረር አልነበር? ሌሎችን ከመምከርህ በፊት እራስህን ምከርልን እንጂ፡፡ ሰለፎች ሙብተዲዕን በስም እየጠሩ ሲያጋልጡ ነበር፡፡ ሰዎቹ “ሙብተዲዕ ነን” ብለው ነው እንዴ ኻሪጂ፣ ሙርጂኢ፣ ጀህሚ፣ ራፊዲ፣ ቀደሪ፣ ሲሏቸው የነበረው? ያኔ እንዲህ እንዳንተ ዳር ድንበር በሌለው ስፋት ተንቦርቅቆ “የአንድነት ጠላት”፣ “ታፔላ ለጣፊ”፣ “የአይሁድ ተላላኪ” አልተባሉም፡፡ ዛሬ ግን ኢኽዋን መጥቶ ሁሉም አንድ ነው አለ፡፡ በጉንም፣ ቀበሮውንም፣ ፍየሉንም፣ ተኩላውንም፣... ከአንድ ጉረኖ ውስጥ ሊያጭቅ በከንቱ ይባዝን ይዟል!!! የሙስሊሙ አንድነት ደግሞ ለቢድዐና ለሙብተዲዕ ከለላ እየሰጡ እንዲሁ በቀረርቶ የሚሳካ እንዳይመስልህ!! ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንደሚለው “ቢድዐ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው”10. ((እኛ ሁሉንም ዐሊም እናከብራለን፡፡ አሊም አናብጠለጥልም)) ብለሃል፡፡መልስ፡- አላህ የእውነት ያርገው፡፡ እንግዲያው ከምታከብራቸው ዓሊሞች ውስጥ ኢኽዋንን “ፀረ- ሱና”፣ “ለዐቂዳ ደንታ የሌለው”፣ “ከአይሁድ በከፋ ለኢስላም የሚያሰጋ”፣ “ከ72ቱ ጠፊ አንጃዎች ውስጥ አንዱ የሆነ”፣ “በአይሁድ የሚረዳ” “የተክፊር ወላጅ”፣ ወዘተ ብለውታል፡፡ ሀሰት የምትል ከሆነ የዐሊሞቹን ስም ዝርዝር ከነማስረጃው እጠቅሳለሁ፡፡ እነኝህን አንተ የምታከብራቸውን ዓሊሞች ተከትለው ኢኽዋንን የሚተቹትን “ከፋፋይ”፣ “መርዝ”፣ “የአይሁድ ተላላኪ” ወዘተ ማለት ከአንድ ጭንቅላት የሚወጣ ነገር ነው? ምናለ ግን ምላስህንና ጭንቅላትህን ብታስተዋውቅልን?11. ((ብጥቅጣቂ ኪታቦችን፣ ወረቀቶችን እያነበቡ፣ ጥራዝ-ነጠቆች፣...)) ብለሃልመልስ፡- አሁን ይሄ ወረቀት ገልጦ ከሚያነብ ሰው የሚወጣ ትችት ነው? “እኔ ትልልቅ ኪታቦችን አንብቢያለሁ” ልትለን ነው አይደል? ይሄ አባባልህ እውነትን በብዛት የሚለካ ሸውራራ እይታችሁ አንድ ነፀብራቅ ነው፡፡ እንጂማ ከቢድዐ ዶሴ አንዲት የሱና አረፍተነገር እንደምትበልጥ ሳይታለም ተፈታ ነው፡፡12. ((ሁሌ “ቅድሚያ ለተውሒድ” “ቅድሚያ ለሱና” ይላሉ ሌላው ለሺርክ ነው የሚያስተምረው ነው ወይስ ውስጦቻቸው ታውረዋል)) ስትል ጠይቀሃል፡፡መልስ፡- በቃ እንዲህ ነው የምትረዳው? ይህን ያክል “ቅድሚያ ለተውሒድ” ማለት የሚያስነውር ሆነ? አሁን ይሄ የተውሒድ ደዕዋ እንዳበገነህ አያሳይምን? ከመስጂድ ስታባሩ በማህበራዊ ድረ-ገፅ ማስተማራቸው እርር ድብን እንዳረገህ አያሳይምን? እኔ እንኳን ባቅሜ ቃል በቃል “ቅድሚያ ለተውሒድ” በሚል ርእስ የተፃፉ ከትንሽ እስከ ትልቅ አራት ኪታቦችን አስታውሳለሁ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ባለ ሶስት ሙጀለድ ነው፡፡ “ብጥቅጣቂ ኪታቦችን እያነበቡ” ስላልክ ነው ሙጀለድ መጥቀሴ፡፡ እንደ አቶ አብዱልመጂድ ግንዛቤ ግን እነኚህ ዐሊሞች “ቅድሚያ ለተውሒድ” ሲሉ ሌላውን “ቅድሚያ ለሺርክ” ይላሉ ማለት ነው፡፡ እስኪ ይህን ግንዛቤ ታዘቡ፡፡ በዚህ መልኩ “ከዝሙት እንጠበቅ” የሚል ሁሉ ሌሎችን “ወደዝሙት ትጣራላችሁ” ማለቱ ነው፣ “አላህን እንፋራ” የሚለው ደግሞ ሌሎችን “አላህን አትፍሩ” እያለ ያስተምራል ማለት ነው፡፡ አልሐምዱ ሊላህ ዐላ ኒዕመቲል ዐቅል!!13. ((አክፍራቸውና ይለይልህ ባንድ ፊቱ ተክፊር አትሆኑም)) እያልክ ተሳልቀሃል፣ ጎትጉተሃል፡፡መልስ፡- እስኪ ይህን የፍንዳታ ደዕዋ ተመልከቱ!! “ከእውቀት በቂ እውቀት የለለው፣ ከብስለት ብስለት የለለው” ማለትህን ታስታውስ ይሆን? አሁን ይሄን እውቀት እንበለው ብስለት? ጭራሽ የሰፈር ጥል አደረግከው እኮ! ወይ ጉድ!! “የቤትሽን አመል እዚያው” አለ ባለታክሲው፡፡ ((እውቀት ሲጨምር አደብም አብሮ ያድጋል)) ብለህ ነበር እኮ? አሁን ይሄ አደብ ነው አቶ ዐብዱልመጂድ?14. ((የራሱንና የምርጡን ትውልድ ወጣትነት የሚያነፃፅር... አለ፡፡ አላህን አትፈራም ከወጣት ሰሐቦች ጋር እራስህን ስታነፃፅር)) ብለሃል፡፡መልስ፡- ደጋግመህ “አፍላ ወጣቶች” እያልክ በጭፍን ስትወነጅል እኮ ነው ወጣትነት በራሱ የሚያስተች አይደለም በሚል ወጣት ሰሐቦችን የዘረዘረልህ፡፡ አሁን ይቺ ከባድ ሂሳብ ሆና ነው ወይስ የዘመዶችህ በሽታ ተጋብቶብህ ነው? ደግሞስ አንተ “በጣት የሚቆጠሩ ናቸው” ፣ “ኢምንት ናቸው” ያልካቸው ሰለፍዮች ውስጥ አንተን የሚወልዱ ሽማግሌዎች አሉ፡፡ ምናለ ውሸትህንም ድፍረትህንም በልክ ብታደርገው? ጆሮም፣ አይንም፣ ልብም ሁሉም እንደሚያስጠይቁ የምታስገነዝበዋን አንቀፅ ስታነብ እራስህን አትርሳ እንጂ፡፡15. ((ሰላማዊ ሰልፍ ለመከልከል አንድ ማስረጃ የላቸውም)) ብለሃል፡፡መልስ፡- ማስረጃ እኮ የሚጠየቀው ከልካዩ አይደለም፡፡ እያነጠርክ ስትጎርርበት የነበርከው የኡሱል እውቀት የት ገባ?!! ደግሞ አታጭበርብር ሰልፍ የከለከሉት የሳውዲ ዓሊሞች ብቻ አይደሉም፡፡ እኔ ግን ከርካሽ ስድቦቹ በከፋ እየደነቀኝ ያለው ገደብ ያጣሁለት ውሸቱ ነው፡፡ ቆይ ግን “ዋሽ” እያለ ጥይት የደቀነብህ አል እንዴ? ኧረ “ሙስሊም አይዋሽም” የሚል ህፃን አዋቂው የማይስተው ሐዲሥ አለ አጎቴ?16. ((ኢስላም የማይቀበላቸውን ስሞች ከየት እንዳመጡት አይታወቅም)) ብለሃል፡፡መልስ፡- ኢኽዋን፣ ተብሊግ፣ ኸዋሪጅ፣... ከየት እንደመጡ የማታውቀው አንተ ነህ፣ በራስህ ምስክርነት፡፡ ወይ ደግሞ በጠራራ ፀሀይ እየካድክ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ሌላ ቦታ “ኢኽዋኑን ኢኽዋን ይላሉ፣ ተብሊጉን ተብሊግ ይላሉ” እያለ ማውራቱ ነው፡፡ ይሄ ማለት እኮ እየለጠፍን ሳይሆን በተጨባጭ አረጋግጠን ነው የምንለው ማለት ነው፡፡ ሳታስበው የሚወጣብህ ቃል አለ ልበል?17. ((ያለበለዚያ፣ ማንነታችሁን ከነስም ዝርዝራችሁ አወጣችኋለሁ፣ ከነአካውንታችሁ፣ እኔ እበቃችኋለሁ፣ በአፍሪካ ቲቪ አጋልጣችኋለሁ፣ ሁሉም ነገር በጃችን ነው፡፡...)) እያለ እየማለ ዝቶብናል፡፡መልስ፡- ወይኔ የት እንግባi ዓጂብ እኮ ነው!! እስከዛሬስ መች አርፋችሁ ነው እንዲህ የምትደነፋው? በየመስጂዱ ስትሰሩት የነበረው ይሄው አልነበር? “ተክፊር ናቸው፣ ጴንጤ ናቸው፣ አይሁድ ናቸው” ማለቱን እኮ ዚክር ካረጋችሁ አመታት ተቆጠሩ፡፡ “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” አይነት አካሄዳችሁ ተፅእኖ አሳድሮባቸው በጥርጣሬ የሚያዩን ብዙ እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ ይሄ ቀረርቶህ “እምቢ ካለ እያንዳንዱን እስከ ድንበር እየተከተልን ... ...ን ነው በጩቤ የምንወጋው” የሚለውን የመንግስቱ ሃ/ማርያምን ዛቻ አስታወሰኝ፡፡ ለምን አስታወስክ እንዳትለኝ እንጂ፡፡ ((አንዳንዴ መናገር ሳልፈልግ እንድናገር የሚያደርጉኝ፣..)) ይለናል፡፡ እስኪ በራስህ ቃል ልጠይቅህ፡፡ አንተ ማን ሆነህ ነው እንዲህ የምታቅራራው? እዚች ጋ አንድ ወንድሜ ለነዚህ ሰዎች የተናገራትን ልዋስማ፡፡ “እኛ እኮ ታኮ ብናረግላቸው እየዘለሉ አስቸገሩን!!” ሁሌ ቁልቁል ይወርዳሉ!! መጨረሻቸው የት እንደሆነ አናውቅም!! ለማንኛውም አደራህን ኒኩለር እንዳትተኩስብንi ምን ይታወቃል? “ሁሉም በእጃችን ነው” ስትል ጊዜ እኮ...፡፡ ከዚያ ውጭ እንኳን ያለው ብዙ አይጨንቀንም፡፡ አፍሪካ ቲቪንም፣ በእጃችሁ ያለውን ሁሉንም ተጠቅማችሁ፣ አይደለም የኢትዮጵያን ህዝብ፣ አለም ጋር ብታጣሉን አይሞቀን አይበርደን፡፡ ”አላህ ለኛ የፃፈለን እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ ይላል ጌታችን፡፡ “እወቅ! ህዝቦች በሙሉ ሊጎዱህ ቢሰበሰቡ አላህ በወሰነብህ ካልሆነ በቀር በምንም አይጎዱህም፡፡” “ያገኘህ ነገር የሚስትህ አልነበረም፡፡ የሳተህም ነገር የሚያገኝህ አልነበረም፡፡ ብእሮቹ ተነስተዋል፡፡ መዝገቦቹ ደርቀዋል፡፡” ይላሉ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡18. ጥቂት የዐብዱልመጂድን ውሸቶች ልቀንጭብላችሁማ፡፡ (((በሀገራችን ያሉ ሰለፍዮችን) በጣት የሚቆጠሩ፣ ኢምንት ናቸው))፣ ((ኢህአዴግን የሚቃወሙትን “የኢኽዋኒ ስብስብ ናቸው” ይላሉ))፣ ((የሙስሊሙ አንድነት ሲመጣ ጊዜ ቀኑ፣ ተንገበገቡ! ስም መለጠፍ ጀመሩ)) ((“የምናባቱ ወልይ ነው” እያሉ ደዕዋ ያደርጋሉ...፣ ((“አንድ ሁኑ” ሲባል “ሙስሊምና ሙሽሪክ አንድ አይሆንም” ይላሉ)) ((ከበስተጀርባቸው አይሁድ አለ)) ቱቱቱ...መልስ፡- እስኪ ይህን የውሸት ጋጋታ ተመልከቱ፡፡ “ካላፈርክ ያሻህን ስራ” ይላሉ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡ “ኧረ አላህን ፍራ!” ልልህ ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው? ይሄ ቋንቋ አይገባህ? “መሳጂድ ስታፍኑባቸው የነበሩ ሰዎች በማህበራዊ ድረ-ገፆች ስለተውሒድ ስላስተማሩ ቆጫችሁ፣ አቃጠላችሁ ለሺርክ አለቀሳችሁ!!” ብንል ደስ ይልሃልን? ከፊል እውነት ከመያዙም ጋር፡፡ መቼም አንተ ስትዘረጥጥ አፋቸውን ለጉመው ይቀመጣሉ ብለህ የምታስብ ቂል አትመስለኝም፣ እርግጠኛም ባልሆን፡፡ (እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጥፉ ሰዎች አይድኑም) የሚለውን አንቀፅ እኮ መግቢያህ ላይ ቀርተኸው ነበር፡፡ አንተ ጋ ትርጉሙ ሌላ ነው እንዴ? እንዳውም ያንተኑ አማርኛ ልጠቀምማ “ዐረብኛው ከሌለህ ለምን አማርኛውን አታነብም?” ችግሩ እዚያም ይከትልህ እንደሁ አላውቅም እንጂ፡፡ ሰውየው ውሸት የመተንፈስ ያክል የቀለለው ቅልል ያለ ጉድ ነው!! ቢላሂ ዐለይኩም አለመግባባት ቢኖርስ ከቻሉ “አይተናል” የሚሉትን ጥፋት ማጋለጥ እንጂ ውሸቱን ምን አመጣው? እድሜ ለኢኽዋን ውሸታም ዳዒዎችን አፈራልን፡፡ ገና ብዙ እንጠብቃለን፡፡ ሙዚቀኛ ሸይኾች አርቲስት ኸጢቦች!!! ኡስታዙ እንዲህ ከዋሸ ከተማሪዎቹ ምን ይጠበቃል? “አስተማሪ ከፈሳ ተማሪ ይቀዝናል” አሉ፡፡እኔ ግን አድንቄሃለሁ፡፡ በ45 ደቂቃ ብቻ ይህን ሁሉ ቅጥፈት፣ ዘለፋ፣ ልጠፋ፣ ዝርጠጣ ማውጣት ከቻልክ ወደ ፊት ጥሩ የስድብ መዝገበ-ቃላት የማውጣት ብቃቱ አለህ፡፡ ጅምሩንም በአፍሪካ ቲቪ እንጠብቃለን፡፡ ብራቮ ኢኽዋን!!ዐብዱልመጂድ! እኛም እንደናንተ ሰዎችን የሚያስደስት ርእስ እየመረጥን ማውራት፣ ሁሉን እንደስሜቱ ማስተናገድ፣ ብሎም ደጋፊና አድናቂ ማፍራት አላቃተንም፡፡ ወተላሂ እናንተ እንደምትገምቱትም እንደምታላዝኑትም ሙስሊሙን የመበታተን አባዜ የለብንም!! ገና ሰው እንዳይቀየመን በሚል ህዝብ የተነከረበትን ጥፋት ገሸሽ አድርገን ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ ማውራቱን ግን ሃላፊነት የጎደለው፣ ነገ ፀፀት ላይ የሚጥል፣ ከንቱ ሽወዳ እንደሆነ አምነን ትተነዋል፡፡ የሰውን ስሜት እየተከተሉ መፍሰስ የኢኽዋን ልዩ መታወቂያ ነው፡፡ ልክ አንተ በአፍሪካ ቲቪ ልታስፈራራ እንደሞከርከው በደሊል ሳይሆን በመሀይማን ቲፎዞ ሌሎችን ማስፈራራት የሙብተዲዖች ነባር መገለጫ ነው፡፡ አላማህ “አፍሪካ ቲቪን ተጠቅሜ መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ እከፍታለሁ” ነው፡፡ እስካሁንስ ምን ላይ ሆናችሁ? መድረክ ላይ ፊጥ ባልክ ቁጥር እንደማስቲካ ማኘክ ካማረክ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ፡፡ ከዚያ “አፍሪካ ቲቪን ሲቃወሙ ሰው ሁሉ ይነሳባቸዋል” ነው፡፡ የዋህ! እንዲህ አይነቱን ማስፈራሪያ ዋጋ ብንሰጠውማ ቀድመንም መንገዳችሁን መንገዳችን ባደረግን ነበር፡፡ ብታሾፉም ብትሳለቁም በማስረጃ ሳይሆን እንደፓርላማ በእጅ ብልጫ ነገሮችን ለሚለካ አሉባልተኛ ቅንጣት ታክል ጆሮ አንሰጠውም፡፡ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ነበር፡፡ ትንሽ ህሊናን ማሰራት እንጂ ሌላ አይጠይቅምና፡፡ ይሁን እንጂ ለወላእና ለበራእ ይህ ነው የሚባል ቦታ የሌለው፣ በሐቅና በባጢል መሀል የማያወላዳ መለያ ያላስቀመጠ፤ ለአላህ ብሎ የመውደድንና ለአላህ ብሎ የመጥላትን አርኪ ጣእም ያላጣጣመ፤ በሐቅ ሒሳብ መላው ሁለት እግራን ለማስደሰት የሚጥር፤... ከሰለፎቹ በላይ ዲን አዋቂ፣ ለኡማው ተቆርቋሪ መስሎ የሚቀርብ ጥራዝ-ነጠቅ ነጭና ጥቁር አይለይም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ህሊና ዲስኮ ሰዐት ማለት ነው- የተበላሸ ዲስኮ፡፡ የተበላሸ ዲስኮ አንዱን ቁጥር ከሌላው ሳይለይ ሁሉንም ስምንት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ቀኑ 88፡፡ሌቱ 88፡፡ ትላንትም 88፡፡ ዛሬም 88፡፡ ጧትም 88፡፡ ማታም 88፡፡ ክፉ ህመም!! ይህም እንደዚያው ነው፡፡ ሰባ ሁለቱም ጠማማ አንጃዎች ቢደረደሩ ከእውነተኛው ቡድን ለይቶ አያያቸውም፡፡ እሱ ዘንድ በኢስላም ስም እስከተንቀሳቀሱ ድረስ ሁሉም ለኢስላም እየሰሩ ነው፡፡ “አንዳንድ ችግሮች ቢኖሩም በውይይት ይፈታል” ይላችኋል፡፡ ሰለፎች “እከሌ ጀህሚ ነው”፣ “እከሌ ኻሪጂ ነው”፣ “እከሌ ቀደሪ ነው”፣ “እከሌ ጠማማ ነው”፣... ሲሉ የነበረውን ልዩነት በውይይት መፍታት አቅቷቸው ኖሯልን? እነ ዐብዱልመጂድ ግን ሙብተዲዖቹን ጥለው “እናንተ ብቻ ሱኒ ሌላው ሙብተዲዕ” እያሉ ይሳለቃሉ፡፡ ሁሉን ሱኒ ሊያደርግ በጠራራ ይጮሃል፡፡ ለኢኽዋኒው ይጮሃል፣ ለተብሊጉ ይጮሃል፣ ለሱፊው ይጮሃል፣ ለአሽዐሪው ይጮሃል፣ ለአልቃኢዳው (ለኸዋሪጁ) ይጮሃል፣ ለሺዐው ይጮሃል፣ ሰሐባን ለሚሳደበው ለሰይድ ቁጥብ ይጮሃል፣... ምን አለፋችሁ በሆነ መስመር ላይ ከተላተማቸው ሙብተዲዖች ውጭ ለሁሉም ይጮሃል፡፡ ልብ በሉ ጩኸቱ “በአንድነት” ስም ነው፡፡ “ሀሰት” እንደምትል እጠብቃለሁ፡፡ እንግዲያው እስኪ ይህን የምትፎክርበትን የምታስፈራራበትን አፍሪካ ቲቪ ተጠቅመህ ሰለ ኢኽዋን፣ ስለ ተብሊግ፣ ስለሱፊያህ፣ ስለ አሽዐርያህ፣ ተናግረሃልን? በኢስላም ስም በስሜት እየተነዳ የኢስላምን አንፀባራቂ ውበት ጥላሸት እየቀባ ስላለው አልቃኢዳስ አፍረጥርጠህ አውጥታሃልን? ነው እነሱ ጀግኖችህ ናቸው? ሽንጡን ገትሮ ስለሙዚቃ ስለሚሰብከው ሐሰን ታጁ በአፍሪካ ቲቪ አውርተሃልን? ይሄን ሁሉ ያደረገው ሰለፍዩ ቢሆን ስንት በቀባጠራችሁ ነበር?! አመት ብታወሩት አይሰለቻችሁም ነበር፡፡ ለተውሒድ ሲሆን ዶማ ናችሁ ለነገር ሲሆን ግን ሹል ናችሁ ከመርፌ የሾላችሁ፡፡ ከነዚህ ይልቅ የሰለፍዩ አደጋ ስለከፋ ነው በአፍሪካ ቲቪ የምትዝተው? በነ አልባኒ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ኢብኑ ባዝ ስም ባደባባይ ትነግዳላችሁ፡፡ ይሄው እነኚህ ዓሊሞች እነዚህን ጠማማ አንጃዎችና ድርጊቶቻቸውን አንዴ አይደለም ደግመው ደጋግመው አውግዘዋል፡፡ እናንተ ግን መንታ ፊት ሆናችሁ በስማቸው ተከልላችሁ አካሄዳቸውን ትወጋላችሁ፡፡ በመጨረሻም ወላሂ ከንቱ ውንጀላዎችህን እንደ አጥጋቢ ደሊል የሚመለከቱ መሳኪን ባይኖሩ ኖሮ ዝብርቅርቅ ያለ አማርኛህን፣ አሁንም አሁንም የምትደጋግመው ባዶ ዛቻህን፣ እጅ እጅ የሚል እንቶፈንቶህን ጨርሼ ለማዳመጥ፣ አልፎም መልስ ለመስጠት ትእግስቱም አልነበረኝ፡፡ “መልስ መስጠት አለብኝ” ብየ ስለተነሳሁ ብቻ ረጃጂምና አሰልቺ የሆኑ 45 ደቂቃዎችን ተሰቃይቻለሁ፡፡ ስጨርስ እንዴት እንዳንቀጠቀጠኝ ብነግርህ...፡፡ እንግዲህ አንተንም ዳዒያህ ብሎ አፉን ከፍቶ የሚያዳምጥ አለ ማለት ነው፡፡ “ቅል ግጥሙን አያጣም” አለ ያገሬ ሰው፡፡ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!