Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የእውቀት መጀመሪያ፤ ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ የለም፡፡



አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል ‹‹እወቅ፤ እነሆ ከአላህ በስተቀር በሃቅ የሚመለክ የለም››አላህን ልናውቀው የምንችለው፤ በመልካም ስምቹና ባህሪያቱ ነው፡፡ የአላህ ተውሂድ 1) ብቸኛው ፈጣሪ፤ ንጉስ፤ ተንከባካቢ፤ ገዳይ፤ ህያው አድራጊ እና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡ ይህ ተውሂድ አል-ሩቡብያ ይባላል፡፡ የአላህ ጌትነቱ፤ ወይንም የአላህ ተግባራት በመባል ይታወቃል፡፡2) ብቸኛ ተመላኪነቱ፤ ወይንም የፍጡራኖቹ ተግባራት በብቸኝነት ለእርሱ ብቻ መደረጋቸው፡፡ ለምሳሌ ዱዓ፤ ስግደት፤ እርድ፤ በአጠቃላይ አንድ ባሪያ ለአላህ የሚሰራው፤ ይህ ተውሂደል ኡሉሂያ (የአላህ ተመላኪነት) ይባላል፡፡3) የአላህ መልካም ስሞችና ባህሪያት፤ ይህ ተውሂደል አስማኡላሂ ወሲፋቲሂ ይባላል፡፡ከኡለማዎች አንዱ እንዲህ ብሎ ገጥሟል ጌታህን ሳታውቀው የምትገዛውእንደ ገለባ ነው፤ ፍሬ የማይወጣውአላህ ከሽርክ ይጠብቀን፡፡ አሚን፡፡ አላህ ሆይ! እውቀትን ጨምርልን፤ አንተውእንዳልከው፤ አንተን የሚፈሩህ ያወቁት ናቸው፤ አንተን መፍራትና እውቀትን ለግሰን፡፡ አሚን