Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል”

“ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል”ከሰሞኑ ኢኽዋኖችን የሚያቅበጠብጣቸው ነገር በዝቷል፡፡ አንዱ ሰለፍዮችንለመዝለፍ በፃፈው ሹፈት ማንነቱን አጋልጧል፡፡ ቆይማ መታዘብ ትችሉ ዘንድ አጠር ያለች ፅሁፉን ኮፒ ላድርግላችሁማ((‹‹ኢትዮ-ሂዝበ-ኑሮች››ቆይ ሌላ ተውሂድ አለ ልበል:: ማለቴ ከተማርነው ውጭ፤ እንግዲህ አል-ኢርሻድ፤ኪታቡ ተውሂድ (የሸይኸል ኢስላም ዓብደል-ወሃብም ይሁን የፈውዛንን) ቀርተናል፡፡ የሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን ከሽፉ ሹብሃትም ተምረናል ዐቂደቱል-ዋሲጢያንም እንዲሁ፡፡ ሸይኸል-ኢስላም አዩብ ደርባቸውና ተቀዳሚ ተማሪያቸው ሳዳት ከማል የከተቡት ታለም እኛ ሀቅን እንጂ አንወግንም፡፡ ከድፍንነትና ዝግነት የሚያወጣንን እንጂ ወደ መቀመቅ የሚከተንን አንሻም፡፡ ስርዓት አልባነታችሁን ህዝብ ማየቱ ጥሩ ነው፡፡ እንግዲህ ትንቀራቸው ውስጡ ስድብ፤ትችትና ማግለል የለበትም ንፁህ ናቸው፡፡…ሌላ ካለ ሳትሰድቡን አስተምሩን ወይም ጠቁሙን ‹‹ሸይኾቻችን፤ሙፍቲዎቻችን›› የተውሂድ ዓላማስ ሰዎችን አንድና እኩል ማድረግ አይደለምን??? ))
እንግዲህ በዚች አጭር ፓራግራፍ ውስጥ ምን ያህል እንደዘላበደ አብረን እንይማ
1. “ኢትዮ-ሒዝበ-ኑሮች” ብሎናል፡፡ ሒዝበንኑር ግብፅ ውስጥ የሚገኝ “ሰለፊ ነኝ” የሚል ፓርቲ ነው፡፡ እኛ እሱንም አንደግፍም፣ ሰለፊ እንደሆነም አናምንም፡፡ እናንተን ያበገናችሁ የሱ ሰለፊ መሆን አለመሆን ሳይሆን ሙርሲን ካስወገደው ወታደራዊ ስርኣት ሰነድ ላይ መፈረሙ ነው፡፡
2. ((‹‹ኢትዮ-ሂዝበ-ኑሮች››ቆይ ሌላ ተውሂድ አለ ልበል)) ብሎናል፡፡ ዘላቂ በሆነ መልኩ መቼ ተውሒድን አስተምራችሁ? “ቅድሚያ ለተውሒድ” ማለት ቅጥል ብግን አድርጓችሁ እያየን እኮ ነው፡፡
3. ((ኪታቡ ተውሂድ (የሸይኸል ኢስላም ዓብደል-ወሃብም)) ይላል ፀሀፊው፡፡ ኪታቡት-ተውሒድ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ ነው አጎቴ፡፡ የተማርከውን ኪታብ ፀሃፊም አታውቅም ማለት ነው፡፡ ነው ወይስ ሳትቀራ ነው መስለህ የቀረብከው?
4. ((የሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን ከሽፉ ሹብሃትም ተምረናል)) ይላል፡፡ ከሽፉሽ-ሹብሃት የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ እንጂ የኢብኑ ተይሚያህ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ምን አይነት ሰዎች ናቸው የሚያቀሯችሁ
5. ((ሸይኸል-ኢስላም አዩብ ደርባቸውና ተቀዳሚ ተማሪያቸው ሳዳት ከማል የከተቡት ታለም እኛ ሀቅን እንጂ አንወግንም፡፡)) ብለሃል፡፡ እውነት ከሐቅ የምትወግን ከሆነ አላህን ፍራ ሽሙጥህን አቁም፡፡ የማታውቀውን አታውራ፡፡
6. ((ስርዓት አልባነታችሁን ህዝብ ማየቱ ጥሩ ነው፡፡)) ብለሃል፡፡ እኔ ሲገባኝ ስርኣት አልባ ማለት በማያውቀው የሚያቦካ ነው፡፡ መድረኮችን ካልዘጋችሁ ደግሞ ህዝቡ እውነቱን ያያል፣ ጠብቁ፡፡ ላንተ ግን የምልህ ሳይመሽ እራስህን አትርፍ ነው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በማታውቀው እየዘላበድክ የኢኽዋኖችን ማንነት ስላሳየህ ግን ባላመሰግንህም ስለውለታህ “አላህ ሂዳያ” ይስጥህ እላለሁ፡፡
7. ((እንግዲህ ትንቀራቸው ውስጡ ስድብ፤ትችትና ማግለል የለበትም ንፁህ ናቸው፡፡)) ብለሃል፡፡ ታዲያ በዚችው አጭር ፅሁፍህ ውስጥ ስድብ አለ እኮ፡፡ ቢያንስ ((‹‹ሸይኾቻችን፤ሙፍቲዎቻችን››)) ማለትህ ሽሙጥ እንደሆነ ሳይገባህ ነው የፃፍከው ማለት ነው? በቃ እናንተ አንባቢው ሁሉ በናንተ ጭንቅላት የሚረዳ ሳያመዛዝን የምትሉትን የሚያስተጋባ ቅል እራስ ይመስላችኋል አይደል? ወላሂ እኔ በጣም ግርም የሚለኝ ኢኽዋኖች ሌሎችን ከሚተቹበት ነገር አንድ ቀን እንኳን ነፃ ሆነው አለማየቴ ነው፡፡ ግን አያችሁ አይደል ባንዲት ፓራግራፍ ምን ያህል እንደዘላበደ? ቀዳዳ ላለመክፈት ብዬ እንጂ ሌሎች ጥፋቶችንም መጨመር ይቻል ነበር፡፡
እንግዲህ በዚች አጭር ፓራግራፍ ውስጥ ምን ያህል እንደዘላበደ አብረን እንይማ1. “ኢትዮ-ሒዝበ-ኑሮች” ብሎናል፡፡ ሒዝበንኑር ግብፅ ውስጥ የሚገኝ “ሰለፊ ነኝ” የሚል ፓርቲ ነው፡፡ እኛ እሱንም አንደግፍም፣ ሰለፊ እንደሆነም አናምንም፡፡ እናንተን ያበገናችሁ የሱ ሰለፊ መሆን አለመሆን ሳይሆን ሙርሲን ካስወገደው ወታደራዊ ስርኣት ሰነድ ላይ መፈረሙ ነው፡፡2. ((‹‹ኢትዮ-ሂዝበ-ኑሮች››ቆይ ሌላ ተውሂድ አለ ልበል)) ብሎናል፡፡ ዘላቂ በሆነ መልኩ መቼ ተውሒድን አስተምራችሁ? “ቅድሚያ ለተውሒድ” ማለት ቅጥል ብግን አድርጓችሁ እያየን እኮ ነው፡፡3. ((ኪታቡ ተውሂድ (የሸይኸል ኢስላም ዓብደል-ወሃብም)) ይላል ፀሀፊው፡፡ ኪታቡት-ተውሒድ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ ነው አጎቴ፡፡ የተማርከውን ኪታብ ፀሃፊም አታውቅም ማለት ነው፡፡ ነው ወይስ ሳትቀራ ነው መስለህ የቀረብከው?4. ((የሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን ከሽፉ ሹብሃትም ተምረናል)) ይላል፡፡ ከሽፉሽ-ሹብሃት የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወሃብ እንጂ የኢብኑ ተይሚያህ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ምን አይነት ሰዎች ናቸው የሚያቀሯችሁ5. ((ሸይኸል-ኢስላም አዩብ ደርባቸውና ተቀዳሚ ተማሪያቸው ሳዳት ከማል የከተቡት ታለም እኛ ሀቅን እንጂ አንወግንም፡፡)) ብለሃል፡፡ እውነት ከሐቅ የምትወግን ከሆነ አላህን ፍራ ሽሙጥህን አቁም፡፡ የማታውቀውን አታውራ፡፡6. ((ስርዓት አልባነታችሁን ህዝብ ማየቱ ጥሩ ነው፡፡)) ብለሃል፡፡ እኔ ሲገባኝ ስርኣት አልባ ማለት በማያውቀው የሚያቦካ ነው፡፡ መድረኮችን ካልዘጋችሁ ደግሞ ህዝቡ እውነቱን ያያል፣ ጠብቁ፡፡ ላንተ ግን የምልህ ሳይመሽ እራስህን አትርፍ ነው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በማታውቀው እየዘላበድክ የኢኽዋኖችን ማንነት ስላሳየህ ግን ባላመሰግንህም ስለውለታህ “አላህ ሂዳያ” ይስጥህ እላለሁ፡፡7. ((እንግዲህ ትንቀራቸው ውስጡ ስድብ፤ትችትና ማግለል የለበትም ንፁህ ናቸው፡፡)) ብለሃል፡፡ ታዲያ በዚችው አጭር ፅሁፍህ ውስጥ ስድብ አለ እኮ፡፡ ቢያንስ ((‹‹ሸይኾቻችን፤ሙፍቲዎቻችን››)) ማለትህ ሽሙጥ እንደሆነ ሳይገባህ ነው የፃፍከው ማለት ነው? በቃ እናንተ አንባቢው ሁሉ በናንተ ጭንቅላት የሚረዳ ሳያመዛዝን የምትሉትን የሚያስተጋባ ቅል እራስ ይመስላችኋል አይደል? ወላሂ እኔ በጣም ግርም የሚለኝ ኢኽዋኖች ሌሎችን ከሚተቹበት ነገር አንድ ቀን እንኳን ነፃ ሆነው አለማየቴ ነው፡፡ ግን አያችሁ አይደል ባንዲት ፓራግራፍ ምን ያህል እንደዘላበደ? ቀዳዳ ላለመክፈት ብዬ እንጂ ሌሎች ጥፋቶችንም መጨመር ይቻል ነበር፡፡

Post a Comment

0 Comments