Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሀብት ፣ ጤና ፣ ልጅ ለሚለምኑ



ኢስላም የነብያት ሁሉ ሃይማኖት እንዲህ ሲል ይመክራቸዋል፡፡ኢብራሂም ኸሊል ከአላህ ውጭ ሲያመልኩ የነበሩ ህዝቦቹን እንዲህ ሲል መከረ
إِنَّ ٱلَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمْلِكُونَ لَكُمْ رِزْقًا فَٱبْتَغُوا۟ عِندَ ٱللَّهِ ٱلرِّزْقَ وَٱعْبُدُوهُ وَٱشْكُرُوا۟ لَهُۥٓ ۖ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَእነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፡፡ አምልኩትም (ተገዙትም)፡፡ ለእርሱም አመስግኑ፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ነው፡፡
وَسْـَٔلُوا۟ ٱللَّهَ مِن فَضْلِهِۦٓ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًاአላህንም ከችሮታው ለምኑት (የሁሉ ነገር ባለቤት እርሱ ብቻ ነው)፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
ዛሬ ስንቶች ናቸው ሙታንን ‹‹ልጅ ስጡን፤ ሪዝቅ ስጡን›› እያሉ የሚለምኑት አገራችን ላይ፡፡ ‹‹የጠመጠሙ ጠንቋዬች›› የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰርቶ መብላትን ነበር ያስተማሩት፤ ዛሬ ዛሬ አገራችን ላይ የተንሰራፋው ‹‹ዱዓ አድራጊ ነን፤ እኛ ያልነው ይሁን፤ ልጅ ላማራት የደግዬው ሸይኽ ልጅ ሰጧት፤ እና የመሳሰለውን›› እያሉ ሰርተው አይበሉ የሰው ገንዘብ እየበዘበዙ፤ ከዚህም አልፎ የሰው ሚስት ጋር እየተገናኙ፤ የሰው ገንዘብ እየዘረፉ፤ ከዚህ ሁሉ የከፋው ‹‹ወልይ›› ተብለው መጠራታቸው ገርሞ የሚገርም ነገር ነው፡፡
እስቲ ይህን ልብ እንበል እነዚህ ጠንቋዬች ቤት ሲሳይን ፈልጎ የሚሄደው ሰው እነርሱ (ጠንቋዬቹ) ሲሳይን ሊሰጡት ቢችሉ ኖሮ ለምንድን ነው እርሱ ‹‹ሙክት እና ሌላ ስጦታ›› ይዞላቸው የሚሄደው???ለራሱ ሪዝቅ የሌለው ጠንቋይ እንዴት ለሰው ይሰጣል???
የሚገርመው ሁሌ ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም ይባልለታል፡፡ መቼ ነው ለሰውስ አውቆ የሚያውቀውና??? የስንቱን ሰው ሚስት ተጫወቱበት፡፡አላህ ሆይ! እኛንም ሆነ ቤተሰቦቻችንን ከነዚህ ደጃሎች ጠብቀን፡፡