Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በእስልምና የሰው ስም አንስቶ መናገር ይቻላል ወይ?


በእስልምና የሰው ስም አንስቶ መናገር ይቻላል ወይ?*******************************************የሰው ስም ማንሳት የሚቻልባቸው ወቅቶች አሉ፡፡ ኢማመ ነወዊ (አላህ ይዘንላቸውና) የሚከተሉትን ስድስት ነጥቦች ‹‹ሪያዱ ሷሊሂን›› የተባለው ኪታባቸው ላይ ከቁርዐንና ከሀዲስ ጨምቀው እንዲህ በማለት አስቀምጠዋል፡፡ እወቅ ሀሜት ትክክለኛ ለሆነ አላማ ይቻላል፡፡ ከዚህ መንገድ ውጭ (ስም አንስቶ መናገር) ሌላ አማራጭ ከሌለ፤ እሱም በስድስት ምክንያት ነው፡፡
1. የተበደለ ሰው፡- የተበደለ ሰው ለሚመለከተው አካል፤ ለዳኛ ወይንም ለባለስልጣን፤ ለመሪ ሰውየው በሌለበት እገሌ በድሎኛል ቢል አይከለከልም፡፡
2. መጥፎን ነገር ለማስቆም (ለማገድ)፡- ለምሳሌ አከሌ መጥፎ ስራ እየወራ ነው፤ መጠጥ እየጠጣ ነው፤ እያጭበረበረ ነው ብለህ ለማስቆም ወይንም ለመምከር አቅም ላለው ሰው መናገር፡፡ ይህን ሲያደርግ ሰውየውን ለመመለስ ብቻ መሆን አለበት፡፡
3. ፈትዋ ለመጠየቅ፡- ለምሳሌ ለዳኛ አባቴ፤ ወንድሜ፤ ሚስቴ ወይንም እገሌ በድሎኛል፡፡ ለዚህ አካል ይሄ ይገባዋልን? ይበቃለታል ወይ? የሚሻለው ግን አባቴ፤ ወንድሜ ሳይሉ አንድ ሰው ነበር እንዲህ አደረገ ብሎ መጠየቅ ይሻላል፡፡
4. ሙስሊሞችን ከሸር ለማስጠንቀቅና ለመምከር፡- ለምሳሌ የሀዲስ ዘጋቢዎችና መስካሪዎችን ችግር ካለባቸው ችግር አለባቸው ማለት (ለምሳሌ የሚረሱ ከሆነ ይረሳሉ ብሎ መናገር)፤ እንዲያውም ይህ ዋጂብ ግዴታ ነው፡፡ ሌላ ምሳሌ፡- እገሌን ልጄን ልድረው ነበር፤ እገሌን ንግዴ ላይ ሸሪካ ላደርገው ነበር ምንትላለህ ተብሎ ከተጠየቀ፤ የተጠየቀው ሰው ሀቁን መናገር አለበት፡፡ ሌላው፡- አንድን ጡላበል ኢልም (የዲን ትምህርት የሚቀስም) ሙብተዲዕ (ቢድዐ የሚያራምድ ሰው) ጋር ወይንም ፋሲቅ ዘንድ ዲን ሊማር ሲመላለስ ካየሀው የሰውየውን ማንነት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ መስፈርቱም ምክርን አስቦ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰዎች የሚሳሳቱበት በመሆኑ ነው፤ ምክንያቱም ተናጋሪውን ምቀኝነት ሊያነሳሳው ይችላል፡፡ ሸይጧን ምክር ነው ብሎ ሊያመሳስልበት ይችላል፤ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ሌላው፡- ሰውየው ሀላፍትና ቦታ ይቀመጥና ሀላፍትናውን የማይወጣ ከሆነ ወይ ሀላፍትና ላይ የተቀመጠው ሰው ለቦታው ብቁ ካልሆነ ወይንም ፋሲቅ ከሆነ ለሚመለከተው አካል፤ አከሌ ተነስቶ አከሌ ቢቀመጥ ብሎ መናገር ይቻላል፡፡
5. ሰውየው ወንጀሉንና ቢድዐውን ግልፅ የሚያደርግ ከሆነ፡- በግልፅ እየሰሩ ያሉትን በግልፅ ለማህበረሰቡ ስም አንስቶ መጥቀስ
6. ለማስተዋወቅ፡- አንድ ሰው በሚታወቅበት ቅፅል ስም ማንሳት ለምሳሌ ሶስት ሙሀመዶች ቢኖኑ አንዱን ሙሀመድ የሚያነክሰው ተብሎ ቢጠራ፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው ለመለየት ብቻ እንጂ ለማነወር ከሆነ አይቻልም፡፡1. የተበደለ ሰው፡- የተበደለ ሰው ለሚመለከተው አካል፤ ለዳኛ ወይንም ለባለስልጣን፤ ለመሪ ሰውየው በሌለበት እገሌ በድሎኛል ቢል አይከለከልም፡፡2. መጥፎን ነገር ለማስቆም (ለማገድ)፡- ለምሳሌ አከሌ መጥፎ ስራ እየወራ ነው፤ መጠጥ እየጠጣ ነው፤ እያጭበረበረ ነው ብለህ ለማስቆም ወይንም ለመምከር አቅም ላለው ሰው መናገር፡፡ ይህን ሲያደርግ ሰውየውን ለመመለስ ብቻ መሆን አለበት፡፡3. ፈትዋ ለመጠየቅ፡- ለምሳሌ ለዳኛ አባቴ፤ ወንድሜ፤ ሚስቴ ወይንም እገሌ በድሎኛል፡፡ ለዚህ አካል ይሄ ይገባዋልን? ይበቃለታል ወይ? የሚሻለው ግን አባቴ፤ ወንድሜ ሳይሉ አንድ ሰው ነበር እንዲህ አደረገ ብሎ መጠየቅ ይሻላል፡፡4. ሙስሊሞችን ከሸር ለማስጠንቀቅና ለመምከር፡- ለምሳሌ የሀዲስ ዘጋቢዎችና መስካሪዎችን ችግር ካለባቸው ችግር አለባቸው ማለት (ለምሳሌ የሚረሱ ከሆነ ይረሳሉ ብሎ መናገር)፤ እንዲያውም ይህ ዋጂብ ግዴታ ነው፡፡ ሌላ ምሳሌ፡- እገሌን ልጄን ልድረው ነበር፤ እገሌን ንግዴ ላይ ሸሪካ ላደርገው ነበር ምንትላለህ ተብሎ ከተጠየቀ፤ የተጠየቀው ሰው ሀቁን መናገር አለበት፡፡ ሌላው፡- አንድን ጡላበል ኢልም (የዲን ትምህርት የሚቀስም) ሙብተዲዕ (ቢድዐ የሚያራምድ ሰው) ጋር ወይንም ፋሲቅ ዘንድ ዲን ሊማር ሲመላለስ ካየሀው የሰውየውን ማንነት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ መስፈርቱም ምክርን አስቦ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰዎች የሚሳሳቱበት በመሆኑ ነው፤ ምክንያቱም ተናጋሪውን ምቀኝነት ሊያነሳሳው ይችላል፡፡ ሸይጧን ምክር ነው ብሎ ሊያመሳስልበት ይችላል፤ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ሌላው፡- ሰውየው ሀላፍትና ቦታ ይቀመጥና ሀላፍትናውን የማይወጣ ከሆነ ወይ ሀላፍትና ላይ የተቀመጠው ሰው ለቦታው ብቁ ካልሆነ ወይንም ፋሲቅ ከሆነ ለሚመለከተው አካል፤ አከሌ ተነስቶ አከሌ ቢቀመጥ ብሎ መናገር ይቻላል፡፡5. ሰውየው ወንጀሉንና ቢድዐውን ግልፅ የሚያደርግ ከሆነ፡- በግልፅ እየሰሩ ያሉትን በግልፅ ለማህበረሰቡ ስም አንስቶ መጥቀስ6. ለማስተዋወቅ፡- አንድ ሰው በሚታወቅበት ቅፅል ስም ማንሳት ለምሳሌ ሶስት ሙሀመዶች ቢኖኑ አንዱን ሙሀመድ የሚያነክሰው ተብሎ ቢጠራ፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው ለመለየት ብቻ እንጂ ለማነወር ከሆነ አይቻልም፡፡