Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሀሰን ታጁ እና የጀዛ ፊልም ምርቃት!!!

አስተያየት ከሰጡት ሰዎች አንዷ ሴት እንዲህ ስትል ትናገራለች ‹‹ኢስላማዊ ስነ ጥበብ ላይ ከዚህ የበለጠ መሰራት እንደሚችል እና የሲኒማ ቤቶች መስፋፋት የበለጠ ደረጃ ለማድረስ…. የሚቻለውን ኢስላማዊ ማህበረሰብ ቢያበረክት እላለሁ ››
አላህ ይጠብቀን ‹‹የሲኒማ ቤቶች መስፋፋት የበለጠ ደረጃ ለማድረስ›› አለች፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡ መስጂዶች ባዶ ሆነው እስታዲዬም እና ሲኒማ ቤቶች እንዲሰሩ ይፈለጋል፡፡ ወዴት ይሆን እነዚህ ሰዎች የሚጠሩን???
ሀሰን ታጁ ጀዛ ፊልምን ግርማ ንዋይ ህንፃ ምርቃቱ ላይ ተገኝቶ እንዲህ ብሏል
‹‹እና ኢንሻአላህ ሃብት ያላቸው፤ ምሁራን መፃፍ የሚችሉ፤ መተወን የሚችሉ ሰዎች፤ ትልቅ ጉልበት ነው፤ ሺህ መስጂዶች፤ እኔ ልንገራችሁ፤ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኢብን ሂሻም፤ ሌላም ሌላም መፃሃፍ ተፅፏል፤ ረሂቅ ተፅፏል በአማርኛ፤ እንደ ‹ሪሳላ› የረሱልን ታሪክ ያስተዋወቀ የለም፡፡ የአንድ ሰዓት ፊልም ነው ግን ሁሉንም ታሪክ እንድናውቅ ያደረገ፡፡
ዩሱፍ ሺህ ጊዜ ቁርዓን ውስጥ ተፍሲር ውስጥ ቀርተነዋል፡፡ ዩሱፍ ፊልም ነው ግን እያንዳንዱ ቤት ውስጥ፤ የዩሱፍን ታሪክ ህይወት ዘርቶ እንድናውቅ የሚያደርገው፡፡ እና አርት 1000 ገፅ ከምንፅፍ 2 ሰዓት ፊልም በጣም ፓወር አለው በጣም ጉልበት አለው፡፡ እና ይህንንም ለመረዳት ስላበቃን፤ አላህ የተመሰገነ ይሁን እላለሁ፡፡ ተዋኒያኖቹን አመሰግናለሁ፤ በጣም በጣም አሪፍ ነው የሰሩት፡፡››

ሳይጨመር ሳይቀነስ ይህ የሀሰን ታጁ ንግግር ነው፡፡ የጀዛ ፊልምን ሲመርቅ ግርማ ንዋይ ህንፃ ላይ የተናገረው፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ለኡማው ‹‹ኮከብ እና ከዋክብት›› ሲባሉ የነበሩት፡፡

እውነት ፊልም ከኪታብ ይበልጣልን???

አይ የቢድአ አራማጆች የሆነ ሳምንት ያህል ‹‹ኮከብ›› ቢባሉም አላህ መልሶ ያዋርዳቸዋል፡፡
ከኢማን ስራ ሁሉ በላጭ ለአላህ ብሎ መውደድ ለአላህ ብሎ መጥላት ነው፡፡ እነ ሀሰን ታጁ ለኡማው እናስባለን በሚል ስም ኡማውን ወደ እንደዚህ አይነት የተሳሳተ መንገድ ነበር እየመሩት የነበረው፡፡ በጊዜው ያወቀ አውቋቸዋል፡፡
አሁንም ይህን ማስረጃ ካየ በኋላ እነዚህን ሰዎች መራቅ ነው፡፡

አላህ ይጀመርበት ያለው፤ ነብያት በጠቅላላ የጀመሩበትን ተውሂድ ቅድሚያ ያልሰጡ ሰዎች ብለውም በካሃዲያን ህዝቦች መንገድ ‹‹ፊልም›› ላይ ጥሬ የሚያደርጉ ሰዎች እውነት ለእኛ ያስቡልናል???
ነቃ በል የአላህ ባርያ! እራስህን ቤተሰብህን ከነዚህ መንገድ አሳች ሰዎች ጠብቅ፡፡
አላህም ይጠብቀን፤ ያሸበረቀን ቃል ይዘው መንገድ ከሚያስቱ ሰዎች፡፡
Sadat Kemal Abu Nuh