Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ጀመዐ ማለት ምን ማለት ነው››? ‹‹አንድነት›› ማለትስ ምን ማለት ነው?


===================
በዘመናችን ብዙ ሰዎች ‹‹ጀመዐ›› እና ‹‹አንድነት›› የሚለውን ቃል ያላግባቡ ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ ለምሳሌ ተውሂድ እና ሱና ትምህርት ሲሰጥ ‹‹አንድነታችን ተበታተነ›› የሚል አስተያየት ይሰነዝራሉ፡፡ ከተውሂድ እና ከሱና ውጭ አንድነት አለን??? አንድነት ወይንም ጀመዐ ምን ማለት እንደሆነ ታላቁ ሰሃባ አብደላህ ኢብን መስኡድ እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል፡፡
‹‹ጀመዐ ማለት ሀቅን የገጠመ (ሀቅ ላይ መሆን) ነው፡፡ብቻህን እንኳን ብትሆን››
ነብየላህ ኑህ (አለይሂ ሰላም) 950 ዳዕዋ አድርጎ ያመኑለት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ታድያ ኑህ ማድረስ ብቻ ነበር ግዴታው፡፡ከታላቁ ሰሃባ ንግግር እንደምንረዳው **) ሀቅ በሰው አይመዘንም፤ ሰዎች በሀቅ ይመዘናሉ እንጂ፡፡ **) ቁጥር የሃቅ መለኪያ አይደለም፡፡ **) አንድነት ከሀቅ ጋር የተያያዘ ነው ከቁጥር ጋር አይያያዝም፡፡ ነብያችን እንዲህ ይላሉ ‹‹የውመል ቂያማ አንድ ነብይ ብቻውን ይመጣል አሉ›› አላህ ሆይ! የእውነተኛውን አንድነት ስጠን፡፡