Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቢድዓ ምንድነው? የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና መከተል


የአላህ መልዕክተኛ  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙትን ትዕዛዝ እንድንቀበል፤ የከለከሉትን እንድንከለከል፤ እሳቸውን እንዳንፃረር አላህ በብዙ አንቀጾች አዞናል። እሳቸውን መታዘዛችን ለሳቸው ላለን ውዴታና ፍቅር መገለጫ መሆኑ ግልጽ ነው። 
﴿وَمَا آَتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانْتَهُوا وَاتَّقُوا اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ﴾ الحشر 7
“መልዕክተኛውም የሰጣትሁን (ማንኛውም ነገር) ያዙት ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡” አል ሐሽር 7
عن عبدالله بن مسعود أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال : ما من نبي بعثه الله في أمة قبلي إلا كان له من أمته حواريون وأصحاب يأخذون بسنته ويقتدون بأمره ثم إنها تخلف من بعدهم خلوف يقولون ما لا يفعلون ويفعلون ما لا يؤمرون فمن جاهدهم بيده فهو مؤمن وليس وراء ذلك من الإيمان حبة خردل) رواه مسلم
ሙስሊም ከአብዱላህ ኢብኑ መስዑድ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፤“ከህዝቦቹ መካከል ፈለጉን የሚከተሉና ትዕዛዙን የሚያከብሩ ረዳቶች “ሀዋርያት” እና ጓደኞች አድርጐለት እንጂ አላህ ከእኔ በስተፊት የትኛዉንም ነብይ አልላከም፤ ከዚያም ከነሱ በኃላ የማይሰሩትን የሚናገሩ ያልታዘዙትን የሚሰሩ ሰዎች ይተካሉ፤ እነዚህን በእጁ የታገላቸው ሙእሚን ነው፡፡ በአንደበቱም የታገላቸው ሙእሚን ነው፤ ከዚህ በኃላ ግን የሰናፍጭ ፍሬ ያህል እንኳ ኢማን የለውም፡፡” ሙስሊም ዘግበዉታል
ያልታዘዙትን የሚሰሩትን አስመልክቶ የታገላቸው ሙእሚን ነው ማለታቸው የእሳቸው ትዕዛዝ የሌለበት ነገር አደገኛ መሆኑን ያስረዳል፡፡ 
ቡኻሪና ሙስሊም ከሙእሚኖች እናት አዒሻ በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል “ትዕዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው፡፡”

እንደዚሁም “የእኔን ሱናና ከእኔ በኃላ የተመሩ የሆኑ ምትኮቼን ፈለግ ጠብቁ በሷም ተከተሉ አጥብቃችሁም ያዙ (በመንጋጋችሁ ነክሳችሁ ያዙ) ፈጠራ ነገሮችን ወየውላችሁ ማንኛውም ፈጠራ ቢድዓ ነው ማንኛውም ቢድዓ (ከሃይማኖት ላይ) የሚጨመር ፈጠራ ጥመት ነው ማንኛውም ጥመት የእሳት ነው፡፡” ብለዋል ከዒርባድ ኢብኑ ሳሪያህ ت የተዘገበ ሲሆን አህመድ (4/126-127) አቡዳውድ (46ዐ7) ሌሎችም ዘግበውታል፡፡

ማንኛውም የቢድዓ ተግባር ጥመት ነው
ነብያችን  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጀነት የሚያስገባን ማንኛውም ስራና ንግግር በተገቢው መልኩ አስተላልፈዋል ከመጥፎ ነገሮችም ሁሉ አስጠንቅቀዋል አስፈራርተዋል፡፡ ወደ አላህ የሚያቃርቡና የአላህን ውዴታ የሚያስገኙ የሆኑ መልካም ስራዎችን ሁሉ ያለምንንም ማጓደል ለህዝባቸው አስተምረዋል፡፡ ይህንን ትምህርት በመቀበል እና በመተግበር ባልደረቦቻቸው አዳዲስ ነገር በሃይማኖት ላይ ከመፍጠርና ከመጨመር ተብቃቅተዋል፡፡ ሱናን በመስራራት ከአዳዲስ ፈጠራ መታቀብ እንዳለብን አስተምረዋል፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ይላል “ተከተሉ አዲስ ነገር (በሃይማኖት ውስጥ) አታምጡ ሱና በቂያችሁ ነውና፡፡”

ሁዘይፍ ኢብኑል የማን እንዲህ ይላሉ “ማንኛውም የመልዕክተኛው ባልደረቦች ያልሰሩትን የኢባዳ ተግባር አትፈፅሙ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ለመጨረሻዎቹ ይህንን ክፍተት አልተውም፡፡” አቡዳውድና ሌሎችም ዘግበውታል፡፡
ዐብደላ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይላሉ “ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው ሰዎች መልካም አድርገው ቢያዩትም እንኳ”
የአላህ ዲን ሞልቷል ነብዩም ع መልዕክታቸውን አድርሰዋል ብሎ ያመነ ሰው በፍፁም ቢድዓ የሆነን ነገር ፈጥሮ ጥሩ ነው አይልም ፈጠራ እስከሆ ጥሩ ሊሆን አይችልም፡፡ እስቲ ይህንን ክስተት እንመልከት፡-
አንድ ቀን አቡሙሰል አሽዓሪ ወደ ዐብደላ ኢብኑ መስዑድ ቤት መጡና እንዲህ አሏቸው “አሁን መስጂድ ውስጥ የሚነቀፍ ነገር ተመለከትኩ” “ምንድነው?” አሉ ኢብኑ መስዑድ “በህይወት ካላችሁ ታዩታላችሁ ሰዎች መስጊድ ውስጥ ክብ ሰርተው ተቀምጠው ሰላትን ይጠባበቃሉ ከተሰበሰቡት አንዱ በእጅ ጠጠር ይዞ አንድ መቶ ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) አንድ መቶ ጊዜ ተስቢህ (ሱብሃነሏህ) አንድ መቶ ጊዜ ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) በሉ እያለ ያዛቸዋል እነሱም መቶ መቶ ጊዜ ይላሉ፡፡” ኢብኑ መስዑድም “ምን አልካቸው ታዲያ?” ብለው ጠየቋቸው “ምንም አላልኩም የአንቱን መልስ በመጠበቅ” አሉ ኢብኑ መስዑድም “ታዲያ ለምን ወንጀላቸውን እንዲቆጥሩ በመንገር በጎ ተግባራቸውን ግን አላህ ዘንድ እንደማያጡት ዋስ በሆንካቸው?” ከዚያም ወደ መስጊድ በመሄድ ምንድን ነው መስራት የያዛችሁት? እያሉ ገቡ ወደ ተሰበሰቡት ሰዎች በመሄድም ወንጀላችሁን ቁጠሩ ጥሩ ስራችሁን ግን አላህ ዘንድ እንደማታጡት ቃል እገባላችኋላሁ፡፡” የመሐሙድ ع ህዝቦች ሆይ ለመጥፋት ምን አስቸኮላችሁ የነብዩ  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰሃቦች ሞልተዋል የነብዩም ልብሶች ገና አላለቁም ዕቃቸውም እንኳ አልተሰበረም ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እናንተ ከነብዩ  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ የበለጠ የተመራችሁ ናችሁ ወይስ የጥመት በር ከፋቾች ናችሁ? አሉ “ የአብድራህማን አባት ሆይ እኛ እኮ ጥሩ ነገር አስበን እንጅ ለሌላ አይደለም” አሉ “ጥሩ እያሰቡ ግብ የማይመቱ ስንቶች ናቸዉ?! ነብዩ  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንደነገሩን “ሰዎች ይመጣሉ ቁርአን ይቀራሉ ግን ከጉሮሯቸው አይወርድም ምናልባት ብዙዎቹ ከናንተ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡” ከዚያም ጥለዋቸው ሄዱ (ዳረሚይና ሌሎችም ዘግበውታል)

ቡኻሪና ሙስሊም ከሙእሚኖች እናት አዒሻ በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ  (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል “ትዕዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው፡፡”
እንደዚሁም “የእኔን ሱናና ከእኔ በኃላ የተመሩ የሆኑ ምትኮቼን ፈለግ ጠብቁ በሷም ተከተሉ አጥብቃችሁም ያዙ (በመንጋጋችሁ ነክሳችሁ ያዙ) ፈጠራ ነገሮችን ወየውላችሁ ማንኛውም ፈጠራ ቢድዓ ነው ማማንኛው ቢድዓ (ከሃይማኖት ላይ) የሚጨመር ፈጠራ ጥመት ነው ማንኛውም ጥመት የእሳት ነው፡፡” ብለዋል ከዒርባድ ኢብኑ ሳሪያህ ت የተዘገበ ሲሆን አህመድ (4/126-127) አቡዳውድ (46ዐ7) ሌሎችም ዘግበውታል፡፡


﴿لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِمَنْ كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآَخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا ﴾ الأحزاب 21
“ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ፡፡” አል አህዛብ
﴿ فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَنْ تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ﴾ النور 63
“እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡” አል ኑር 63
አላህ መልዕክተኛውን የተፃረረ የእሱን እዕዛዝ ያልያዘን በሱናው ያልተብቃቃን ሰው መከራ ወይም አሳማሚ ቅጣት እንደሚያጋጥመው እንደገለፀው ሁሉ ረሱል ع የተላኩበት የእስልምና ሃይማኖት ሙሉ እንደሆነ ምንም ጭማሪ እንደማያስፈልገው በማኢዳ ሶስተኛ አያት ላይ አስፍሯል፡፡
﴿ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ﴾ المائدة 3
“ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ ፀጋዬንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ ለናንተም ኢስላምን በሃይማኖትነት ወደድኩ፡፡” አል ማኢዳህ 3
አላህ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ ብሏል መልዕክተኛውም የተላኩበትን ነገር ሁሉ በተገቢው መልኩ አስተላልፈዋል ይህ ሆኖ እያለ በሃይማኖት ውስጥ ጥሩ ወይም ያማረ ፈጠራ አለ ማለት ሃይማኖቱ አልሞላም ትንሽ ይጨመርበት ወይም ረሱል ለህዝባቸው ማስተላለፍ ያለባቸውን ነገር አላስተላለፉም ማለት ነው፡፡
ይህን የሚል ሰው ደግሞ ከእስልምና ርቋል ጌታውን አስቆጥቷል ራሱን ለጥፋት ዳርጓል መልካም ስራውን አውድሟል ግልፅ የሆኑ የቁርአን መልዕክቶችን ተቃርኗል፡፡ 
እውቁና ታላቁ ዓሊም ኢማሙ ማሊክ ኢብኑ አነስ የሚከተለውን ተናግረዋል “አንድ ሰው በኢስላም ውስጥ አዲስ ፈጠራን አምጥቶ የፈጠረው ፈጠራ መልካም መስሎ ከታየው ነብዩ ع መልዕክታቸውን አጉድለዋል ብሎ ሞግቷል ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏል 
﴿ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ﴾ المائدة 3
“ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ ፀጋዬንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ ለናንተም ኢስላምን በሃይማኖትነት ወደድኩ፡፡” አል ማኢዳህ 3 ያኔ ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን አይሆንም፡፡”
የነብዩ ምርጥ ባልደረቦች (ሰሃቦች) እና የእነሱ ተተኪዎች (ታቢዕዬች) ሃይማኖት ሙሉ መሆኑን ተረድተው ነብያዊ ፈለግን በመከተላቸው ዲናቸውን ከአዳዲስ ልጣፊዎች ጠብቀው በማስተላለፍ አደራቸውን በሚገባ ተወጥተዋል፡፡ ነገር ግን ከነዚህ ምርጥ ትውልዶች ጊዜ በራቀ ቁጥር ሰዎች ስለዲናቸው ያላቸው ግንዛቤ እየተዳከመ በመምጣቱ ብዙ አዳዲስ የቢድዓ ተግባራትን መፈፀም ጀምረዋል፡፡ አላህ ያላዘዘውን መልዕክተኛው ያልተገበሩትንና መደንገጉን ያልፈቀዱትን ነገር መደንገግ ይዘዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
﴿ أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ ﴾ الشورى 21
“ከሃይማኖት አላህ በርሱ ያልፈቀደውን ለነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለነርሱ አልሏቸውን?” አል ሹራ 21

ነብያችን የተሰጣቸውን መልዕክት በሚገባ አድርሰዋል አማናቸውንም ተወጥተዋል
የተከበሩት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ ለህዝቦቹ የሚያውቀውን መልካም ነገር መጠቆም እና ከሚያውቅላቸው ክፉ ነገር ማስጠንቀቅ ግዴታ ቢሆንበት እንጂ ከእኔ በፊት (አንድም) ነብይ አልተላከም›› ሙስሊም በቁጥር 1844 ከአብዱላህ ኢብኑ ዓምር ዘግበውታል
ወደ አላህ ውዴታ የሚያቃርቡንን የአምልኮ ተግባራት በሙሉ በጌታቸው መመሪያ መሰረት ቅንጣት ሳያጓድሉ በአግባቡ አስተላልፈዋል፡፡ አማናቸውንም ተወጥተዋል፡፡ ይህንን እውነታ በመሠናበቻ ሀጃቸው ላይ ሠሀቦችን አስመስክረዋቸዋል እኛም ምሉዕ በሆነ መልኩ የአላህን መልዕክት እንዳደረሱ ሀላፊነታቸውንም እንደተወጡ እንመሰክራለን፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በእርሳቸው ላይ ይሁን፡፡ 
አላህ ይህንን ዲን ምሉዕ አድርጎታል ጭማሪን አይቀበልም
እውቁና ታላቁ ዓሊም አል-ኢማም ማሊክ ኢብኑ አነስ የሚከተለውን ተናግረዋል “አንድ ሠው በኢሳለም ውስጥ አዲስ ፈጠራን አምጥቶ የፈጠረው መልካም መስሎ ከታየው ነብዩ መልዕክታቸውን አጉድለዋል ብሎ ጠርጥሯል ምክንያቱም አላህ እንዲህ ይላል ‹‹ዛሬ ሀይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ ፀጋዬንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ ለእናንተም ኢስላምን በሀይማኖትነት ወደድኩ›› አል ማዒዳህ ቁጥር 5 ያኔ ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን አይሆንም)
ይህ ኢማም ማሊክ የጠቀሱት አንቀፅ የወረደው በ 10ኛው አመተ ሒጅራ በዙልሒጃ ወር በጁምዓ እለት ነብዩ ዓረፋ በቆሙበት ነው፡፡ የመሠናበቻ ሐጅ (ሐጀቱል ወዳዕ) ማለት ነው አል ቡኻሪ ቁጥር 45 እንዲሁም ሙስሊም ቁጥር 30/73 ይመልከቱ
አንዳንድ ሰሀቦች ከዚህ አንቀፅ በኋላ የቁርዓን አንቀፅ አልወረደም ይላሉ፡፡ ቢወርድም በጣም ጥቂት ነው የረሱል ምርጥ ባልደረቦች (ሰሀቦች) እና የእነሱ ተተኪዎች (ታቢዕዮች) ዲን ምሉዕ መሆኑን ተረድተው ነብያዊ ፈለግን በመከተላቸው ዲናቸውን ከአዳዲስ ልጣፊዎች ጠብቀው በማስተላለፍ አደራቸውን በሚገባ ተወጥተዋል፡፡ ከዚህ ዑማህ ምርጥ አበው ትውልዶች ጊዜ በራቀ ቁጥር ሰዎች ሰወስለዲናቸው ያላቸው ግንዛቤ እየተዳከመ በመምጣቱ ብዙ አዳዲስ የቢድዓ ተግባሮች መፈፀም ጀመሩ፡፡
አላህ ያላዘዘውን መልዕክተኛው ያልተገበሩትንና መደንገጉን ያልፈቀዱትን ነገር በአምልኮ ተግባርነት መደንገግ ለማንም የምይፈቀድ ግልፅ ጥመት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
﴿ أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ ﴾ الشورى 21
‹‹ አላህ ከሀይማኖች በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ (ከአላህ ጋር) ተጋሪች አሏቸውን?! ›› አል ሹራ 21
ረሱልም እንዲህ ብለዋል ‹‹በዚህ በጉዳያችን (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ (ስራው) ተመላሽ ነው፡፡›› አል ቡኻሪይ 2550 እንዲሁም ሙስሊም በቁጥር 1718 ከአዒሻ ዘግበውታል
ነብያችን በንግግራቸው መግቢያ ላይ የሚከተለውን ይሉ እንደነበር ተዘግቧል ‹‹ከንግግር ሁሉ የተሻለው የአላህ መፅሀፍ ነው ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) መመሪያ ነው፡፡ የነገሮች ሁሉ መጥፎ አዳዲስ ነገሮች ናቸው፡፡ ሁሉም የፈጠራ ተግባር ጥመት ነው›› ሙስሊም በቁጥር 867 ከጃቢ ኢብኑ አብዲሎህ ዘግበውታል
ይህንኑ ጉዳይ አደራ ብለው ነበር ወደ አኼራ ያለፉት፡፡ እንዲህም አሉ ‹‹ የእኔንና ቅን የተመሩ የሆኑ ምትኮቼን (ኹለፋእ) ፈለግ በመከተል ላይ አደራችሁን (ይህችን ፈለጌን) አጥብቃችሁ ያዟት! አደራችሁን! አዳዲስ ነገሮችን ተጠንቀቁ አዲስ ነገር ሁሉ ፈጠራ ነው ሁሉም ፈጠራ ደግሞ ጥመት ነው›› አህመድ (4/126-127) አቡዳውድ (4607) ቲርሚዚይ (2676) ኢብኑ ማጀህ (44) ከአርባድ ኢብኑ ማሪያህ የዘገቡት ሀዲስ
ሁሉም የቢድዓ ተግባር ጥመት ነው
ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፉልን ትዕዛዞች በመቀበል እና ሱናቸውን በመተግበር ልንብቃቃ ይገባል፡፡ ኢብኑ መስዑድ እንዳሉት (ተከተሉ! አዲስ ነገር አታምጡ ሱንና በቂያችሁ ነውና) ሁዘይፋ ኢብኑ የማን እንዲህ ይላሉ (ማንኛውም የመልዕክተኛው ሰሀቦች ባልሰሩት የኢባዳ ተግባር አምልኮን አትፈፅሙ! የመጀመሪያዎቹ ለመጨረሻዎቹ ይህንን ክፍተት አልተውም) አቡ ዳውድ እና ሌሎችም ዘግበውታል
አላህ የሚያቃርቡን እና የእርሱን ውዴታ የሚያስገኙልን የመልካም ስራ በሮች ብዙ ከመሆናቸው ጋር አዳዲስ የፅድቅ መንገዶችን ለመቅደድ መሯሯጥ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው አላህ ከደነገጋቸው እና መልዕክተኛው ከወደዷቸው የመልካም ስራ በሮች ምን ያህሉን አንኳክቻለሁ ብሎ ራሱን ቢጠይቅ ጉድለቱን ያስተውላል፡፡ 
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው ሰዎች መልካም አድርገው ቢያዩት እንኳ!›› ኢብኑ በጣህ አለለካኢይና ሌሎችም በትክክለኛ ሰነድ ዘግበውታል
የአላህ ዲን ሞልቷል ነብዩም መልዕክታቸውን አድርሰዋል ብሎ ያመነ ሰው በፍፁም ቢድዓ የሆነን ነገር ፈጥሮ ጥሩ ነው አይልም! ፈጠራ እስከሆነ ጥሩ ሊሆን አይችልም፡፡ እስቲ ይህንን ክስተት እናስተዉል፡፡
አንድ ቀን አቡ ሙሳአል-አሽዓሪ ወደ ዓብዱላህ ኢብኑ መስኡድ ቤት ይመጡና እንዲህ ይለዋቸዋል፡- ‹አሁን መስጂድ ውስጥ የሚነቀፍ ነገር ተመለከትኩ።› ‹ምንድነው›? አሉ ኢብኑ መስዑድ።‹በሕይወት ካለ ህታየዋለህ! ሰዎች መስጊድ ውስጥ ሆነው ክብ ሰርተው ተቀምጠው ሶላትን ይጠባበቃሉ፤ ከተሰበሰቡት አንዱ በእጁ ጠጠር ይዞ፡-አንድ መቶ ጊዜ ተክቢራ አድርጉ፣ አንድ መቶ ተስቢህ፣ አንድ መቶ ታህሊል እያለ ያዝዛቸዋል።እነሱም መቶ፣ መቶ ጊዜ ይላሉ።› ኢብኑ መስዑድም ‹ምን አልካቸው ታዲያ?› ብለዉ ይጠይቋቸዋል።‹ምንም አላልኩም፣ የአንተን አስተያየት በመጠበቅ!› ኢብኑ ‹ታዲያ ለምን ወንጀላቸውን እንዲቆጥሩ በመንገር፣ በጎ ተግባራቸውን መስዑድም ግን አላህ ዘንድ እንደማያጡት ዋስ አትሆናቸውም?› ከዚያም ወደ መስጊድ ‹ምንድነው መሥራት የያዛችሁት? ገቡ። ወደተሰበሰቡት ሰዎች በመምጣትም ወንጀላችሁን ቁጠሩ፣ ጥሩ ሥራችሁን ግን አላህ ዘንድ እንደማታጡት ቃል እገባላችኋለሁ።የሙሀመድ (ሠ.ዐ.ወ) ኡመቶች! ለመጥፋት ምን አስቸኮላችሁ።የነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) ሰሀቦች ሞልተዋል፤ የነቢዩም (ሠ.ዐ.ወ) ልብስ (ገና) አላለቀም፤ ዕቃቸው እነኳ አልተሰበረም።ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እናንተ ከነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) መንገድ የበለጠ የተመራችሁ ናችሁ ወይም የጥመት በር ከፋች ናችሁ?!› ‹አቡ አብዱራህማን እኛ እኮ ጥሩ አስበን እንጂ ሌላ አሏቸው። ሰዎቹም አይደለም›‹ጥሩ እያሰቡ ግብ የማይመቱ ስንቶች አሉ?! ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) አሉ። እንደነገሩን፡- (ሰዎች ይመጣሉ፣ ቁርዓን ይቀራሉ፤ ግን ከጉሮሯቸው አይወርድም!) ምናልባት ብዙዎቹ ከእናንተ ሳይሆኑ አይቀሩም።…› ከዚያ ጥለዋቸው ሄዱ። (አድዳሪሚይና ሌሎች ዘግበውታል)



ልብ ያለው ልብ ይበል
ከላይ እንደተብራራው፤ ነብያችንን ع መውደድ ግዴታ ነው። እውነተኛ ውዴታ ግን በተግባር ነው የሚገለጸው፡፡ ማንኛውም የቢድዓ ተግባር ጥመት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ታዲያ ይህ እንዲህ ከሆኑ ነብያችን የተወለዱበትን ቀንን ማክበር የውዴታ መግለጫ ነውን? ሱና ነው ወይስ ቢድዓ? ከእምነት ነው ወይስ ከባህል? በሚቀጥለው ርዕሳችን የምናየው ነጥብ ነው፡፡
ትክክለኛ የውዴታ መግለጫ ነውን? ውዴታ ነው ወይስ ጥላቻ?
መውሊድ የሚያከብሩ ሰዎች መውሊድን የሚያከብሩት ነብዩ ع ወደው ነው ወይስ ጠልተው ? አላህን መገዛት ነው ወይስ አላህን ማመፅ? ነብዩን ወደው አላህን እየተገዙ ከሆነ ታዘው ነው ወይስ ሳይታዘዙ? ታዘው ከሆነ ይህን ትዕዛዝ ነብያችን ع ለህዝባቸው አብራርተውታል ወይስ አላብራሩትም? አብራርተውታል ከሆነ የት አለ? ከቁርአን ከሀዲስ? ደብቀውታል አላብራሩትም ከሆነ ነብዩን ع መልዕክታቸውን አላደረሱም ማለት ነው ይህ ደግሞ የማያጠራጥር ክህደት ነው፡፡
﴿ يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنْزِلَ إِلَيْكَ مِنْ رَبِّكَ وَإِنْ لَمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ وَاللَّهُ يَعْصِمُكَ مِنَ النَّاسِ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ ﴾ المائدة 67
“አንተ መልዕክተኛ ሆይ ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ ባትሰራም መልዕክቱን አላደረስክም አላህም ከሰዎች ይጠብቅሃል አላህም ከሃዲዎችን ሕዝቦችን አያቀናም፡፡” አል ማኢዳህ 67 
ኢባዳ ላይ አላህና ረሱል ከደነገጉት ውጭ ምንም አይነት ድንጋጌ የለም ማንም ሰው በዘፈቀደ እንደፈለገ ሊወስንና ሊደነግግ አይችልም ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፡-
﴿ أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ وَلَوْلَا كَلِمَةُ الْفَصْلِ لَقُضِيَ بَيْنَهُمْ وَإِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ ﴾ الشورى 21
“ከሃይማኖት አላህ በርሱ ያልፈቀደውን ለነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለነርሱ አሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኑሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር በደለኞችም ለነርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አላቸው፡፡” አል ሹራ 21