Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከረመዷን ምን ተማርን

 ከረመዷን ምን ተማርን

❓
📮የወራቶች ሁሉ አለቃ የሆነው ረመዷን ሙእሚኖችን ብዙ ቁም ነገሮችን ያስተምራል ከነዚህም በጥቂቱ:-
①ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉ ነገር (ሰላት፣ ሰደቃ፣ ቁርኣን፣ ትዕግስት/መቻልና በጎ መሆን ወዘተ) ቀላል እንደሆነ፣
② ምንም ሳናውቀው ረመዷን መጥቶ ሲሄድ ማየታችን የዱኒያ ህይወትም አጭርና እድሜያችን ሳናውቀው እንደሚኮበልል፣
③አንድ ሀገር ብሎም የተለያዩ የዓለማችን ሀገራት ላይ ያሉ ሙስሊሞች በተመሳሳይ ሰዓት ጾም እየጀመሩ በተመሳሳይ ሰዓት ጾምን መፍታታቸው እውነተኛ አንድነት ያለውና ሊገኝ የሚችለው ሐቅን(ቁርኣንና ሐዲሥን )በመከተል ብቻ እንደሆነ፣
④ስለደጋግ ቀደምቶች በብዛት እንሰማውና እንገረምበት የነበረው 30ውን ጅዝእ ቁርኣን በ7፣ በ3 እና በ1 ቀን ማኽተም ቀላልና ባለንበት ዘመንም የሚቻል መሆኑን
⑤የተለያዩ የባዕድና ጎጂ ሱሶች ባሪያ የሆኑ ሰዎች ረመዷን ላይ ቀኑን ሙሉ ከነዚህ ነገሮች ታቅበው እንደሚውሉት ሁሉ ካመኑበትና አቅላቸውን (አዕምሯቸውን) ከተጠቀሙ ከረመዷን ውጪም መተውና መታቀብ እንደሚችሉ፣
⑥ ብዙ ሰዎች የሸሪዓን እውቀት ችላ የሚሉት የዲኑን ህግጋት ከመተግበር ወደ ኋላ በማለት እንደሆነና ሰዎች ወደ ዲናቸው ሲመለሱ ህግጋቱን ለማወቅ እንደሚጥሩ ረመዷን ላይ የፈትዋ ጠያቂዎች መብዛት በግልጽ ያሳያል
⑦ ረመዷን ላይ የብዙ ሰዎች ስነ-ምግባር እንዲስተካከል ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል አንዱ ከምግብ በመራቃቸው ሆዳቸው ባዶ ሆኖ ረኀብና ድካም ስለሚሰማቸው በመሆኑ ከረመዷን ውጪም ምግብ መቀነስና አንዳንዴም መራብ ጥጋበኝነትን በማስቀረት ጸባይን ሊያስተካክል እንደሚችልና
⑧ ወደ ኣኺራ ለሚደረግ ጉዞ ዋና አስፈላጊ መሳሪያ የፈረጠሙ አካላት ሳይሆኑ ንጹህና ንቁ ልብ እንድሆነ ብዙ ወጣቶች ተራዊሕ መስገድ አቃተን እያሉ አዛውንቶች እስከመጨረሻው ሲሰግዱ በማየታችን ይህን መረዳት እንደሚቻልና ወዘተና ሌሎችንም እውነታዎችንና ቁምነገሮችን ረመዷን አስተምሮናል
እኔ ባጭሩ እነዚህን ለመጥቀስ ሞክሬያለሁ ሌሎች በርካታ የሚጠቀሱ ነገሮችም ይኖራሉ እናንተው አስቧቸው
✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
ሸዋል 6/1439 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ

Post a Comment

0 Comments