Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኮሮና(የወረርሽኝ በሽታ) እና ዐቂዳ

ኮሮና(የወረርሽኝ በሽታ) እና ዐቂዳ

▪️ማንኛውም በሽታ የሚመጣውም ይሁን የሚወገደው በአላህ ፍቃድና ኀይል ነው።ማስክ በማድረግ፣ ከቤት ባለመውጣትና ወዘተ በመሰል የሰው ብልሃቶች ብቻ ከበሽታ እድናለሁ፣ እነዚህ ነገሮችም በራሳቸው ብቻ የመጠበቅና የማዳን ኀይልና አቅም አላቸው ብሎ ማመንና አላህን ረስቶ በነሱ መመካት ሺርክ (በአላህ ማጋራት) ነው።

▪️በአንጻሩ ደግሞ ሰበብ ማድረስና በአላህ ፍቃድ ይጠቅማሉ የሚባሉ ነገሮችን መጠቀምን በመተው በተሳሳተ ተወኩል እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ደግሞ አላህን ማመጽና የሸሪዓ ትዕዛዝን መጣስ ነው።

▫️ዲናችን "ጠባቂ አላህ ነው" ከማለቱም ጋር "ተጠንቀቁ"ም ብሏል።ሰበብ ማድረስ በጭራሽ ከተወኩል ጋር አይጋጭም! አላህ በእርሱ እንድንመካም ሰበብ እንድናደርስም አዞናል።

▪️አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ መሄድ አላዋቂነት ነውና ዲናችንን በሚገባ እንረዳ! ስሜትና ግምትን እንተው!

አላህ ለሁላችንም ሙሉ ዓፊያና ጠቃሚ  
    እውቀት ያድለን
ኣሚን

✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
4/8/1440ዓሂ

Post a Comment

0 Comments