Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ትዕግስትን ከህፃን ተማርኩ!አስተማሪ ታሪክ!

ትዕግስትን ከህፃን ተማርኩ!
አስተማሪ ታሪክ!

ታላቁ ዓሊም ፉደይል  ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ ፦

"ሰብርን (ትዕግስትን) ከህፃን ልጅ ተማርኩ፦

ከእለታት አንድ ቀን ወደ መስጂድ እየተጓዝኩ ሳለሁ አንዲት እናት  ቤቷ ውስጥ ሆኗ ልጇን እየገረፈች ሳለ እያለቀሰ ከእጇ አምልጦ በር ከፍቶ አመለጠ  እርሷም በሩን ስተዘጋ ተመለከትኩ።

ከመስጂድም ስመለስ ሕፃኑ ቤቱ ደጃፍ ላይ ቆሞ ለአፍታ ካለቀሰ በኋላ እናቱን እዝነት እንድታደርግለት ደጃፉ ላይ ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ። 

እናትም የእናትነት አንጀት አላስችል ብሏት በሩን ከፍታ ቤት አስገባችው።"

ይህን ትእይንት ፉደይል ሲመለከቱ ፂማቸው በእንባ እስኪርስ አለቀሱ።

ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦

"ሱብሓነላህ! የሰው ልጆች አላህ ደጃፍ እንዲዚህ ህፃን ቢታገሱ አላህ በሩን ይከፍትላቸው ነበር!!"

አቡደርዳእ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ ፦

"ዱዓ ላይ በርቱ! እነሆ በተደጋጋሚ በር ያንኳኳ በሩ ሊከፈትለት ይቀርባል።"

📚(ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባ 6/22)

     ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ      

Post a Comment

0 Comments