Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተውሒድ ፍሬዎችና ትሩፋቶች



ثمرات التوحيد وفوائده
(የተውሒድ ፍሬዎችና ትሩፋቶች)
ተውሒድ ታላላቅ ፍሬዎችና ትሩፋቶች አሉት፡፡
ከእነዚህ ፍሬዎችና ትሩፋቶች መካከል የሚከተሉትን ለአብነት መጥቀስ እንወዳለን፡-

1- በተውሒድ መልካም ጸጋዎች ይገኛሉ፡፡ የዱንያና የአኼራ ጭንቀቶች ይወገዳሉ፡፡
2- ተውሒድ የተሟላ ጸጥታና መመራትን ያጎናጽፋል፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
"الذين ءامنوا ولم يلبسوا إيمنهم بظلم أولئك لهم الأمن وهم مهتدون"  (الأنعام: 86)
“እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡ እነሱም የተመሩ ናቸው፡፡”  (አል’አንዓም፡ 86)
3- ተውሒድ ከአላህ ዘንድ የተሟላ  አጅርን ወይም ምንዳን ያስገኛል፡፡
4- በተውሒድ ምክንያት ወንጀሎች ይሰረዛሉ፡፡
ዓነስ ከረሱል - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ይዘው ባስተላለፉት ሐዲሰል ቁድስ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
"يا ابن آدم إنك لو أتيتني بقراب الأرض خطايا ثم لقيتني لا تشرك بي شيئا لأتيتك بقرابها مغفرة" رواه الترمذي
“የአደም ልጅ ሆይ! በእኔ ምንም ሳታጋራ መሬት ሙሉ የሚቃረብ ወንጀል ሰርተህ ብትመጣ በእርሷው ሙሉ ምህረትን እሰጥሃለሁ፡፡”
(ሐዲሱን ቲርሚዝይ ዘግበውታል፡፡)
5- ተውሒድ ጀነትን ያጎናጽፋል፡፡
فعن عبادة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "من شهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له ، وأن محمدا عبده ورسوله ، وأن عيسى عبد الله ورسوله وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ، وأن الجنة حق ، وأن النار حق ، أدخله الله الجنة على ما كان من العمل"  متفق عليه 

ዑባዳ ባስተላለፈው ሐዲስ ረሱል - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ሙሀመድም የአላህ አገልጋይና መልክተኛ ናቸው  ዒሳ ደግሞ ከእርሱ የሆነ አንዱ መንፈስ ወደመሬም ባስተላለፋት ቃሉ (የተገኘ) ነው ብሎ የመሰከረ  ጀነት ሀቅ ነው እሳትም ሀቅ ነው ብሎ የመሰከረ ስራው ይብዛም ይነስም አላህ ጀነትን ያስገባዋል፡፡”
(ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)
وفي الحديث جابر بن عبد الله رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم
أنه قال : "من مات لا يشرك بالله شيئا دخل الجنة"  رواه مسلم


ጃቢር ብን ዓብዲላህ ባስተላለፈው ሐዲስ የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“በአላህ ሳያጋራ የሞተ ጀነት ገባ፡፡”
(ሐዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)
6- ተውሒድ እሳትን ይከላከላል፡፡
ففي حديث عتبان رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم : ".... فإن الله حرم على النار من قال : لا إله إلا الله يبتغي بذلك وجه الله" متفق عليه

ዒትባን ባስተላለፉት ሐዲስ የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“የአላህን ፊት ፈልጎ ላኢላሃ ኢለሏህ የሚለውን ቃል በተናገረ ሰው ላይ አላህ እሳትን እርም አድርጓል፡፡”
(ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስለም ዘግበውታል፡፡)
7- የሰናፍጭ ፍሬ ያክል ኢማን በልቦናው የተገኘ ሰው ከዘላለማዊ የእሳት ቅጣት ይድናል፡፡
8- የአላህን ውዴታና ምንዳ የረሱልን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ምልጃ ለማግኘት ዕድለኛ የሚሆኑት የተውሒድ ሰዎች ናቸው፡፡
"وأسعد الناس بشفاعة محمد صلى الله عليه وسلم : "من قال لا إله إلا الله خالصا من قلبه أو نفسه" رواه البخاري 
“የነብዩን ምልጃ ለማግኘት ከሰዎች ሁሉ እድለኛው ከልቡ ወይም ከነፍሱ ጥርት አድርጎ ላኢላሃ ኢለላህ ያለውን ቃል የተናገረ ሰው ነው፡፡”
(ሐዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡)
9- የምንሰራቸው ስራዎችና ንግግሮች የሚመዘኑትና ተቀባይነት የሚያገኙት በተውሒድ ነው፡፡
10- ተውሒድ ካለ መልካም ስራዎችን ለመስራት መጥፎ ተግባራትን ለመተው ነፍስ ትገራለች፡፡ ተውሒድ ያለው ሰው መከራን በቀላሉ ይጋፈጣል፡፡ ተውሒድ ያለው ሰው የአላህን ውዴታ ተስፋ አድርጎ  ቅጣቱን ፈርቶ ጌታውን ይታዘዛል፡፡
11- የተውሒድ ባለቤቶች ኢማንን እንዲወዱ ክህደትን አመጽንና ወንጀልን እንዲጠሉ አላህ ያደርጋል፡፡
12- ተውሒድ መጥፎ ነገሮችን በትዕግስት ለማስተናገድና የአላህን ውሳኔ በልበ ሰፊነት ለመቀበል ትልቁ ሰበብ ነው፡፡
13- ተውሒድ ሰዎችን ከመፍራት በእነርሱ ተስፋ ከማድረግ ለእነርሱ ብሎ ከመስራት በአጠቃላይ ከፍጥረት ባርነት ነጻ ያደርጋል፡፡ ትክክለኛ ልቅናና ክብር በተውሒድ ይገኛል፡፡
14-  በተውሒድ ምክንያት ጥቂት መልካም ስራዎች ከአላህ ዘንድ እጥፍ ድርብ ይሆናሉ፡፡
15- የተውሒድ ባለቤቶችን አላህ በዱንያም ይሁን በአኼራ ሊረዳ ዋስትና ወስዷል፡፡


ኢብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ከእርሱ ውጭ ያሉ ነገሮችን እርግፍ አድርጎ በመተውና እርሱ በሚወዳቸው ነገሮች  ወደአላህ በመቃረብ ልቦች ሙሉ ደስታንና የእምነትን ጥፍጥና ያገኛሉ፡፡ ይህ ነው የላኢላሃ ኢለሏህ ሀቂቃ ወይም እውነታ፡፡”

نور التوحيد وظلمات الشرك في ضوء الكتاب والسنة (ص: 16-20)

https://t.me/alateriqilhaq

Post a Comment

0 Comments