Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፆም እያለበት የሞተ ሰው

ፆም እያለበት የሞተ ሰው
~~~~~~~~~~~~~~~
① በሕመም ምክንያት ያፈጠረ ሰው እስከሚሞት ድረስ ሕመሙ አብሮት ከዘለቀ ቤተሰቡ እንዲፆሙለት አይገደድም። ምስኪን ማብላትም አይጠበቅባቸውም። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና
(لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَاَ)
[البقرة 286]
"አላህ ነፍስን የችሎታዋን ያክል እንጂ አያስገድዳትም፡፡" [አልበቀራ: 286]
② ቀዷ ማውጣት ሲችል ተዘናግቶ ሳይፆም የሞተ ከሆነ ቤተሰብ ሊፆምለት ይገባል። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
من مات وعليه صيام صام عنه وليه
"ፆም እያለበት የሞተ ሰው ቤተሰቡ/ ዘመዱ ይፆምለታል።" አቡ ዳውድ ዘግበውታል።

ማሳሰቢያ

ቤተሰብ ወይም ዘመድ ያልሆነም ሰው ለሟች መፆም ይችላል። ምክንያቱም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በእዳ ነው የመሰሉት። [ቡኻሪ: 1953] [ሙስሊም: 1148]
እዳን ደግሞ ሌላም ሰው ለሟች መክፈል ይችላል።
والله أعلم

Ibnu Munewor

Post a Comment

0 Comments