Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሐዲስ ሐዲሱን ብቻ!


ሐዲስ ሐዲሱን ብቻ!
.
.
#1. ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መካን የከፈቱ ግዜ እንዲህ ብለው ነበር ...
.
"እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አላህ የጃሂሊያን/ድንቁርና/ ኩራት እና በአባቶች ከፍ ከፍ ማለትን ከናንተ ላይ አስወግዶላችኋል፤ ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው ... መልካም አላህን ፈሪ - አላህ ዘንድ የተከበረ እና አመፀኛ ዕድለቢስ - አላህ ዘንድም የተዋረደ ናቸው። ሰዎች የአደም ልጆች ናቸው፤ አላህም አደምን ከአፈር ፈጥሮታል" (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
.
.
#2. ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ... "እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁ አንድ ነው፤ አባታችሁም (አደም) አንድ ነው። አረቡ ሌላውን አይበልጥም፣ ሌላውም አረብን አይበልጥም፤ ቀዩ ጥቁሩን ጥቁሩም ቀዩን አይበልጥም፤ አላህን በመፍራት ቢሆን እንጂ" ሰሒሕ አል አልባኒ
.
.
#3. ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘረኝነትን "ጥንብ ናትና ተዋት" ብለዋል 
.
.
#4. ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሳቸው ኡማ/ህዝብ ውስጥ ሰዎች የማይተዋቸው አራት የጃሂሊያ/ድንቁርና/ ጉዳዮች እንዳሉ ሲናገሩ ከጠቀሷቸው ሁለቱ ... "በዘር መመፃደቅ እና በዘር መሰዳደብ" ነበሩ። (ሙስሊም ዘግበውታል)
.
.
#5. ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይህን አሉ ..."በውዳቂ ሰንደቅ ስር የሚዋጋ፣ ወደ ዘረኝነትም የሚጣራ፤ ለዘረኝነቱ ሲል የሚቆጣ፤ ሞቱ የድንቁርና/ጃሂሊያ ነው" ሙስሊም ዘግበውታል
.
.
#6. ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይህን ብለው ነበር ... "ስራው ወደኋላ ያስቀረው ዘሩ ወደፊት አያስቀድመውም"
.
.
#7. በጨረሻም ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ... "ወንድምህን በዳይም ሆነ ተበዳይ ሆኖ እርዳው" አሉ። 
ሶሐቦችም "ተበዳይ እንደሆነ እንረዳዋለን፤ እየበደለ ግን እንዴት እንረዳዋለን?" ሲሉ ጠየቁ ... 
እሳቸውም ሲመልሱ "እጁን ትይዘዋለህ፤ ወይም ከበደል ታቅበዋለህ፤ ይህ ነው መርዳት"
.
#Share ማድረግ አይዘንጉ!

Mohammed Ibrahim Ali
September 22 at 2018 

Post a Comment

0 Comments