Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አህሉስ-ሱንና ወልጀማዐህ ፡ ከሌሎች አንጃዎች ከሚለዩባቸው መገለጫዎች የሚከተሉት ጥቂቶች ናቸው፦

አህሉስ-ሱንና ወልጀማዐህ ፡ ከሌሎች አንጃዎች ከሚለዩባቸው መገለጫዎች የሚከተሉት ጥቂቶች ናቸው፦
1.በዐቂዳም ይሁን በሸሪዐ ህጎች ወይም በባህሪ መካከለኛ እና ሚዛናዊ እንደሆኑ ሁሉ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ባሉ አንጃዎችም በጫፍ ረገጦች እና በዘቀጡት መካከል የሚጓዙ የፍትሀዊነት እና የመካከለኝነት ባለቤቶች ናቸው።
°
2.የመረጃ ምንጫቸውን ቁርአን እና ሐዲስ ያደርጋሉ ፤ ለቁርአን እና ለሐዲስ ትኩረት በመስጠት ፤ (ቁርአን እና ሐዲስን) በሰለፎች አረዳድ ይገነዘባሉ። ሙሉ በሙሉ -ለቁርአን እና ሐዲስ - ታዛዥ ይሆናሉ።
°
3.የተቃራኒውን ንግግር እርግፍ አድርገው የሚተውለት ፤ የእርሱን ንግግር ሙሉ በሙሉ የሚይዙለት ታላቅ መሪ ከመልእክተኛው - ﷺ - ውጭ በፍፁም የላቸውም። ስለ መልእክተኛው - ﷺ - አጠቃላይ ባህሪ ፣ ንግግር እና ተግባር ከእነርሱ የበለጠ የሚያውቅ አንድም ሰው የለም። በዚህ ምክንያት ሱንናን ለመከተል እና የሱንናን ባለቤት ለመውደድ ያላቸው ፍቅር የጎላ ነው።
°
4.በዲን ላይ ንትርክን በመተው ፤ በሐላል እና በሐራም ዙሪያ የሚደረግን ሙግት እና ክርክር ከነባለቤቱ በመራቅ ወደ ዲናቸው ጥቅልል ብለው ይገባሉ።
°
5.ለመልካም ቀደምቶቻችን ትልቅ ክብር ይሰጣሉ ፤ የሰለፎች መንገድ ሰላማዊ ፣ በእውቀትና በጥበብ የተነካ እንደሆነ ያምናሉ።
°
6.(ቁርአናዊና ሐዲሳዊ መረጃዎችን) እየጠመዘዙ መተርጎምን (ተእዊል) በማውገዝ ፤ ለሸሪዐው ታዛዥ ይሆናሉ። ከ(ደካማው) አእምሮ ይልቅ ለነቅል (ከአላህ ለወረደው ወሕይ) ቅድሚያ ይሰጣሉ። ዓቅል የነቅል ተከታይ እና ተገዥ መሆኑንም ያምናሉ።
°
7.በአንድ (አወዛጋቢ) ነጥብ የተለያዩ መረጃዎችን በመዳሰስ ብዥታን ያስወግዳሉ።
°
8.በዘመን እና በቦታ ቢለያዩም በመስረታዊ የዐቂዳ ጉዳይ አንድ በመሆን እና በሐቁ ላይ በመፅናት እውቀትን ከአምልኮት ፣ ተወኩልን ከስራ ፣ ዱንያን በአግባቡ ከመጠቀም ፣ ፍርሀትን ከተስፋ ፣ ፍቅርን ከጥላቻ ፣ ለሙእሚኖች ማዘንን ለከሀዲዎች ብርቱ ከመሆን ጋር በማጣመር ወደቀኝ እና ወደ ግራ ሳይሉ ቀጥ ወዳለው መንገድ ህዝብን የሚመሩ የደጋጎች ተምሳሌት ናቸው።
°
9.ከኢስላም ፣ ከሱንና እና ከጀማዐህ ውጭ በሌላ መጠሪያ አይጠሩም።
°
10.ትክክለኛ የሆነው ዐቂዳ ፣ ቀጥ ያለው ዲን ትኩረት ተሰጦት ወደ ህብረተሰቡ እንዲሰራጭ ፤ ሰዎችን ለማስተማር እና አቅጣጫ ለመስጠት ፤ እንዲሁም ለእነሱ ምክር በመለገስና ጉዳያቸውን ለማስፈፀም ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አላቸው።
°
11.በዳዕዋቸው ፣ በእምነታቸው እና በንግግራቸው ላይ በመታገስ ተወዳዳሪ የላቸውም።
12.በጀመዐህ እና (በእርስ በርስ) ትስስር ፤ (በሙስሊሞች) መካከል ክፍፍልን እና ልዩነትን የሚያመጡ ጉዳዮችን በማስወገድ እና በማስጠንቀቅ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሞራል አላቸው።
°
13.ዕውቀትን እና ፍትሃዊነትን መሰረት አድርገው በሰዎች ላይ ፍርድ ይሰጣሉ። (ያለእውቀት) ከፊሉ ከፊሉን ከማክፈር አላህ ጠብቋቸዋል።
°
14.ከፊሉ ከፊሉን ይወዳል ፤ እርስ በእርሱ ይተዛዘናል ፤ በመካከላቸው ይተጋገዛሉ ፤ አንዱ የአንዱን ጎደሎ ይሸፍናሉ ፤ ውዴታቸውም ይሁን ጥላቻቸው ዲንን መሰረት ያደረገ ነው።
°
በጥቅሉ ፡ ከሰዎች ሁሉ በባህሪ መልካሞች ፤ አላህን በመታዘዝ ነፍሳቸውን (ከተለያየ ቆሻሻ) የማጥራት ከፍተኛ ጉጉት ያላቸው ፤ የእይታ አድማሳቸው የጎላ ፤ አርቆ አሳቢ ልዩነትን የማስተናገድ አቅማቸው የሰፋ ፤ የልዩነትን መሰረቶች እና አደቦች የሚያውቁ ናቸው።
________________
ምንጭ ፦ (አልወጂዝ ፊ ዓቂደቲ' ሰ-ሰለፊ አስሷሊህ (አህሊ'ስ-ሱንነቲ ወ'ል-ጀማዐህ) ከገጽ 32 እስከ 33
አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @Ibn yahya ahmed
ዙልሒጃህ 11/1439ሂ. # ነሐሴ 16/2010.

የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦https://telegram.me/ibnyahya7
የፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777

Post a Comment

0 Comments