Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙነሺዶቹና ፊልም ሰሪዎች ለምን ረመዳንን ይመርጣሉ?



ሙነሺዶቹና ፊልም ሰሪዎች ለምን ረመዳንን ይመርጣሉ?
እነሱ የፈለገ መልካም አስበን ነው ቢሉም ሙስሊሙን ከረመዳን ወር እያዘናጉት ነው፡፡
ውዴታ በተግባር ይገለፃል፡፡
ረመዳን ቁርዓን የወረደበት፣ ሰይጣን የሚታሰርበት፣ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ የእሳት በሮች የሚዘጉበት፣ ቁርዓን በብዛት የሚቀራበት፣ ተራዊህ የሚሰገድበት፣ ሰደቃ የሚበዛበት ታላቁ የአምልኮ ወር ነው፡፡
ሰይጣን እና ሰራዊቶቹ “ከአላህ ጋር ልናጣላችሁ ነው” ብለው በግልፅ ቢመጡ ማንም አይቀበላቸውም፡፡ እነሱ ግን ይህን አይደለም የሚያደርጉት ይልቁንስ ከዚህ በተገላቢጦሹ አዛኝ፣ መካሪና ተቆርቋሪ መስለው ነው እራሳቸውን የሚያቀርቡት፡፡ ሰይጣን አደም እና ሀዋን አላህ የከለከላቸውን ፍሪ እንዲበሉ ሲጎተጉት እንዲህ ነበር ያላቸው
وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّى لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ
“እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ” ሲልም አማለላቸው፡፡
ተመልከቱ “እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ” ሲል ሽነገላቸው፡፡ የአላህ ባሪያዎች ሆይ እስቲ ተመልከቱ በዚህ በተከበረ ወር ሰዎች ቁርኣንን እንዳይቀሩ ለማዘናጋት “ኢስላማዊ ፊልም፣ ኢስላማዊ ነሺዳ፣ ኢስላማዊ ድራማ” እየተባለ ሰዉን ያዘናጉታል፡፡
አስገራሚው በአላህ ፍቃድ ከዘፈን የተመለሰው ሙሐመድ አወል ሳላህ ዛሬ ፂሙን ላጭቶ “ዉዴታ እስከ ጀነት” ሲል ይሰብካል፡፡ ሙኣዝ የተባለው ደግሞ ፀጉሩን ፓንክ ተቆርጦ “እኔን” ይላል፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፂማችሁን ልቀቁት፣ ቀድሞ ቀመሳችሁን (ከንፈር ላይ ያለውን) ቁረጡት” ሲሉ ያውም ዛሬ እንደ ሙሐመድ አወል ሳላህ ያሉት ኢስላማዊ ሙነሺድ ተብለው የነብዩን ትዕዛዝ ተቃርኖ ፂሙን ይላጫል ሱሪውንም ይለቃል፡፡ ሙኣዝም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ፀጉራችሁን ስትቆረጡ አንዱን ካንዱ አታበላልጡት” የሚለውን የነብዩ ትዕዛዝ ጥሶ “ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ” ሲል ይቀጣጥፋል፡፡ አሳዛኙ የአላህ መስጂድ ቤቶች በሮቻቸው በእንዲህ አይነት ግለሰቦች ፎቶ ተበላሽተዋል፡፡ የአላህ ቤቶች ከማንኛውም ምስል መፅዳት ሲገባቸው፡፡
እንደሚታወቀው ረመዳን ሲወጣ ብዙ ሰዎች ከመስጂድ እና ከመልካም ነገሮች ይርቃሉ፡፡ እንዲህ አይነት በሽታዎችን በአላህ ፍቃድ የሚያሽረው የጌታችን የአላህ ቃል ቁርኣን ነው፡፡ እነዚህ መንዙማ፣ ነሺዳ ባዬች፣ ፊልም አክተሮች ከመስጂድ ርቆ የነበረውን ሙስሊም የአላህን ቃል እንዳይቀራ፣ እንዳያዳምጥ ጋሬጣ ሆነውበታል፡፡
ቁርኣን ፀጥ ብሎ ላዳመጠው የአላህን እዝነት ያስገኛል፡፡ ከቀራው በእያንዳንዱ ሀርፍ 10 ያስከፍላል፡፡ ፊልም የሚሉት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ አይመልከት፣ ሴት ልጅ ወንድ ልጅን አትመልከት” ያሉትን ነብያዊ ትእዛዝ ተቃርኖ በውሸት ገፀ ባህሪ ሙስሊሙን ያጠማል፡፡ አጅር አይገኝበትም፡፡ ሙነሺድ ተብየዎቹም በሸሪኣ የተቀመጠው ግጥም ሆኖ ሳለ ይዘፍናሉ፣ ያዜማሉ….. የመሳሰለውን፡፡ ይህም ለሙስሊሙ ምንም አይፈይድም፡፡ ምክንያቱም አንድ አምልኮ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ኢኽላስ እና ሙታበኣን (የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ገጥሞ መገኘት አለበት) ሊኖረው ግድ ይላል፡፡
ከማንም በላይ አላህን እና መልክተኛውን በተግባር ወደው ያሳዩን ሰሃባዎች በረመዳንም ይሁን ከረመዳን ውጭ ፊልምና ድራማ እየሰሩ ሱሙንም “ኢስላማዊ” እያሉ አልነበረም፡፡ ኢስላማዊ ነሺዳ ብለውም የእራሳቸውንም ከነሱ በኋላ የመጡትን ጊዜ አላባከኑም ነበር፡፡
ፊልም፣ ነሺዳ፣ መፀሀፍ ምርቃት እያሉ ቲያትር ቤት ሰዎችን ጠርተው ወንድ እና ሴቶችን ያለ መጋረጃ ሳይለዩ በተለያየ ረድፍ አስቀምጠው ለፈተና መዳረግ መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው፡፡
አላህን እንፍራ፡፡
ዉዴታ በተግባር ይገለፃል፡፡ ሰሃባዎች ከእኛ በላይ አላህን እና መልክተኛውን ይወዳሉ፡፡ እነሱ ረመዳናቸውን በቁርኣን፣ በተራዊህ በሰደቃ እንዳሳለፉት እኛም እናሳልፍ፡፡
መልካም ሁሉ ሰለፉነ ሷሊሂንን በመከተል ላይ ነው፡፡ መጥፎ ሁሉ መጤ መንገዶች እና አስተሳሰቦችን በመከተል ላይ ነው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts

Post a Comment

0 Comments