Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሽንት ቤት አጠቃቀም ስነ ስርኣት



የሽንት ቤት አጠቃቀም ስነ ስርኣት
ፅሑፉን ለማሳጠር ስል በእያንዳንዱ ነጥብ ስር ያሉትን ማስረጃዎች አልጠቀስኩም። ሆኖም ግን ማስረጃዎቹ የሚገኙበትን ምንጭ ስለጠቀስኩ ያስፈለገው በቁጥሩ ማግኘት ይችላል።
① እንዳይሰረቁ ወይም እንዳይጠፋ ካልሰጉ በስተቀር የአላህ ስም ያለበት ነገር ይዞ ሽንት ቤት ውስጥ አለመግባት።
② የሚፀዳዱት ሜዳ ላይ ከሆነ ከሰው እይታ ራቅ/ ሰወር ማለት። [ሶሒሕ ኢብኑ ማጃህ: 1/ 60]
③ በሰው መተላለፊያ መንገድ ላይ ወይ አጠገብ፣ ሰዎች ከሚጠለሉበት ዛፍ ስር፣ ፍሬው ከሚበላ ዛፍ ስር፣ የፍራፍሬ ዛፍና አትክልቶች አጠገብ፣ ወራጅ ባልሆነ ውሃ ላይ፣ የውሃ ምንጭ ላይ፣ በሙስሊሞች መቃብር ውስጥ አለመፀዳዳት። [ኢርዋኡል ገሊል: 1/100] [ሙስሊም: 269፣ 281] [ኢርዋእ: 1/102]
④ ንፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ዙሮ አለመፀዳዳት፣ ይህን ትኩረት መስጠት ለጤናም፣ ለንፅህናም የተሻለ ነው።
⑤ የተሰነጠቀ መሬት ላይ ወይም ቀዳዳዎች ላይ አለመፀዳዳት። [አቡ ዳውድ: 29]
⑥ ውጭ ላይ የሚፀዳዱ ከሆነ ወደ መሬት ዝቅ እስከሚሉ ልብስን አለመሰብሰብ ወይም አለማውረድ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4652]
⑦ ውጭ ላይ በሚፀዳዱ ጊዜ ወደ ቂብላ አለመዞር፣ ጀርባንም ለቂብላ አለመስጠት። ሽንት ቤት ውስጥ ከሆነ ወይም ከፊት የሚጋርድ (ግድግዳና መሰል) ነገር ከኖረ ችግር የለውም። ይህንንም ቢሆን ከተቻለ መጠንቀቅ። [ቡኻሪና ሙስሊም] [ኢርዋእ: ቁ· 61]
⑧ ሽንት ቤት ሲገቡ ግራ እግርን ማስቀደም፣
⑨ ሽንት ቤት ሲገቡ "ቢስሚላህ። አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹቡሢ ወልኸባኢሥ" ብሎ ከሸይጧን መጠበቂያ ዱዓ ማድረግ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 3611] [ቡኻሪና ሙስሊም]
(10) በሚፀዳዱ ጊዜ ብልትን በቀኝ እጅ አለመንካት፣ በቀኝ እጅ አለመፀዳዳት፣ [ቡኻሪና ሙስሊም]
(11) በሚፀዳዱበት ጊዜ በተቻለ መጠን ከማውራት መቆጠብ። [ሙስሊም: 370]
(12) ቢያንስ በሶስት ድንጋይ፣ ሶፍት፣ ወረቀትና መሰል ነገር መፀዳዳት። አንድም ቢሆን ሶስት የተለያዩ ጎኖች ወይም ገፆች ከኖሩትም በቂ ሊሆን ይችላል። ወይም በውሃ መጠቀም። አጥንት፣ ፋንዲያ፣ ምግብ ነክ ነገር እና ንፁህ ያልሆነ ነገር ለመፀዳጃነት አይውልም። [ሙስሊም: 262፣ 263፣ 271]
(12) ከሽንት ቤት ሲወጡ ቀኝ እግርን አስቀድሞ መውጣት።
(13) ከሽንት ቤት ሲወጡ "ጉፍራነክ" ማለት። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4707]
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 26/2010)

Post a Comment

0 Comments