🌿 ሙራቀበቱላህ! 🌿
የአላህ ፍራቻ "ተቅዋ" ን ለመላበስ እና ኢማንን ለማበልፀግ ከሚያግዙ ብዙ ነገሮች መካከል የአላህን ተቆጣጣሪነት ማሰብ እና ለምንሰራው ስራ ሁሉ አላህ እንደሚያየን ማሰብ "ሙራቀበቱላህ" በብዙ ኡለማዎች በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።
አላህ ተመልካች መሆኑን በማስታወስ አላህን በራሳችን ላይ ተቆጣጣሪ ማድረግ ስንል፤ ስራን መገምገም፣ በግልፅም ይሁን በድብቅ የምንሰራዉን ሁሉ አላህ እንደሚያውቅ ማስተዋል ማለት ነው።
አላህ ከፍጥረታቱ ጋር ነው፤ ለእርሱ የታዘዙትን እና እርሱን ብቻ የተገዙትን በእርዳታው ከነሱ ጋር ነው። የካዱትም ቢሆን በአላህ ቁጥጥር ውስጥ ናቸው።
አላህን ባናየው እንኳ እርሱ ያየናልና ስናመልከው እንደምናየው አድርገን መሆን አለበት። ኢህሳን የምንለው የመልካም ስራ እርከን ይህ ነው። ከአላህ እይታና ቁጥጥር መራቅ አንችልም።
ስለዚህም፤ ለምንናገረውና ለምንሰራው ሁሉ አላህን እንፍራ! መልካም ስራን ስንፈፅምም ፍፁም ለአላህ ብቻ ይሁን።
በተለይ ከሰዎች እይታ በራቅንበት ወቅት አላህን በኛ ላይ ተቆጣጣሪ ማድረግ ተቅዋን በእጅጉ ከሚያበለፅጉ ነገሮች አንዱ ነው።
አል አንደሉሲይ ልጃቸውን ለመምከር የቋጠሯቸው ስንኞች ተከታዩን መልእክት ያዘሉ ነበሩ፤
وإذا خلوت بريبة في ظلمة
والنفس داعية إلى الطغيان
አል አንደሉሲይ ልጃቸውን ለመምከር የቋጠሯቸው ስንኞች ተከታዩን መልእክት ያዘሉ ነበሩ፤
وإذا خلوت بريبة في ظلمة
والنفس داعية إلى الطغيان
فاستحيي من نظر الإله وقل لها
إن الذي خلق الظلام يراني
إن الذي خلق الظلام يراني
በጨለማ አሻሚ ቦታ ላይ ሆነህ
ነብስህ ድንበር እንድትጥስ ስትገፋፋህ፤
ነብስህ ድንበር እንድትጥስ ስትገፋፋህ፤
ጌታህ ያይሀልና ሀፍረት ይሰማህ
ለነብስህም በላት፤
ጨለማን የፈጠረው አምላክ ይመለከተኛል!!
ለነብስህም በላት፤
ጨለማን የፈጠረው አምላክ ይመለከተኛል!!
አዎን! አላህ ኢስቲቃማን ይሰጥህ ዘንድ በጌታህ ታገዝ አትሳነፍም!
🔗 ከአቡሁረይራ በተዘገበ ሀዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ : ”...احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ وَاسْتَعِنْ بِاللهِ وَلَا تَعْجَزْ، وَإِنْ أَصَابَكَ شَرٌّ فَلَا تَقُلْ لَوْ أَنِّي فَعَلْتُ كَذَا وَكَذَا قُلْ قَدَّرَ اللهُ وَمَا شَاءَ اللهُ فَعَلَ، فَإِنَّ لَوْ تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطَانِ“ رَوَاهُ مُسْلِم
ٌ
«በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አትሰላች፤ መጥፎ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ፤ ‘ይህን ነገር እንዲህ ወይም እንዲያ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል» ሙስሊም ዘግበዉታል
ٌ
«በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አትሰላች፤ መጥፎ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ፤ ‘ይህን ነገር እንዲህ ወይም እንዲያ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል» ሙስሊም ዘግበዉታል
አላህ ተቅዋን እና መልካም ስራን ያግራልን!
وصلَّى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلَّم
© ተንቢሀት
http://www.t.me/tenbihat
http://www.t.me/tenbihat
0 Comments