بسم الله الرحمن الرحيم
አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን ማስተማር ፣ ቁርአን የአላህ ንግግር መሆኑን ማመን፣ መውሊድም ቢድዓና የተወገዘ ነው ብሎ ማመንና መግለፅ አንድ አማኝ ሰለፊ መሆኑን ከሚጠቁሙ ትልልቅ አቋሞች ውስጥ ለመሆናቸው ጥርጥር የለም! ! ነገር ግን በነዚህና በመሰል የዓቂዳና የቢድዓ ጉዳዮች ቀጥተኛ አቋም ያለው ሁሉ ከአህሉሱና ነው ማለት አይደለም — አንዳንድ የኡለሞችን አስተምሮ በመዘንጋት ይሁን ባለማወቅ የራሳቸውን ስሜት በመፃፍ የተጠመዱ ሚስኪኖች ነው ይህን ለማለት ቢዳዳቸውም! !
ይህንን ሓሳብ ፉሩሽ የሚያደርግ አንድ ምሳሌን ልጥቀስ ፣
ነብዩ የቢድዓ ሰዎች የተረገሙ መሆናቸውን በገለፁበት ሓዲስ ላይ ለነዚህ አካላት ከለላ የሚሰጠውም ይህንኑ እርግማን እንደሚቋደስ ገልፀዋል! ከለላ ይሰጣል የሚባለው ደሞ ለነሱ የሚከራከር ፣ ባጢላቸውን በመደበቅ የሚሞግት ሱና ላይ መሆናቸውን በውሸት የሚመሰክረው አካል መሆኑን የኡለሞች ትንታኔ ያመላክታል!
በዓቂዳው "አሽዓሪ " "ማቱሪዲ" ባይሆንም አንድ አማኝ ለነዚህ የቢድዓ አንጃዎች የሚሟገትና በአንድነት ስም ይሁን በሌላ "እነሱን አትንኩብኝ" "ከሱና አይወጡም" በማለት ጥብቅና የሚቆምላቸው ከሆነ የሙብተዲዖችን ጎራ በገዛ ፈቃዱ ተቀላቅሏል— ዑለሞቻችን እነደሚሉት።
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ፣ ኢብኑ ባዛና ሌሎች ዑለሞቻችን እንዳሉት፣ አንድ ግለሰብ ስለ አንድ የቢድዓ አንጃ ጥመት ከተነገረውና ከተብራራለት በሗላ ለዚህ አንጃ ከለላ የሚስጥ ከሆነ ራሱ ከነሱ ነው ብለዋል ።
እናም አንድ ሙስሊም የቢድዓ ሰው የሚባለው የግድ አላህ ከአርሹ በላይ መሆኑን ሲክድና የመውሊድን ቢድዓነት ሲያስተባብል ብቻ አይደለም!!
