Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዩሱፍ አል ቀርዳዊ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ ።

ዩሱፍ አል ቀርዳዊ አላህን የተሳደበ ፣ ሰሐባዎችን የተሳደበ ፣ አላህና መልዕክተኛው ሀራም ያደረጉትን ሀላል ያደረገና ሌሎች ብዙ ወንጀልና የኩፍር ትምህቶችን ያስተማረ ፣ ከኢስላም ምንም ድርሻ እንደሌለው በኡለማዎች የተረጋገጠለት ሰው ነው ። 

በወንጀሉ ምክንያት አንደነ ሼኽ ኢብኑ ኡሰይሚን ባሉ በአለማችን ስመጥርና ታላላቅ በሆኑ የኢስላም ሊቃውንቶች የሞት ፍርድ የተላለፈበት ወንጀለኛ የሆነ ግለሰብ ነው ።

ከኢስላም ጠላቶች ጋር በመተባባር ሶሪያ ፣ ሊቢያና የመን እንዲፈራርሱ ፣ እርስ በእርስ ደም እንዲፋሰሱ ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከተም ሰው ነው ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ላይ አንዳንድ ሰዎች የቀርዳዊና የመሰሎችን የተሳሳተ አመለካከት ለማስተዋወቅ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ።

ለዚህም ዋነኛ ምክንያታቸው የፖለቲካ ስልጣን ለመቆናጠጥ ሲባል አመፅና ረብሻ ለማነሳሳት የነዚህን ሰዎች ትምህት ጠቃሚ ሆነው ስላገኙት ነው ።

በርግጥም ትምህርታቸው በኢትዮጲያ ላይ አመፅ ለማስነሳትና ሀገራችንን ለማፍረስ የሚጠቅም አይደለም አይባልም ። ሀገር ለማፍረስ ሊጠቅም ይችላል ፥ ነገር ግን ሀገርን መልሶ ለማግኘትና አኼራ ላይ ነጃ ለመውጣት የሚጠቅም ግን አይሆንም ።

ወንድም እህቶቼ ከቀርዳዊም ሆነ የሱን ትምህርት ከሚያሰራጩ ሰዎች ራሳችሁን ጠብቁ ፣ አትከተሏቸውም ፣ በተቻለ መጠን ምከሯቸው እንቢ ካሉ ግን ራቋቸው ። ጀሀድ ብለው ለሰልፍ ለአመፅ ሲጠሯችሁ እሺ አትበሏቸው ። ከቤታችሁም አትውጡ ። እነሱ እየተደበቁ እናተን በማስፈጀት ሀገራችሁን አፈራርሰው ሀገር አልባ አድርገው ያስቀሯችኋልና ።

☞ ታላላቅ ኡለማዎች ከቀርዳዊና ከስራዎቹ በተደጋጋሚ ጊዜ አስጠንቅቀዋል !!

☞ ከታች ያለውን ሊንክ በመክፈት የኡለማዎቹን ፈትዋ ፣ የሱን የኩፍር ፣ የወንጀል ንግግሮችና አቋሞቹን ማግኘት ትችላላችሁ ።

1) ቀርዳዊ ሙዚቃን ሀላል ያደረገበት ።

https://youtu.be/UnOaiYvKv3s

https://youtu.be/F91XFPHnCLg

2) ቀርዳዊ ሴት መጨበጥን ሀላል ያደረገበት

https://youtu.be/0OW4Y5UXRXs

3) ሪባን ( ወለድን ) ሀላል ያደረገበት

https://youtu.be/sfn5GiZ9s8E

4) ሂጃብ ማውለቅን የፈቀደበት

https://youtu.be/0Y5sJ6HfAWo

5) ከሸሪአ ህግ ይልቅ የፖለቲካ ህግ ይሻላል ብሎ የከፈረበት ንግግር

https://youtu.be/jM01nmeoc6I

6) አላህን የተሳደበበትና ኡለማዎች የፈረዱበት ፍርድ

https://youtu.be/Q6jKlgiOpPM

7) የአለማችን ስመ ጥርና ታላላቅ ኡለማዎች ከቀርዳዊ ያስጠነቀቁበት ሙሉ ዝርዝር መረጃ ።

https://youtu.be/3jxMzg6kc44

የዚህ ሰውዬ ጥፋትና ጉድ ተቆጥሮ የሚዘለቅ አይደለም ። ለዛሬ ይሄ ይበቃናል ። ካስፈለገም በሌላ ጊዜ ከነኪታቦቹ መረጃዎቹን ሁሉ በዝርዝር ማቅረብ ይቻላል ።

በረሱል ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ ሰላምና እዝነት ይስፈን ።