✋🏼 ልጆቻችሁን አብዙ ሪዝቃችሁ ይበዛል!
👈🏽 ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ ...
❌ " 'ልጆችን አታብዙ ሪዝቃችሁ ይጠባል' በማለት በጌታው ላይ መጥፎን የገመተ በእርግጥ ግልፅ የሆነ ጠመትን ጠሟል!
➰ በዓርሽ ጌታ እምላለሁ ዋሽተዋል! ልጆቻቸውን ቢያበዙ አላህ ሪዝቃቸውን ያበዛላቸዋል፤ ምክንያቱም ከአላህ ሪዝቅ ቢኖራት እንጂ በምድር ላይ አንድም ተንቀሳቃሽ አትኖርም!
✅የልጆችህና የህፃናቶችህ ሪዝቅ በአሸናፊውና የላቀው አላህ ላይ ነው። በእነርሱ ላይ እንድትለግስ የሪዝቅን በር የሚከፍትልህ እርሱ ነው!
⁉ ነገርግን ብዙ ሰዎች በአላህ ላይ መጥፎ ጥርጣሬ አላቸው፤ በሚታዩ ቁሳዊ ጉዳዮች ላይ ይመረኮዛሉ፤ ራቅ ወዳለ
ግብ፤ ወደ አሸናፊውና የላቀው አላህ ችሎታ አይመለከቱም። ልጆች ቢበዙም ሪዝቁን የሚለግሰው እርሱ ነውና።
✔ ልጆችህን አብዛ ሪዝቅህ ይበዛልሀል፤ ይህ ነው ትክክለኛው!
📚 ሸርህ ሪያዱ ሷሊሒን 1/91
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•