Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወጣት ሆይ ልብ ብለህ ስማ!! በምን መልኩ ትዳር ስንመሰርት ነዉ አላህ ቃል የገባልንን ሚሞላልን? ለምንስ ነዉ የምታገቡት?

ወጣት ሆይ ልብ ብለህ ስማ!!
በምን መልኩ ትዳር ስንመሰርት ነዉ አላህ ቃል የገባልንን
ሚሞላልን? ለምንስ ነዉ የምታገቡት?
1በኑሮ ለመደጎም?
2 ገንዘብ ለመቆጠብ?
3 ልብስ ለማሳጠብ?
4 ምግብ ለማስበሰል?
5 የተቃራኒ ጾታ ፍላጎትህን ለማሟላት?
6 ሌሎች ጓደኞችህ ስላገቡ?
7 እናት አባትህ እንድታገባ ስለሚፈልጉ?

ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ኣንድ ሙስሊም ትዳር እንዲመሰርት የሚያደርጉት ዋነኛ ነጥቦች አይደሉም፡፡
ኣንድ ሙስሊም ትዳር መመስረት ያለበት እነኚህን ነጥቦች
መሰረት በማድረግ ነዉ
• የ አላህና የመልእክተኛዉ ትእዛዝ ስለሆነ!
• መልእክተኛዉ የተገበሩት ተግባር(ሱና)ስለሆነ!
• ብልታችንን ከሀራም ለመጠበቅ ና አይናችንን ለመስበር!
• ኢስላማዊ ቤተሰብ ለመመስረት ና በርሱ ዉስጥ የሚገኙትን ምንዳዎች ለማግኘት በትዳር ዉስጥ ያለ ምንዳ ሲባል ለአብነት ያህል ለተለያዩ ነገሮች ከሚሰጡ ሰደቃዎች በሙሉ በላጩ ባል ለቤተሰቡ የሚያወጣዉ ሰደቃ ነዉ ማለትም በሰደቃ ከነየተ ማለት ነዉ፤ለምሳሌ በአላህ መንገድ
ላይ የሚሰጥ ሰደቃ እንዲሁም ለሚስኪን ከሚሰጥ ሰደቃ ሁሉ ባል ለቤት ዉስጥ መሽሩፍ እና ለተለያዩ ለቤት ዉስጥ ወጪዎች የሚያወጣዉ ገንዘብ ምንዳዉ አላህ ዘንድ በላጭ ነዉ።
ለነኚህን አራት አላማዎች ብለን ትዳርን የምንመሰርት ከሆነ
አላህ በቁርኣን ዉስጥ ቃል በገባልን መሰረት ደስተኛ ህይወትን እንድንኖር እና ደሃ እንኳ ብንሆን ከሲሳዩ ሊያብቃቃን ቃል ገብቷል የ አላህ መልእከተኛም ሰ.አ.ወ
በሀዲሳቸዉ ዉስጥ እንደገለጹት አላህ ለሶስት ሰዎች ቃል
ገብቷል ካሉት ዉስጥ
አንደኛዉ ብልቱን ከሀራም ለመጠበቅ ትዳርን የመሰረተ
ሰዉ ነዉ፡፡ትዳራችን ጤናማ እንዳይሆን እና አላህ ለባለትዳሮች ቃል ከገባዉ መካከል ተቋዳሽ እንዳንሆን የሚያደርጉን ተግባራት!
•የሚረዝቀዉ አላህ ሆኖ ሳለ ልጅ ከመዉለድ ይልቅ ደህነትን
በመፍራት የተለያዩ የወሊድ መከላከያ መድሃኒቶችን መጠቀም።
•ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ዉጪ ለሌላ አላማ ብለዉ
ትዳርን መመስረት።
•በሰርጋቸዉ እለት ሙሽራዋን በማራቆት አደባባይ ላይ ይዞ
መዞር እና በእለቱ በኢስላም የተከለከሉ ተግባራትን መፈጸም።
• የኢማን ጥንካሬዋን እንደ ዋና መስፈርት ከማስቀመጥ
ይልቅ ሌሎች ነገሮችን መስፈርት በማድረግ ትዳር መመስረት፤ለምሳሌ፡-ጎሳዋን፣ሀብቷን፣ዉበቷን ወዘተ።
አላህ የተሻለ አዋቂ ጌታ ነዉ።