Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥቂት ስለ ጠርዘኞቹ እና ሰሞነኛው ድራማ



ነገ አላህ ፊት የሚቆምበት ብርቱ የጭንቀት ቀን እንደሚጠብቀው የማይጠራጠር አማኝ ለምላሱ ልጓም ሊያደርግ እንደሚገባው መገንዘብ አይከብደውም። ይህንን ለመተግበርም የቻለውን ይተጋል።
እያንዳንዱ መልካምና ጸያፍ ንግግር በጠባቂ መላኢኮች የሚጻፍና፣ የውመል ቂያማም ተገቢውን ዋጋ የምንመነዳበት ነውና ምላሳችንን መረን መልቀቁ አክሳሪ አካሄድ ለመሆኑ ሁለት አማኞችን የሚያጨቃጭቅ አይደለም። ግልጽ እውነት ነውና
مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيد ٌ
ۭ
ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡
إِذْ تَلَقَّوْنَهُۥ بِأَلْسِنَتِكُمْ وَتَقُولُونَ بِأَفْوَاهِكُم مَّا لَيْسَ لَكُم بِهِۦ عِلْمٌۭ وَتَحْسَبُونَهُۥ هَيِّنًۭا وَهُوَ عِندَ ٱللَّهِ عَظِيمٌۭ
በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ (ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር)፡፡
ነብዩ እንዲህ ብለዋል
من كان يؤمن بالله واليوم الآخر فاليقل خيرا أو ليصمت
በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል
ንግግር የማያስፈልግበት ቦታ ላይ በዝምታ አልፎ ጠቃሚ የሚባልበት ጉደይ ላይ ደግሞ ድምበር ሳያልፉ በልኩ መናገር እና ሚዛን መጠበቅ ክብርንና ዲንን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው።
የቢድዓ አንጃዎች እና ግለሰቦች ላይ ይቅርና የክህደትና የኩፍር መሪዎች ላይ የሚነገሩና የሚፃፉ ተችቶች ላይ ሚዛን ያስፈልጋል ! ሚዛኑ የተዘባባት ሰው ዝምታው የሻለዋል— ቤቱ ይስፋውና ዝም ይበል! ተናግሮ ከሚያበላሽ!
#ዛሬ ዛሬ በ “ረድ” ስም ቁልቁል ወርዶ ሌሎችችንም እያወረደ ያለው "ልጅ"ና ወጣት ቁጥር ስፍር እያጣ ነው። የሓጁሪ ተከታዮች ደሞ በዚህ ጉዳይ ያንበሳውን ድርሻ አያጡም!
በረድ ስም ስነ ምግባርና ተቅዋቸው እየወረደ የመጣው እኚህ ልጆች የመንደሩ “ድድ አስጪ” ዱርዬ እንኳን የማይናገረውን ፀያፍ ንግግር ሲናገሩ ደጋግመን ሰምተን ደጋግመን ታገስን!
ትእግስቱ ግን ነገሮችን ለማስተካከል ከመፈለግ እና ለሌሎች ነገሮች ቅድሚያ ከመስጠት የመነጨ ሳይሆን የሚባልን ወይም የሚጻፍን ምላሽ ከማጣት የተነሳ መሰላቸውና “ምናምንቴአቸውን” ረድ እያሉ ቀጠሉበት
* ሸይኹል ኢስላም እንደሚሉት ስድብ ከምላሽ (ከረድ) የሚቆጠር አይደለም ይሄንንማ (ስድቡን) ቂላቂሎቹም ይችሉበታል አይሰንፉበትም
# ከቅርብ ጊዜ ወዲህማ “ የኢስቲዋእ” (የዑሉው) መስኣላ ይመስል ቀን ተሌት የሚያነበንቡበት፣
ጀምዕያ ጀምዕይ ሆኗል ! አንዱማ " ጀዕሚያ" አለኝ! ስሙን እንኳን ባግባቡ መጥራት ሳይችል "ጀዕሚያ" ቢድዓ ነው ይላል!
ለመሆኑ ማነው ጀምዒይ የሚባለው?! ጀምዕዮች ዓቂዳቸው ምን ይመስላል?! ኢስቲዋእ ላይ ያላቸው አቋም ምን ይመስላል?! ኡሉህያ ላይስ?! ነው ... ጀምዒያ ይቻላል በማለት ብቻ ጀምዒይ ይኮናል?! አንዲህ ከሆነ የጀምዒዮችን ቁጥር በመጨመር ልተባበራችሁ
የመጀመሪያው ጀምዒይ አልባኒ ሲሆን 2) ibn baz 3) uthaymeen 4) muqbil .. ሌሎችም
# ጀምዒይ እያለ ከሱና ቀለበትየሚያስወጣ / ያስወጣ ዓሊም ጥቀሱልን ስንል ደግሞ ኢብኑ ባዝንም አልባኒንም ዑሰይሚንንም አይጠቅሱም —ያንኑ ኢማማቸው ብቻ እንጂ! እኛ ደሞ እሱን ዝለሉልን ! ይለፈንና .....እንላለን ለምን? እሱን ከነዚህ ኢማሞች ጋር የሚያወዳድር ካለ ጤና ርቆታል እኛ ደሞ ከነ ዓቅላችን ነን!
በተጨማሪም አንድ ወዳጄ ያለውን አስታወስኩ የ “ አሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ” ነውና እሱን ተዉት --—-- ስጋ ቁጠር ቢሉት ....
ሌላው፣
ሰውየውን መቸም በጭፍን ሲከተሉት ጉድ ነው። ትናንት ሷሊሕ አለ ሸይኽን أصبح إخوانيا ብሎ በኢኽዋንነት ሲፈርጃቸው አሜን ብሎ የተቀበለው የሓጁሪ ተከታይዮችአሁን በቅርቡ ይሄው መሪያቸው የተከበሩ ሸይኽ ብሎ በነደፋቸው ምላሱ ሲያሞካሻቸው ያለ ጥያቄ ተቀብለውታል!
ለመሆኑ ሳሊህ አለ ሸይኽ ትናንት ኢኽዋን ያረጋቸው አካሄድ ምን ነበር?! ዛሬ ደግሞ ተከበሩ ሸይኽ?!!አንኳር ነገሩ አንድ ብቻ ነው! ሸይኻቸው ስለተናገረ ብቻ!
ከሰሊም አል ሂላሊ ሲያስጠነቅቁ እንዳልነበረ ደማጅን ዘይሮ መርከዛቸውን ሲያሞካሽላቸው አርቀው ሰቀሉት! ሓጁሪን የነካ ቀን ደሞ አውርደው ይፈጠፍጡታል!
ሌላኛውን የዚህ ድራማ አካል ስንመለከት በርካታ ብልሹ ነገሮ ችን እያየን በዝምታ ማለፍ አንዳንዴም እነዚህን ብሉሹ ነገሮ ች መጋራቱ በጅጉ የሚያስወቅሰው ሆኖ ታየኝ የተለቀቀው ልጅ ከሆነ ለተቀጠረላቸውም ርካሽ የዱንያ ምና ምንቴ ተገቢ ያልሆ ነን ዝንባሌ አሳይተው ያሉትን አሉ። ከነዚህ ነገራቸውም እንዲመለሱ መካሪ ቢመክር መልካም ነው
ለነሱ የሚጠቅመው ከዛ ጥቂት እንዲመለሱ መምከር እንጂ ለነሱ ሙሉ ከለላ መስጠት መሞገት አይደለም
ሰሞ ኑን በተለቀቀው የፊትና ኦድዮዎች ምክንያት ሰው ሲታወክ እንደከረመው ሁሉ እኔም ስታወክ ከረምኩና ለወንድሞ ችና እህቶ ች በአቅሜ ጥቂት ነገርን ለማለት ፈለግኩ ( የሚያሳዝነው በዚህ ፊትና የተደሰቱ ፣ ጮቤ የረገጡ ወፈፌዎች መኖራቸው ነው!
#የሰሞኑን ፈተና በተመለከተ ፣
ሴራውና የጠነሰሱትና ያከናወኑትን ወንበዴዎችን ስንመለከት በትክክልም ተቅዋና ስነ ምግባር የጎደለቸው ሆነው እናገኛቸዋለን! ሙስሊሙን ማህበረሰብ ሊጠቅምና ሊጎዳ የሚቸለውን ነገር የማያውቁ ከመሆናቸው ጋር አቋማቸውን ለማራመድና ለማሳካት አይሁዶች ብሎም ኢኽዋኖ ች መንገድ አድርገው የያዙት “ውሸት” በድፍረትና ብልበ ደረቅነት ሲጠቀሙበት አየን ።
እውነቱንለመናገርያህል የሰሩት ስራ የረከሰ ማንነታቸውን የልቦናቸውን ደዌ አግዝፎ ያሳየ ነበር ! በዚህ ኦድዮው ውስጥ ያላረጉትን አድርገናል የማያደርጉትን እናደርጋለን እያሉ እንደወፈፌ ሲጮሁ መስማታችን ጠንካራ ዱላ እንጂ ልስላሴ የሚያስፈልጋቸውና የማይመልሳቸው ተራ አሉባልተኞችና ውሸታሞችን መሆናቸውን አስገነዘበን !
ይህንን ውንብድና ከፈፀሙት ባልተናነሰ መልኩ (ቅርፁን የለወጠ ቢሆንም )ተመሳሳይ ውንብድና ላይ የተዘፈቁም አሉ — ነገገሩን የደገፉት ! በንግግርም ይሁን በዝምታ የደገፉት!
ዝምታ እንዴት ድጋፍ ይባላል? ከተባለ: ይህን እንላለን— የተጭበረበረውን (የድራማውን ሰለባ) ድምበር ባለፈ መልኩ እየተቃወሙ ይህኛውን (አጭበርባሪውን) በትንሹ (በስሱ) እንኳን አልተቃወሙም!
የሞገርመው ነገር ደግሞ: ሁለት ግለሰቦች የተፈተኑበትን ጉዳይ የበርካቶች ፣ የአለም ጀምዒያዎች ጉዳይ አስመስለው ለማቅረብ አላህን አለመፍራታቸው ነው!! إذا لم تستحي فاصنع ما شئت
ካላፈርክ "የማታፍር ከሆነ ያሻህን ስራ" ነው ነገሩ!
ሌላኛውን የዚህ ድራማ አካል ( ድራማው የተሰራበትን አካል) ስንመለከት በርካታ ብልሹ ነገሮችን እየሰማ ያለ ምንም ማስተባባል በዝምታ ማለፉ አንዳንዴም እነዚህን ብልሹ ነገሮ ች መጋራቱ በጅጉ የሚያስወቅሰው ሆኖ ታየኝ!
ለተቀጠረላቸውም የዱንያ ምናምንቴ ተገቢ ያልሆነን ዝንባሌ አሳይተው ያሉትን አሉ። የተሰማው ድምፅ የተጭበረበረ ነው እስካልተባለ ድረስ አደጋን አይተናል።
ከነዚህ ነገሮቻቸውም እንዲመለሱ መካሪ ቢኖር መልካም ነው! ከጥፋቶቻቸው እንደሚለሱ መጠቆምም ተገቢ ነው ብየ አምናለሁ! እነሱን በዚህ ጉዳይ ብቻ ከሱ ማስወጣቱን ግን ጠርዘኞቹ ብቻ የሚዳፈሩት የፈንጅ ወረዳ ነው!። አንድን ሙስሊም ከሱና ማውጣት አደገኛ ነውና— ኢማሙ አሕመድና ሌሎች ኡለሞቻችን እንደሚሉት።
አላህ ይምራን!