ይገርማል?
መልክተኞች ሁሉ የተላኩት በሽርክ ጨለማዎች ውስጥ የተዘፈቁትን ህዝቦች ወደ ተውሒድ ብርሃን በአላህ ፍቃድ ለመምራት ነበር፡፡ መልክተኞችን የተከተሉ የእውቀት ባለቤቶችም በዚሁ በመልክተኞች ፋና ላይ ነበር የተጓዙት፡፡
ዛሬ በተገላቢጦሹ አላህ ካዘነላቸው ጥቂት የነብያት ተከታዬች ውጭ፣ የነብያትን ፈለግ ተቃርነው የሚከተሉት ከባባድ ሽርክ ጨለማዎች እና ተግባሮች አገራችንም ላይ ይሁን አለም ላይ እያሉ እነሱ ወደ ሌላ አርስት የሚጣሩ በጣም ብዙ አሉ፡፡
እስቲ ምን ይሆኑ እነዚህ ሽርኮች፡፡ በአላህ ፍቃድ አገራችን ላይ ካለው ሽርክ ዘልዬ አልወጣም፡፡
- ነጃሺ ቀብር ላይ የሚሰራው አስፀያፊ ሽርክ፣
- ጎንደር ላይ የሚመለከው “የአሊ ጎንደር” ቀብር፣ አባድር…..
- ጎጃም ላይ “እኔ ኢንቨስተር እንጂ ሸህ አደለሁም” ያለውን ሸህ አስራት ማምለክ፣
- ጎጃም አዴት “ለውሻ” የሚፈፀመው አመታዊ እርድ፣
- ጎጃም ዳንግላ…..
- ጎጃም ቲጃኒያ….
- ወሎ “የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ”፣
- ወሎ ሌሎች ብዙ ቦታዎች ላይ ሽርክ…...፣
- ቡሬ የቲጃንዩ ሸህ……
- አዲስ አበባ ጉለሌ እስላም መቃብር….፣
- አዲስ አበባ ብዙ ጠንቋይ ቤቶች…..
- በጉራጌ “ቃጥባሬ”፣ “አብሬት”….
- በስልጤ “አልከሶ”…
- ድሬ ባሌ ኑር ሁሴን….
- አባድር በሃረር….
እና የመሳሰሉትን፡፡ እዚህ ጋር የጠቀስኳቸው ቀብራቸው ላይ ጠዋፍ የሚደረግ፣ ከአላህ ውጭ ድረሱልን እየተባሉ የሚጠሩ፣ ስለት የሚገባላቸው፣ መውሊድ እየተባለ ባወጡት ቀን የሚከበርላቸው እና የመሳሰለውን ነው፡፡
አሳዛኙ ብዙ ዱዐቶች እነዚህ ሁሉ ሽርክ ከሚሰሩባቸው ክፍለ ሀገራት ነው ተወልደው ያደጉት፡፡ የመጀመርያ ጥሪያቸውም ተውሒድ ነበር መሆን የነበረበት፡፡ ግን እነሱ አደራቸውን በልተው ተውሒድ ካልተስተካከል ምንም ጥቅም የሌላቸውን አርስቶች ሲደጋግሙ ይታያሉ፡፡
መንዙማ እየተባለ
- “ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ”፣
- “ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ መዲና ና ይበሉኝ”፣
አረ ስንት ማለት ይቻላል፡፡ እነዚህ ለምሳሌ በቂ ናቸው፡፡ አንዱ ሽርክ ስራዎችን ሁሉ አፈር ከድሜ ለማስገባት በቂ ነው፡፡ ተመልከቱ ህያው አላህን ትተው በሞቱት ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲመኩ፡፡
አላህ ግን እንዲህ ብሎን ሲያበቃ
وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦ ۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا
በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ (አላህ) ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡

ሌላው ይህን ምድር በብቸኝነት የሚያስተናብረው አላህ ሆኖ ሳለ አላህን ትተው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) “መዲና ና ይበሉኝ” ብለው ይጠይቃሉ፡፡
አሳዛኙ ግን አብዛኛዎቹ ዱዐት የተባሉት ሰዎች አይደለም ይህን ሽርክ ሊቃወሙና፣ የእንደዚህ አይነት ሽርክ አቀንቃኞችን ቻናላቸው ላይ የኢድ ባዕል “እንግዳ” አድርገው ያቀርባሉ፡፡
ሱብሃነላህ፡፡ አላህ እኛንም እነሱንም ይምራን፡፡
ታድያ ይህ ሁሉ ሽርክ የሚፈፀምበት አገር ላይ ተቀምጦ ተውሒድን ማስተማር ሲገባ ከዚህ አርስት ውጭ ሌላን አርስት መተንፈሱን ምን አመጣው?
እውነት ለኡማው ታስቦ ነውን?
ለኡማው እማ ከአላህ እና ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የበለጠ ያዘነለት የለም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሽርክን አስጠንቅቀው ወደ ተውሒድ ተጣርተው ነበር ዳእዋቸውን የከፈቱት፣ በዛም ላይ የሞቱት፡፡
አሳዛኙ የነብዩላህ ኑሕ (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች የጠፉት በሽርክ ሰበብ ነበር፡፡ ዛሬ አብዛኛው ዘንድ ይህን ሁሉ ሽርክ፣ ቢድዐ፣ ፍልስፍና እና ወንጀሎች ተሸክሞ “ድል ናፈቀን” እና የመሳሰለውን ቃል ከአፋቸው ሲያወጡ፣ እነዚህ ሰዎች አእምሮዋቸው ይሰራል ወይ? ያስብላል፡፡ ምክንያቱም መጀመርያ ይህን የሚያክል ሽርክ ፊት ለፊታችን አፍጥጦ ተቀምጦ እሱን ከመዋጋት ይልቅ አድበስብሰው እያለፉ ከዛም “ነስሩ ቅርብ ነው” እያለ በየሶሻል ሚድያው እና በየመድረኩ የሚደሰኩር ሳይ ግርም ይለኝል፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለ “ድል” አያውቁም ወይ?
ከሽርክ እና ከቢድዐ ፀድቶ በተውሒድ እና ሱና ላይ ከመኖር የበለጠ ምን ድል አለ?
እስቲ ይህችን ነጥብ ልብ እንበል፡፡ አላህ እዝነቱ ካፊሩንም አማኙንም፣ ሙናፊቁንም ሙኽሊሱንም፣ ሱንዩንም ሙብተዲውንም፣ እንስሳውንም ያጠቃለለ ነው፡፡ ድልን ግን ከሸርጥ ጋር ነው ያደረገው፡፡ ተውሒዳቸውን አሟልተው የኖሩ ሰዎች በዱንያ ላይ መመራት አላቸው፣ በአኸይራ ላይ ደህንነት አለላቸው፡፡ ከእሳት ተጠብቀው ጀነት ይገባሉ፡፡ አላህ ከነሱ ያድርገን፡፡
ሽርክ እና ቢድዐን አዝሎ ሌላ ነገር ማውራት እብደት፣ ድንቁርና፣ መሃይምነት ነው፡፡
አላህ መመልከቻ ልቦና ይስጠን፡፡