ምቀኝነት የመጀመሪያው አላህ የታመፀመበት ወንጀል ነው፡፡ ጌታችን አላህ “ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት
እንዳትሰግድ ምን ከለከለህ? ኮራህ? ወይስ ከትእቢተኞቹ ሆንክ?” ሲለው የሰጠው መልስ ያገጠጠ ምቀኝነት ነበር፡፡
“እኔ ከርሱ (ከኣደም) በላጭ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው!” ነበር ያለው፡፡ [ሳድ፡
75-76]
ምቀኝነት ጥንታዊ በሽታ ነው፡፡ የአባታችን አደም ልጅ ቃቢል ወንድሙን ሃቢልን የገደለው በምቀኝነት ምክንያት ነው፡፡ ዩሱፍን ወንድሞቻቸው ከውሃ ጉድጓድ የጣሏቸው በምቀኝነት ተነሳስተው ነው፡፡ “ዩሱፍና ወንድሙ ወደ አባታችን ዘንድ ከኛ ይበልጥ የተወደዱ ናቸው” በሚል መነሻ፡፡ [ዩሱፍ፡ 8] አይሁዶች የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነብይነት ለመቀበል “አሻፈረን” ያሉት በምቀኝነት ሰበብ ነው፡፡ ከኛ ዘር ሳይሆን ከዐረብ ሆኖ በሚል መነሻ፡፡ የመካ አጋሪዎች የሙሐመድን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነብይነት ለመቀበል የዘጋቸው ቀዳሚው ምክንያት ምቀኝነት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- “ይህም ቁርኣን ከሁለቱ ከተሞች በታላቅ ሰው ላይ አይወረድም ኖሯልን?” አሉ፡፡ እነሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን?! እኛ በቅርቢቱ ህይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል፡፡ ከፊላቸውም ከፊሉን ሰራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች አስበለጥን፡፡ የጌታህም ፀጋ ከሚሰበስቡት በላጭ ናት፡፡” [አዝዙሕሩፍ፡ 31-32]
የመፃህፍቱ ሰዎች በሙስሊሞች ላይ ለሚያደርሱት ሁሉ ቀዳሚው ምክንያት ምቀኝነት ነው፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ከመፅሀፉ ባለቤቶች ብዙዎቹ እውነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በሆነው ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሃዲዎች አድርገው ሊመልሷችሁ ተመኙ፡፡” [አልበቀራህ፡ 109]
ምቀኝነት የአላህን ውሳኔ መፃረር ነው፡፡ አላህ ለፈለገው ይሰጣል፣ ከፈለገው ይነሳል፡፡ አንድን አካል አላህ በሆነ መልኩ ፀጋውን ከዋለለት በኋላ በዚያ ላይ ቂም ማርገዝ፣ በክፋት መመልከት የሰጪውን ጌታ ውሳኔ በይሁንታ አለመቀበል ነው፡፡ ምቀኛ ውስጡን ያቃጥላል እንጂ ምንም ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ ምቀኛ በማያገባው ገብቶ ሲብከነከን በከንቱ እራሱን ያቃጥላል፡፡ እውነት ለመናገር እንዲያውም ምቀኝነት ፍትሃዊ በሽታ ነው፡፡ በብዛት ከሚመቀኙት አካል ይልቅ ምቀኛውን እራሱን ነው ይበልጥ የሚጎዳው፡፡
ምቀኛ ሰው ሲበዛ የሚደንቅ ነው፡፡ ከራሱ ማግኘት ይልቅ የሚያሳስበው የጓደኛው ማጣት ነው፡፡ ምቀኛ እንግዳ የሆነ ፍጡር ነው፡፡ የሚደርስብህን ወይም ያለብህን ብዙ ችግር ችላ ብሎ ያለችህ ጥቂት መልካም ላይ የክፋት አይኑን ይጥልብሃል፡፡ ደግነቱ በብዛት ውስጡን የሚያቃጥለው፣ በሀሳብ የሚያብከነክነው እራሱን ነው፡፡
ምቀኛ ሰው ሴረኛ ነው!! ከወንድሙ ላይ ያለውን ፀጋ ለማጥፋት ብዙ ይዳክራል፡፡ ምቀኛ ሰው አታላይ ነው፡፡ ምቀኝነቱ እንዳይታወቅበት የሚመቃኘውን አካል ህፀፅ እየለቀመ አቃቂር እያወጣ ሊጎዳው፣ ሊያሳጣው፣ ሊተናኮለው ይሞክራል፡፡ የሚመቃኘው አካል ዘንድ ያለው ወንጀል አላህ ለሱ መልካም መዋሉ ነው፡፡ አለቀ፡፡ ነገር ግን አቶ ምቀኛ ምቀኝነቱ እንዲታወቅ አይሻምና ለጥፋቱ የተለያዩ ሽፋኖችን ይሰጣል፡፡ በጣም የሚያስጠላው ደግሞ ለዲን ለኢስላም በመቆርቆር ስም የሚፈፀም ምቀኝነት ነው፡፡ ይሄ ድርብ የሆነ አስቀያሚ ጥፋት ነው፡፡ ምቀኝነቱ ብቻውን በቂ ጥፋት ነበር፡፡ ኢስላማዊ ሽፋት ሲሰጠው ደግሞ ሌላ ሸፍጥ ታክሎበታል፡፡ ይሄ እንግዲህ ሰፋ ሲል ነው፡፡ ጠበብ ብሎ ደግሞ በሱንና በሰለፍያ ስም የሚፈፀሙ ምቀኝነቶች በሽ ናቸው፡፡ እዚህም ላይ ከሰለፍዮች መሀል የተንሰራፋ ብዙ ችግር አለ፡፡ ልብ በሉልኝ! አላማዬ “ማንንም መውቀስ አይደለም” እያልኩ ዳር ዳሩን መሄድ አልፈልግም፡፡ አላማዬ በተጨባጭ የሚመለከተውን አካል መውቀስ ነውና፡፡ በመካከላቸው የሚገኙ ከባባድ ጥፋቶችን ከቡድን አጋራቸው ስለመጣ ብቻ እንዳላዩ እያለፉ ለሌሎች አቃቂር የሚያወጡት የስሜት ተከታዮች ናቸው፡፡ በሱንና ስም የምቀኝነት ፈረስ የሚጋልብ ብዙ ሰው አለ፡፡ ከሱ ወይም ከወዳጁ ቢመጣ የማይቃወመውን ነገር ከማይወደው አካል ስለመጣ ብቻ መቃወም ምቀኝነት ካልሆነ ምን ሊባል ነው?!! ከጓደኛው ቢወጣ የማይቃወመውን ነገር ከሌላ ስለመጣ ብቻ መቃወም ምን ማለት ነው?! አላህ ስሜትን ከመከተል ይጠብቀን፡፡ በ “ቃለላህ” እና በ “ቃለ ረሱሉላህ” ሽፋን ምቀኝነታቸውን ሊሸፍኑ አጉል የሚታገሉ የዋሆችን በተጨባጭ እየተመለከትን ነው፡፡ በሱንና ዑለማዎች ስም የምቀኝነት ገበያቸውን የሚያሟሙቁ ሰዎች ይሄው ብርቅ አይደሉም ዛሬ፡፡ ዛሬ ላይ በምቀኝነት መንሰኤ እየተለያዩ ልዩነታቸውን ዲናዊ ሽፋን የሚሰጡ ወንድማማቾች በተጨባጭ ያጋጥማሉ፡፡ ብቻ በየዘርፉ የበዛውን ምቀኝነት ስንመለከት ቆም ብለን ወደ ውስጥ እንድንመለከት ደወል ሊሆነን ይገባል፡፡ ስለዚህ አላማዬ እራሴን ጨምሮ ወንድም እህቶች በሙሉ ውስጣችንን እንድንፈትሽ ማስታወስ ነው፡፡ መቼም ከዚህ ክፉ በሽታ የሚተርፍ ሰው ማገኘት አዳጋች ነው፡፡ ልዩነቱ ውስጥን ከማሸነፍ ወይም ስሜትን ከማስተናገድ ላይ ነው፡፡ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ነገር ግን (ምቀኝነትን) እርኩሱ ግልፅ ሲያወጣው ክቡሩ ግን አምቆ በመያዝ ይሰውረዋል፡፡” [አልመጅሙዕ፡ 10/124]
ምቀኝነት ከአማኝ የማይጠበቅ ቆሻሻ ባህሪ ነው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “በአንድ አማኝ ባሪያ ሆድ ውስጥ ኢማን እና ምቀኝነት ባንድ ላይ አይሰባሰቡም!!” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7616]
ምቀኝነት የኸይር ስራ ሁሉ ፀር ነው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምቀኝነት “ምላጭ ነው! ፀጉርን ይላጫል ማለቴ አይደለም። ይልቁንም ዲንን ይላጫል!!” ይላሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3361]
ከምቀኞች ምቀኝነት እተርፋለሁ ብለህ ነፍስህን እንዳታስከጅላት፡፡ የማይሆን ነገር እየተመኘህ አጉል አትባዝን፡፡ በተለይ ደግሞ ሰዎች ዘንድ የሌለ የሆነ ኒዕማ አላህ ከዋለልህ ያለጥርጥር ምቀኛህ ይበዛል፡፡ ስለዚህ ሌሎች ዘንድ ካለው የሚበልጥ ሀብት፣ ስልጣን፣ እውቀት፣ ተሰሚነት፣ ከሰዎች ዘንድ መወደድ፣ ውበት፣ ቁንጅና፣ ታዋቂነት፣ ወዘተ ከኖረህ ያለጥርጥር ምቀኛህ ይበዛል፡፡ ቀታዳህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “በሰዎች ላይ ፀጋዎች አይበረክቱም፣ ጠላቶቻቸው የሚበረክቱ ቢሆን እንጂ፡፡” [አልዒለል ሊልኢማም አሕመድ፡ 116]
እራስን ከምቀኝነት ማፅጃ መንገዶች
- ሞትን ማስታወስ፡፡ የዱንያን ለዛ ቆራጭ የሆነውን ሞትን የሚያስታውስ ሰው ለወንድሙ ክፋት የሚያስብበት ድፍረት አያገኝም፡፡
- የአላህን ውሳኔ መውደድ፡፡ አንዱን ድሃ አንዱን ሀብታም፣ አንዱን ቆንጆ አንዱን ፉንጋ፣ አንዱን አዋቂ አንዱን መሀይም፣ አንዱን ደረቅ፣ አንዱን ልዝብ፣ አንዱን አንደበተ ርቱእ፣ አንዱን ልጉም፣… ያደረገው ሁሉን ቻዩ ጠቢቡ አላህ ነው፡፡ ሰዎች በምርጫቸው ብቻ አይደለም ከሌላው የሚበልጡት፡፡ ስለሆነም ሰዎችን ስለያዙት ፀጋ መመቅኘት በዚህ መልኩ ፀጋዎችን የከፋፈለውን ጌታ ውሳኔ መፃረር ነው፡፡ ይህን ከግምት ያስገባ ሰው ከምቀኝነት ክፉ ቫይረስ እራሱን ይጠብቃል፡፡ ከውስጡ እሳቱ ቢቀጣጠል እንኳን ስሜቱን ረግጦ ይይዛል፡፡
- የዱንያን ርካሽነት፣ ዝቃጭነት መረዳት
- ለአማኞች መልካምን ማሰብ፣…
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 24/2008)