Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የወንጀል መዘዝ

የወንጀል መዘዝ
•••••••🔄•••••••
ማንንም ከመውቀሳችን በፊት ራሳችንን እንመልከት
ጌታችን አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ
[وَمَا أَصَابَكُمْ مِنْ مُصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ]
«ከአደጋዎች ማንኛዋም አደጋ የምትደርስባችሁ በገዛ እጃችሁ በሰራችሁት ነው።» በማለት በሰራነው ጣጣ ለዱንያዊ መከራም እንደምንዳረግ በግልፅ ነግሮናልና ጠንቀቅ ይበጃል።

ስለዚህ ኑሯችንን የሚያናጋው ቤታችን የሚያምሰው ወንጀላችን ቢሆንስ ? እንደ ደጋጎቹ አስተውለናልን ! ?
قال الفُــضيل بن عياض -رحِــمُه الله-:
«እኔ አላህን ያመፅኩ እንደሆን፣ የወንጀሌን ነፀብራቅ በአህያዬ፣ በአገልጋዬና በባለቤቴ ባህሪ እንዲሁም በቤቴ አይጥ የባህሪ ለውጥ አውቃለሁኝ።» ይላሉ
⚂ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሂመሁላህ
📚(البداية والنهاية) (10/215)
ሀቅ ነው አብዛኞቻችን ጣቶቻችንን የምንቀስረው በሌላው ላይ ስለሆነ ጥፋታችን አይታየንምና በየደቂቃው ኪሶቻችንን እንደምንፈትሸው ሁሉ ተግባሮቻችንም ተራ ይድረሳቸዋ
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
በተለይ ወላጆቻችንን ባናሳዝን መልካም ነው። ካለፉም ለሀቃቸው እንታገል። ከሠለፎች
قال أبــو الحسن القطان -رحِــمُه الله- :
«ዐይኔ ላይ አደጋ ደረሰብኝ። ሐዲስና ዒልምን ፍለጋ ከእናቴ በተለየኋት ግዜያት ስለኔ ታለቅስ ነበርና ከሷ ለቅሶ ብዛት የተነሳ እንደተቀጣሁ እገምታለሁ።» ይሉ ነበር
⚂አቡል ሀሰን አልቀጣን ረሂመሁላህ
📚(معجم الأدباء) ( 12 / 220)
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
ስለዚህም ወደ ሃኪም ሳንሮጥ ራሳችንን እንመርምር
قال الضحاك -رحِــمُه الله- :
ደሃክ ኢብን መዛሂም ረሂመሁላህ
«አንድ ሰው በፈፀመው ወንጀል ካልሆነ በስተቀር ቁርኣንን ከተማረ በኋላ አይረሳውም። ካሉ በኋላ “ከአደጋዎች ማንኛዋም አደጋ የምትደርስባችሁ በገዛ እጃችሁ በሰራችሁት (ጥፋት) ነው።” የሚለውን የአላህ ቃል አነበቡ። ከዚያም "ቁርኣንን ከመርሳት የባሰ ምን ሙሲባ ኣለ ?!"» ኣሉ።
📚(الجامع لأحكام القرآن)(16/30)
ተመልከት በኃጢኣትህ መነባበር የተነሳ ለዱንያም ለኣኺራም ታላቁ ሃብትህን በቀላሉ ታጣለህ
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
ብዙውን ግዜ እያጠፋንም እንታለፋለን። ግን ወዲያው ኣለመቀጣታችን እንዳያዘናጋን፣ ለነገ ክፉ ስንቅ ሆኖ ይጠብቀናልና ከወዲሁ ተውበት እናድርግ።
አል አልላማ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ “አንድ ግለሰብ በሆነ በሽታ ወይም ክፉ የሆነ ሌላ ነገር በህይወቱም ሆነ በንብረቱ ላይ ደርሶበት ቢፈተን ይህ ነገር የፈተና መከራ መሆኑን ወይም ከአላህ ዘንድ የመጣበት ቁጣው መሆኑን እንዴት ሊያውቀው ይችላል? ” ተብለው ተጠየቁና ቀጣዩን ጥበባዊ ምላሽ ሰጡ
الجَـــ☟ـــوَابُ:
⚄«አላህ ባሮቹን በደስታም በጉዳትም በጭንቅም በምቾትም ይፈትናቸዋል። ልክ ለነቢያቱ አለይሂሙ ሰላቱ ወሰላም እና ለደጋግ ባሮቹ እንዳደረገው ደረጃቸውን ከፍ ሊያደርግላቸው፣ ዝናቸውን አጉልቶ ሊያወሳቸውና መልካም ምንዳቸውን ሊያነባብርላቸው ሲል በእርግጥም ይፈትናቸዋል። ይህም ነቢዩ ﷺ
«أشد الناس بلاء الأنبياء ثم الأمثل فالأمثل »
“ከሰዎች መካከል ፈተና የሚጠናባቸው ነቢያት ሲሆን ከዚያም አምሳያዎቻቸውን፣ አምሳያዎቻቸውን” እያለ በየደረጃው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ይህን መከራ እንከን አልባው አምላካችን አላህ በኃጢኣትና በወንጀል ሰበብ ያደርሳል። ይህም ልክ “ከአደጋዎች ማንኛወዋም አደጋ የምትደርስባችሁ በገዛ እጃችሁ በሰራችሁት (ጥፋት) ነው።” ብሎ አላህ ሱብሃነሁ እንደተናገረው እዚህቹ ምድር ላይ ሳለን የምንቀጣባት ትሆናለች።
በአብዛኛው የሰው ልጅ ላይ የሚስተዋለው ግዴታውን ያለመወጣት ጉድለቱ ነው። የደረሰበት አደጋም በወንጀሉና የአላህን ትእዛዛት ካለመፈፀሙ ጉድለቱ የተነሳ ነው።
ከአላህ መልካም ባሮች መካከል በበሽታና በመሳሰለው ነገር አንዳቸው የተፈተኑ እንደሆነ ግን ይህ ልክ ለነቢያቱና ለመልእክተኞቹ ደረጃቸውን ይበልጥ ከፍ ለማድረግና ምንዳቸውንም እጅግ የበዛ ለማድረግ እንዲሁም በትዕግስታቸውና ከአላህ ምንዳን ከመተሳሰብ አንፃር ለሌሎቹም አርዓያ እንዲሆኑ በነሱ ላይ እንደ ደረሰው ፈተና ብጤ መሆኑ ነው።
በአጠቃላይ የሚደርሱት መከራዎች ልክ ነቢያቱና አንዳንድ ደጋግ ባሮቹ ላይ እንደደረሰው ደረጃዎችን ከፍ ለማድረግና ምንዳዎችንም ለማብዛት ሲሆን በአንፃሩም አላህ { مَن يَعْمَلْ سُوءًا يُجْزَ بِهِْ } “መጥፎን የሰራ ዋጋውን ያገኝበታል” እንዳለው ኃጢኣትን ለማበስም ይሆናል። ነቢዩም ﷺ
« ما أصاب المسلم من هم ولا غم ولا نصب ولا وصب ولا حزن ولا أذى إلا كفر الله به من خطاياه حتى الشوكة يشاكها »
“ሙስሊሙ ላይ አስጨናቂም ሆነ አሳሳቢ፣ አድካሚም ሆነ አንከራታች፣ አሳዛኝ ሆነ ሌላ ጎጂ ነገር ቢደርስበት በተወጋው እሾህ እንኳ ቢሆን በዚህ ሰበብ ኃጢኣቱን አላህ ሳያብስለት አይቀርም።” ብለዋል።
በሌላም ሀዲሳቸው ﷺ
« من يرد الله به خيرا يصب منه »
“አላህ መልካም የሻለትን ሰው ፈተናን ያደርስበታል።” ብለዋል።
በሌላም ሀዲሳቸው ـﷺـ
« إذا أراد الله بعبده الخير عجّل له العقوبة في الدنيا وإذا أراد الله بعبده الشر أمسك عنه بذنبه حتى يوافي به يوم القيامة » خرّجه الترمذي وحسنه 》.
“አላህ ለባርያው መልካምን ሲሻለት በዱንያ ላይ እንዲቀጣ ቀደም ያደርግለታል። በባርያው ላይ ሸርን ሲፈልግ ግን በወንጀሉ እንዲቀጣበት የትንሳዔዋ እለት ድረስ ያቆየዋል።” ባሉት መሰረትም በኃጢኣት ሰበብና ለተውበት ካለመፋጠን የተነሳ አፋጣኝ የሆነ የመከራ ቅጣት ሊደርስ ይችላል።»⚄
ብለዋል ረሂመሁላህ።
📚 [مجموع فتاواه] ( ٤/٣٧٠-٣٧١)
ስለሆነም ወንድም እህቶቼ ባለንበት ሁኔታ እኔ ልክ ነኝ፣ እኛ ልክ ነን ብቻ እያልን ከመኩራራት እንጠበቅ። ራሳችንን ዘንግተን የሰው ጓዳን ከመዳሰስም እንራቅ። ላጠፋነው ኢስቲግፋርና ተውበት አይለየን። በመላው የሙስሊሙ ዓለም የሚስተዋለው እልቂት፣ ቸነፈር፣ ውድቀትና ውድመትም ያለ ምክንያት አይምሰለን። والله اعلم
የኃጢኣት መዘዝ ከባድ ነውና አላህ ይጠብቀን።

✏Abufewzan
20/02/1438
20/11/2016