Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለተወሰኑ የጥመት ቡድኖች መጠን ያለ እይታ (የመጨረሻው ክፍል 4 «አልከራሚይያህ» እና «አስሳለሚይያህ» )

ስለተወሰኑ የጥመት ቡድኖች መጠን ያለ እይታ
(የመጨረሻው ክፍል 4 «አልከራሚይያህ» እና «አስሳለሚይያህ» )
ጸሐፊ፡ አልኢማም ሙሐመድ ቢን አልዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸው)
ምንጭ፡ የኢብን ቁዳማህ “ሉምዐቱል-ኢዕቲቃድ” ማብራሪያቸው ላይ
(ገጽ 163)

7. «አልከራሚይያህ»
�ሙሐመድ ቢን ከራም የተባለ ግለሰብ ተከታይ ናቸው። በ225 ዓ.ሂ ሞቷል። (በአላህ ስሞች እና ባህሪያት ላይ) “ተሽቢህ” (አላህን ከፍጡር ማመሳሰል) እና የ’’ኢርጃእ’’ እምነትን የያዙ ናቸው። በበርካታ አንጃዎች ተከፋፍለዋል።
8. «አስሳለሚይያህ»
ኢብን ሳሊም የተባለ ግለሰብ ተከታዮች ናቸው። (በአላህ ስሞች እና ባህሪያት ላይ ያላቸው እይታ “ተሽቢህ” (አላህን ከፍጡር ማመሳሰል) ነው።
��በጸሐፊው የተገለጹት እነዚህ ቡድኖች ሲሆኑ ቀጥለውም “እናም እነዚህን መሰል ሌሎች ቡድኖች” ብለው ገልጸዋቸዋል። ልክ እንደ የአቡል፡ሐሰን ቢን ኢስማዒል አልአሽዐሪ ተከታዮች የሆኑትን ‘’አሽዐሪይያህ’’ አንጃን ይመስል። በመጀመሪያ (አቡል፡ሐሰን) ወደ ሙዕተዚላ አቋም ያዘነበሉ ነበሩ። አርባ ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ። ቀጥሎ በአደባባይ (በኹጥባ ሚንበራቸው ላይ) ከነበሩበት አቋም እንደወጡና ንስሃ እንደገቡ ገልጸው የሙዕተዚላን አካሄድ ባጢልነት (ከንቱነት፥ ሐሰትነት) አጋለጠው የአህሉልሱንናህን አካሄድ ማራመድ ጀመሩ። አላህ ይዘንላቸውና።
ራሳቸውን ወደርሳቸው የሚያስጠጉት ሰዎች (‘’አሽዐሪይ ነን’’ የሚሉት) (ከአቡል፡ሐሰን የፍጻሜ አካሄድ የወጣ) በሌላ ጎዳና ላይ የሚሄዱ ናቸው። አካሄዳቸው ‘’አሽዐሪያ’’ በመባል ይታወቃል። እነርሱም ከአላህ ባህሪያት ውስጥ ሰባቱን ብቻ የሚያጸድቁ ሲሆን አእምሯችን (እነዚህ ሰባቱን ብቻ እንድንቀበል) አረጋግጦልናል ብለው ቀሪዎቹን ባህሪያት ግን ትርጉማቸውን (ከነርሱ አስተሳሰብ ጋር እንዲሄድላቸው ብለው) ያጣምማሉ። ሰባቱ የሚያጸድቋቸው ባህሪያት በሚከተሉት ስንኞች ተገልጸዋል. .
حي عليم قدير والكلام له إرادة وكذاك السمع والبصر
እርሱ ዘውታሪ፤ ዐዋቂ፤ ቻይ እና ንግግርም ያለው
ፍላጎትም እንዲሁ ሰሚም ተመልካችም ነው።
በከላም፥ በቀደር እና በሌሎቹም ባህሪያት ላይ ሌላም ቢድዓ አለባቸው።
------------
��በዚህ ርእስ ዙሪያ የተጻፈው እዚህ ጋር ያበቃል።
�አላህ ባነበብነው የምንጠቀም ያድርገን �