አጭር ወንድማዊ ምክር ለሙስሊም ተመራቂ ተማሪዎች!
እንኳን ደስ አላችሁ!
ውድ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ተመራቂ የሆናቹ ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ!
በመጀመሪያ ለረጅም ዓመታት ስትለፉለት የነበረውን የድካም ፍሬ ለመቅመስ ስላበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ልላችሁ እወዳለሁ! ይህን ደረጃ ለመድረስ የበቃችሁት ከብዙ ድካምና ልፋት እንዲሁም የመንፈስ ጽናት በኋላ መሆኑ እንደ ቀጥር ፀሀይ ፍንትው ያለ እውነታ ነው፡፡ ይሁንና ለዚህ እንድትበቁ የረዳችሁ ሀያሉ አምላካችን አላህ ነውና ማመስገን እንዳትዘነጉ አደራ እላለሁ፡፡
የጥረት ዉጤት ለፍሬ ሲበቃ እጥፍ ደስታን እንደሚፈጥር ግልጽ ነው፡፡ ከመልካም ፀጋዎቹ ጨምሮ ለሁላችንም እንዲሰጠን አላህን እንማፀነዋለን፡፡
እንደመግቢያ ይህን ካልኩ ወደ መልዕክቴ ገባሁ…
ውድ ተመራቂዎ ወንድምና እህቼ!
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا [١٧:٢٣]
"ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡" (አል ኢስራእ፡23)
ከምንም በላይ አሏህ በእኛ ላይ ከጣላቸው ሐቆች ሁሉ ትልቁ አጋንንትንና የሰው ልጆችን የፈጠረበት ፣ መልዕክተኞች የላከበት ፣ ሰማያዊ መፅሀፍትን ያወረደበት እርሱን በብቸኝነት ማምለክ ተውሒድ ነው! ከዚህም ቀጥሎ በላጩ ወይም በቀዳሚነት ሊገለጽ የሚችለው የወላጅ ሐቅ ነው፡፡
አላህ በቁርኣኑ እንዲሁም ረሱልﷺ በሐዲሳቸው በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጠቅሰዋቸዋል፡፡ ገና ከተፀነስንበት ቀን ጀምሮ የወላጆቻችን እንዲሁም የቤተሰቦቻችን እንክብካቤና ድጋፍ ቀላል እንዳልሆነ ከሁላችንም የተሰወረ ጉዳይ አይደለም፡፡ በተጨሪም ከአላህ እርዳታ ባሻገር ለዚህ ቀን እንድትበቁ ዘውትር ከጎናችን ሆነው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለፍተዋል፡፡ ለኛ ምቾት እነርሱ ተጎሳቁለው ከሰውነት ተራ ወጥተው ገርጥተው ፣ እኛ ለማጥገብ እነርሱ ተርበው፣ እንድንደሰት ብዙ አንብተው፣ ለኛ እረፍት እንቅልፍ አጥተው መቆየታቸው የማንክደው እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም ለወደፊት በአላህ ፍቃድ ልናሳካው በምንሻው የህይወት እቅዳችን ትልቁ አካል ልናደርጋቸው እዳቸውን መክፈል ባንችልም በጥቂቱም እነርሱን ለማስደሰት ልንጥር ይገባል፡፡
ውድ ተመራቂዎች! ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን ባላየ ካላለፍነው በቀር የኢስላም ጠላቶች ኢስልምን እና ሙስሊሞችን ለማጥፋት ከተለያየ አቅጣጫ በትራቸውን እንደዘረጉ እየተመለከትን ነው፡፡ ይህም አደጋ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አይን አፍጥቶ ጥርስ አግጥጦ እንደመጣ ፤ ሙስሊሞችን ከትክክለኛ እምነታቸው ከተውሒድ ብርሐን ጎዳና ወደ ኩፍር ጭለማ የማስገባት ስራ በአደገኛ ሁኔታ እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ መሆኑ የአደባባ ሚስጥር ነው፡፡ ይህንንም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከጥንትም እንደሚፍጨረጨሩ መንገር ለቀባሪ ሞትን እንደማርዳት ነው፡፡ ስለሆነም ነገ ወጥተን በምንሠማራበት በምንሰራባቸው አካባቢዎች ህብረተሰቡ ዲኑን በአግባቡ እንዲረዳና በእምነቱ ላይ እንዲፀና ራሳችንንን በዒልም በማጠንከር ለማስተማር ቆርጠን ልንነሰ ይገባናል፡፡ ዲናችንን ከተማርና ከተገበርን ከማንም በላይ ስኬታማ እንደምንሆን ጥርጥር የለውም፡፡
ውድ ተመራቂዎች! የሚከተለውንም የአላህ ቃል ሌት ከቀን ዘውትር አስታውሱ፦
《 يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ [٥:٨] 》
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በፍትህ መስካሪዎች ሆናችሁ ለአላህ የምትቆሙ ሁኑ፤ የሰዎችም ጥላቻ ፍትህን እንዳትፈፅሙ እንዳይገፋፋችሁ፤ ፍትህን ተግብሩ፤ ይህ ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፤ አላህንም (ህግጋቱን በማክበር) ተጠንቀቁት፤ አላህ ስለምትሰሩት ሁሉ ወስጠ- አዋቂ ነውና!» [አል-ማኢዳህ 8]
በተሰማራችሁበት የስራ መስክ ስልጣንን ያለ አግባብ ከመጠቀም፣ የስራ ሰዓትን ከማባከን፣ ከማጭበርበር፣ ጉቦ ከመቀበል ፣ አላግባብ ለመበልፀግ ከመጣር ፣ ሰዎችን ከመበደልና መሰል ከሆኑ ኢስላም አምርሮ ከሚቃወማቸው መጥፎ ተግባራት ራሳችንን ልናቅብ ይገባናል፡፡ በተቃራኒው ታማኝነትን ፣ ፍትህን እኩልነትን የመሳሰሉ ኢስላም ያወደሳቸውን ታላላቅ በሃሪዎች ልናንፀባርቅ እውነተኛ ሙስሊምነታችንን በማሳየት ዲናችንን ማስከበርና ሰዎችንም ወደዚህ ውብ ሀይማኖት ልንጠራቸው ይገባል፡፡ በያዝነው ሀላፊነት አላህ ዘንድ እንደምንጠየቅ ለቅፅበት ልንዘነጋው አይገባም!
ኢብኑ ዑመር ባወሩት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛﷺ ይህን ተናግረዋል።
‹‹ሁላችሁም ጠባቂዎች (እረኞች) ናችሁ የጠበቃችሁትንም ነገር ተጠያቂዎች ናችሁ። መሪ በህዝቦቹ ላይ ጠባቂ ነው።ከጠበቀውም ነገር ተጠያቂ ነው።
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ይህን ሁሉ ለማድረግ ደግሞ የሀያሉ አምላካችን አሏህ እርዳታ ያስፈልጋልና ይርዳን፡፡ አሚን፡፡
አበቃሁ!
Hai Ker GC 07
ጁምዓ ረመዳን 12 1437
ሰኔ 10 2008
ተመራቂ ተማሪዎችን SHARE AND TAG በማድረግ የበኩሎን አስተወፅኦ ያድርጉ!