Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰለፎች ከሶላት ጋር የነበራቸው ቁርኝት


 
ሰለፎች ከሶላት ጋር የነበራቸው ቁርኝት
ሰለፎች (ቀደምት ደጋግ አበዎች)- የነቢዩ ሶሀቦች እና ተከታዮቻቸው- ልንከተላቸው የሚገቡ አርአያዎቻችን ናቸው። እኒህ ምርጥ ህዝቦች በየትኛውም የአምልኮ አይነቶች ጠንካራና አምሳያ የሌላቸው ናቸው። ስለዚህ የነሱን ታሪክና ተሞክሮ ማወቁ እጅግ ጠቃሚ ነው። ቀጥሎ የተወሰኑት ከሶላት ጋር የነበራቸውን ቁርኝት እንመለከታለን።
ሰኢድ ኢብን ሙሰየብ ወደ ሰላሳ አመት ያህል በመስጊድ ውስጥ የአንድም ሰው ጀርባ አይተው አያውቁም። ምክንያቱም እሳቸው ሁሌም በመጀመሪያዉ ሶፍ ይሰግዱ ነበርና።
አቡ ሃያን አባቱን ጠቅሶ እንዳስተላለፈዉ፡- ረቢዕ ቢን ኸይሰም በከባድ በሽታ ታሞ ሳለ ወደ መስጊድ እየተጎተተ-እየተመራ- ይወሰድ ነበር። አላህ በቤትህ ዉስጥ እንድትሰግድ የፈቀደልህ ሲሆን ለምን ይህን ያህል ትጨነቃለህ? ተብሎ ሲጠየቅ ሃየ አለ ሶላህ -ወደ ሶላት ኑ- የሚለዉን የሶላት ጥሪ እየሰማሁ እንዴት እተኛለሁ?! በመዳህም ቢሆንም መምጣት ከቻላችሁ እንዳያመልጣችሁ። በማለት መለሰላቸው።
ኢብራሂም አተሚሚ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል፡- የመጀመሪያዉን ተክቢራ-ተክቢረተል ኢህራም- ከመድረስ የሚሰላች ሰው ካያቹህ እሱ ሙናፊቅ ነዉና ከሱ ራቁ።
ሙስዓብ እንዳስተላለፈው፡- አሚር ኢብን አብደላ በነፍስ ተሞ ሳለ አዛን ሰማና ይዛችሁኝ ወደ መስጊድ ዉሰዱኝ አለ። አንተ እኮ በሽተኛ ነህና መሄድ የለብህም ተባለ። የአላህን ጥሪ ሰምቼ ምላሽ መስጠት የለብኝም በማለት በፍጹም አልቀርም አለ። የመግሪብን ሶላት ነበርና እንዲሰግድ ይዘዉት ወደ መስጊድ ሄዱ። አንድ ረከዓ እንደሰገደ እዚያዉ ህይወቱ አለፈ።
ወኪዕ ኢብን ጀራህ እንዲህ ይላል፡- አእመሽ የሰባ አመት አዛዉንት ነዉ። ነገር ግን አንድ ቀንም ተክቢረተል ኢህራም አምልጦት አያዉቅም።
መሃመድ ኢብኑ ሙባረክ እንዳስተላለፈው፡- ሰዒድ ኢብኑ አብዱልአዚዝ የጀምዓ ሶላት ሲያመልጠዉ ያለቅስ ነበር።
ገሳን የወንድሙን ልጅ ጠቅሶ እንዲህ ብሏል፡- አባቴ ተክቢረተል ኢህራም ሲያመልጠዉ አይቼ አላዉቅም።
ዑመር ኢብኑ ኸጣብ አንድ ቀን የአስር ሶላት በጀምዓ ስላመለጠዉ እራሱን በጣም ወቀሰ እና ከፋራ ይሆነው ዘንድ ወደ ሁለት መቶ ሺህ ዲርሃም የሚገመት መሬት ለአላህ ብሎ ሰደቃ ሰጠ።
አብደላህ ኢብኑ ዑመር አንድ የጀምዓ ሶላት ካመለጠዉ÷ የዚያንን ቀን ሙሉ ሌሊት እየሰገደ ያድር ነበር። አንድ ቀን የመግሪብ ሶላት ስለረፈደበት ሁለት ባሪያዎችን ለአላህ ብሎ ነፃ አወጣ።
ኡወይስ አልቀርንይ ዛሬ የሩኩዕ ሌሊት ነዉ ይልና ሌሊቱን ሙሉ በሩኩዕ ያነጋ ነበር። በሚቀጥለዉ ቀን ደግሞ ዛሬ የሱጁድ ቀን ነዉ ይልና ሌሊቱን ሙሉ በሱጁድ ያነጋ ነበር።
አልይ ስለ ነብዩ ባልደረቦች ሲናገር፡- በአላህ እምላለዉ የሙሃመድ ባልደረቦችን የሚያክል በፍፁም አላየሁም። እነሱም ሱጁድና ቂያምን ከማብዛታቸዉ የተነሳ ፀጉራቸዉ የተቆጣጠረና አቡዋራ በአቡዋራ ሆነዉ ያነጉ ነበር።



Sultan Khedir