Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን... ሂጃብ በይርጋ ሃይሌ፤ በኩርቱ፤ በከሊፋ…….


ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን... ሂጃብ

በይርጋ ሃይሌ፤ በኩርቱ፤ በከሊፋ…….

የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹አሁን የማላያቸው ለወደፊት የሚመጡ አሉ፤ የጀነትን ሽታ አያሸቷትም፤ ለብሰው ያለበሱ›› አሉ፡፡

ዛሬ ዛሬ ‹‹ኢስላሚክ እስታይል›› እየተባለ፤ ሴቶች እህቶች የሚለብሱት በጣም አስገራሚ፤ አላህን አይፈሩም ወይ፤ ምንድን ነው ከሌሎች ልብሶች ያለው ልዩነት የሚያስብል ልብሶች ‹‹ኢስላሚክ እስታይል›› የሚባሉ ልብሶች ውስጥ ሲሸጡ ይታያል፡፡

ወገባቸው ጋር ሰፋ ብሎ የመጣውን አባያ፤ ቅርፃቸውን ‹‹8 ቁጥር›› እንደሚሉት ያሳይላቸው ዘንድ ያስጠብቡታል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሆነ አካላታቸውን ለሰዎች ጎልቶ እንዲታይ ከውስጥ እስፖንጅ የሚያደርጉም እንዳሉ፤ ልባችንን ቢከፋው እና ብናዝንም ለመስማት ተገደናል፡፡ እነዚህ ሂጃብ ከመሰሉሽ ሂጃብ አይደሉም፡፡

ቀሚስሽን በእጅሽ ከፍ አድርገሽ ‹‹አሳየው ላላየው፤ አጢንዤ ላላንዤ›› እያልሽ እግርሽን ለአጅነቢ ወንዶች ላሳየሽው ሁሉ ነገ አላህ ፊት ትጠየቂያለሽ፡፡ ዛሬውኑ ቶብች እህቴ፡፡ አረ ይብቃሽ፤ ሂጃብሽን አስተካክይ፤ ውበት ሲለካ ሂጃብ ነው ለካ፡፡

ለአላህ ታማኝ የሆነ ባል የሚገኘውም አላህን በመፍራት እንጂ እንዲህ በየአደባባዩ አላህ የጠላውን ተገላልጦ መሄድ፤ ጥብቅ ብቅ ያለ ልብስ መልበስ፤ ዊግ መቀጠል፤ መነቀስ፤ ቅንድብ መቀንደብ አይደለም፡፡

ይሰመርበት መንገድ ላይ የለከፈሽ ወንድ ለትዳር አይሆንም፡፡ ትዳር ማለት አላህን ፈሪዎች፤ እሱን በመፍራት ብቻ እና ብቻ የሚመሩት የአምልኮ ህይወት ነው፡፡ በተገላቢጦሹ አንቺን ከመንገድ ላይ የለከፈሽ ሌላዋን እንደማይለክፍ በምን ትትማመኛለሽ????

አንተስ ወንድሜ እራሷን ተገላልጣ ንዶችን በንግግሯ እና በተግባሯ የምትጠራ ሴት ላንተ ትሆናለች ብለህ ትገምታለህ????

አረ እህቴ ሆይ! ምን ነካሽ???? የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹እናንተ ሴቶች ሆይ! ጀሃነም ውስጥ በዝታችሁ ተመለከትኳችሁ ብለዋል››፡፡ ተው አላህን ፍሩ! ተው አላህን ፍሩ! ተው አላህን ፍሩ!
አላህን ፍሩ ከማለት ውጭ ሌላ ምን አለን፡፡ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን


Sadat Kemal