ــــــ ــــــ ﷽ ــــــ ــــــ
❁❁ ቅራ/ ቅሪ ❁❁❁❁ አትዘናጋ / አትዘናጊ! ❁❁
ሁለችንንም የሚያስማማ አነድ እውነት አለ እርሱም ወደ ዲናችን መመለስ ለዱኒያም ሆነ ለአኸይራ ስኬት ቁልፍ መሆኑ ነው።
ይህን የስኬት ቁልፍ ማግኘት ደግሞ በሁላችንም ላይ የውዴታ ግዴታ ነው ። የዚህ ቁልፍ ማግኛ ብቸኛው መንገድ ደግሞ እውቀት ብቻ ነው፤ ሸሪዐዊ ዒልም!!! ታዲያ ምን ትጠብቃለህ/ሽ?
ይህን የቁርአን አያ እስካሁን አላነበብክም/ሽም??
« ﻣَﻦْ ﻋَﻤِﻞَ ﺻَﺎﻟِﺤﺎً ﻣِّﻦ ﺫَﻛَﺮٍ ﺃَﻭْ ﺃُﻧﺜَﻰ ﻭَﻫُﻮَ ﻣُﺆْﻣِﻦٌ
ﻓَﻠَﻨُﺤْﻴِﻴَﻦَّﻩُ ﺣَﻴَﺎﺓً ﻃَﻴِّﺒَﺔً ﻭَﻟَﻨَﺠْﺰِﻳَﻦَّﻫُﻢْ ﺃَﺟْﺮَﻫُﻢ
ﺑِﺄَﺣْﺴَﻦِ ﻣَﺎ
ﻛَﺎﻧُﻮﺍْ ﻳَﻌْﻤَﻠُﻮﻥ »
«ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡» [ነህል-97]ኢማሙል ቡኻሪ በሐዲስ ስብስባቸው ውስጥ ፦
«እውቀት ከንግግርም ከተግባርም ይቀድማል» ሲሉ ርዕስ አበጅተዋል። ማስረጃውንም ፦
« ﻓَﺎﻋْﻠَﻢْ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺍﺳْﺘَﻐْﻔِﺮْ ﻟِﺬَﻧﺒِﻚَ ﻭَﻟِﻠْﻤُﺆْﻣِﻨِﻲﻥَ ﻭَﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨَﺎﺕ ِ»
«እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ዕወቅ ስለ ስህተትህም ለምዕመናንና ለምዕመናትም ምሕረትን ለምን» [ሙሐመድ :19]ሲል "እወቅ" ብሎ የጀመረውን የአላህ ቃል አድርገዋል! ሀፊዝ ኢብኑ ሀጀር በዚህ አባባል የተፈለገበት፡-
«እውቀት ለንግግርና ለስራ ትክክለኝነት መስፈርት መሆኑ ነው።…» ብለው ፈትሁል ባሪ ላይ አስፈራዋል!
ከንግርህም ሆነ ከስራ በፊት እውቀት ይቀደማልና ዒልምን ተዋወቀው/ቂው።
፠ ከአንተ/ቺ የሚጠበቀውን ትተገብር ዘንድ ለእውቀት የጎላ ስፍራን ለግስ።
፠ አላህ ጀነትን ያዘጋጀው ለሚታዘዙት ባሮቹ ነውና እርሱን ትታዘዝ/ዢ ዘንድ ትእዛዛቱን ተማር/ሪ።
፠ አላህ ምህረቱን ያዘጋጀው ከከለከላቸው ለሚታቀቡት አማኞች ነውና የከለከለህን/
ሽን በሙሉ ትርቅ/ቂ ዘንድ ወደ ሸሪዐዊ እውቀት ፍጠን/ኚ።
ወደ ቁርአንና ሐዲስ ገስግስ ። ቀናውን ጎዳና ልትይዝ ይከጀላልና።
ነቢዩ ነቢዩ (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«ከነርሱ በኃላ በፍፁም የማትጠሙበትን የሆኑ ሁለት ነገሮችን በመሀከላቹ ትቼ ሄጃለሁ እነሱም የአላህ ኪታብ እና የኔ ሱና ናቸው»
[ኢማሙ አልባኒ ሰሂህ ብለውታል]
አንተ/ቺ በርግጥ አሁን እውቀትን በመገብየት ላይ ነህን? ወይስ ተዘናግተሀል/ሻል?... ጠይብ! ጊዜ የለህም/ሽም??።
አንሞኝ! አጅሬ መች እንደሚመጣ አይታወቅምና ካሁኑ ተዘጋጅ/ጂ። ዛሬውኑ ፤ ለነገ ምንም ዋስትና የለማ!
የእውቀት ማዕዶች በዙሪያህ/ሽ ተጥደዋልና ተሽቀዳደም/ሚ። አላህ ግዴታ ያደረገውን፤ የከለከለውን ከተፈቀደው ለመለየት ቂርአት ብቸኛ መንገድ ነውና ታገሉ።
አልችልም እንዳትል/ትይ፤ ትችላለህና!
« ﺭَﺏِّ ﻫَﺐْ ﻟِﻲ ﺣُﻜْﻤًﺎ ﻭَﺃَﻟْﺤِﻘْﻨِﻲ ﺑِﺎﻟﺼَّﺎﻟِﺤِﻴﻦ » َ
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ስጠኝ ከደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ፡፡»[አል አሹዐራእ 26-83]