Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሊቃውንቶቻችን አንደበት ኢማም አልበርበሃሪ ኣላህ ይዘንላቸውና


ከሊቃውንቶቻችን አንደበት��
ኢማም አልበርበሃሪ ኣላህ ይዘንላቸውና
" ሸርህ አል-ሱን'ና " በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ ባሰፈሩት ላይ እንዲህ ይላሉ :•
“ አንድ ሰው ከቢድዓ የሆነ ነገርን (ሲተገብር) በግልፅ ያሳየህ እንደሆነ፤ ተጠንቀቀው።
☞ ምክንያቱም ካንተ የሸሸገው (ቢድዓ) ግልፅ ካደረገልህ ይብሳልና።»
ሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊም አላህ ይጠብቃቸውና ይህንን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ :–
« የቢድዓ አራማጆችና ስሜታቸውን የሚከተሉ ሰዎች ራሳቸውን በመሸሸግና እንዳይደረስባቸው በመጠንቀቅ የታወቁ ናቸው።
~ የቢድዓ ሰዎች እምነታቸውንም ይሁን አካሄዳቸውን ሙሉውን ግሃድ አያደርጉልህም።
☞ የቢድዓ አራማጆች መርዛቸውን በጥቂት በጥቂቱ እንጂ አይሰጡህም።
ስለ ቢድዓ አራማጆች እንደሚባለው፤
" በቅድሚያ ስትገናኛቸው መርዛቸውን አይሰጡህም። ቀድመው የሚሰጡህ ማር ማሩን ነው።
~ በዚህም መልኩ ይሄድና ስትግባባው ይጋርድብሃል፤ ከዚያም ወደ ቢድዓው ይዘፍቀሃል።
~ ስለዚህ ከሆነ ሰው ላይ ቢድዓን በግልፅ ካገኘህ ጥንቃቄ አድርግ። ምክንያቱም የቢድዓ አራማጆች ሴረኞችና አታላዮች ናቸውና።»
��ምንጭ:
ዓውነል ባሪ (ገጽ 876)].

Sultan Khedir