Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነጃሳን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል!

ነጃሳን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል!

1. ነጃሳው መሬት ወይም ቦታ ላይ ከከሆነ የነጃሳውን እይታ በሚያስወግድ መልኩ አንድ ጊዜ ውሃ ከተደፋበት በቂ ነው፡፡
ለዚህ ማስረጃው ነብዩ (ﷺ) መስጂድ ላይ አንድ የገጠር ሰው ስለሸና ውሃ እንዲፈስበት ማዘዛቸው ነው::

(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. መሬት ላይ ካልሆነና ለምሳሌ ልብስ ወይም ዕቃ ላይ ከሆነ ውሻ አፉን የከተተበት እቃ ሰባት ጊዜ አንዱን በአፈር ቀላቅሎ ማጠብ ሲሆን ማስረጃው፦

ነብዩ (ﷺ)
«እቃችሁ ላይ ውሻ አፉን ከነከረ ሰባት ጊዜ አንዱን በአፈር አድርጋችሁ እጠቡ::»

[ሙስሊም ዘግበውታል]

የነጀሳው ከሆነ ግን ከዑለማዎች አቋሞች ትክክለኛው አንድ ጊዜ ብቻ ነጃሣውን የሚያስወግድ እጥበት ማጠብ ነው፡፡ በመሆኑም ሰባት ጊዜ ማጠብ አያስፈልገውም፡፡ የሽንት የሰገራ የደምና የመሳሰሉት ነጀሳ ከሆነ አንድ ጊዜም ቢሆን በደብም አሽቶ በማጠብና በመጭመቅ እስኪወገድ ድረስ ማፅዳት በቂ ነው፡፡

ምግብ መብላት ያልጀመረ የወንድ ህፃን ልጅ ሽንት ግን ውሃ ላዩ ላይ መርጨት በቂ ነው፡፡ ማስረጃውም፦

«የሴት ህፃን ልጅ ሽንት መታጠብ አለበት የወንድ ህፃን ሽንት ግን ውሃ መርጨት በቂ ነው፡፡»

[አቡዳውድ ነሳኢይና ኢብን ማጃህ ዘግበውታል] የሚለው ሀዲስ ነው::

ከላይ ያሳለፍነው ኡሙ ቀይስ ቢንት ሚህሰን ያስተላለፉትም ሀዲስ ለዚህ ማስረጃ ሊሆን ይችላል፡፡

ስጋው የሚበላ እንስሳ የበክቱን ቆዳ በማልፋት ጦሃራ ማድረግ ይቻላል፡፡
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

«የሞተ እንስሳ ቆዳ በማልፋት ጦሃራ ይሆናል፡፡»

[ነሳኢይ ቲርሚዚይና ኢብኑ ማጃህ ]

የወር አበባ ደም ደግሞ ቆንጥራ ከፈተገችው በኋላ አጥባው ልትሰግድበት ትችላለች፡፡

በጥቅሉ አንድ ሙስሊም ነጃሳን ከቦታ ከአካሉና ከልብሱ በማፅዳት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ለሰላቱ ቅድመ መስፈርት ነው፡፡

‪#‎ፊቅህን_ለመረዳት‬

የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!