ቃና፣ ኢ ቢ ኤስ፣ እና ሌሎችም ኡማውን የሚያደነዝዙ ቻናሎችን ሙስሊሙ ይርቃቸው ዘንድ በአላህ ስም እጠይቃለሁ፡፡
እድሜን አይደለም እንዲህ አይነት አላህ በሚጠላው ነገር፣ ዝም ብሎ ማባከንም አደጋ ነው፡፡
እነ ቃና በሌላ ቋንቋ የተሰሩ እርኩስ ፊልሞችን ወደ አገራችን ቋንቋ ተርጉመው ትውልድን የማደንዘዝ ስራ ነው የሚሰሩት፡፡
የሰው ልጅ እውነተኛ የተግባር ህይወት ነው መኖር ያለበት፡፡ ድራማ፣ ፊልም ለቅዠተኞች፣ ተስፋ ለቆረጡት ነው፡፡ የሩቅ ተጓዥ የሆነ ሰው፣ ቀብር ያለበት ሰው፣ ከነዚህ እርኩስ ቻናሎች እራሱን ያርቃል፡፡
በእስልምና አንድ ነገር በአረብኛ ሀራም ከሆነ ወደ አማርኛ መተርጎሙ ሃላል አያደርገውም፡፡
በተለይ መጪውን ረመዳን ሙስሊሙ ኡማ ከእንደዚህ አይነት አጓጉል እርኩስ ተግባሮች ሊርቅ ይገባዋል፡፡ ከረመዳንም ውጭ ቢሆን፡፡
በአላህ ፍቃድ በቅርቡ የድምፅ ፋይል ይለቀቃል፡፡