ከዛፍ ከድንጋይና ከመሳሰሉ ነገሮች በረከትን መፈለግ
በረከትን መፈለግ ሸሪዓው ከፈቀደው እና ካልፈቀደነው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ሸሪዓው ከሚፈቅዳቸው ነገሮች ለምሳሌ ከቁርዓን በመካ በመዲናና በበይተል መቅዲስ ከመስገድ በረከት ለማብዛት መጣር የተወደደ ተግባር ሲሆን ሸሪዓው ከማይፈቅዳቸው ነገሮች ግን ለምሳሌ ከዛፍ ከድንጋይና ከቀብር በረከትን መፈለግ ሽርክ ነው፡፡
አቡ ዋቂድ አልለይሢይ እንዲህ ብለዋል፡-
“አዲስ ሰለምቴዎች ሳለን ከነብዩ ጋር ወደ ሁነይን ስንሄድ አጋሪዎች እርሱ ዘንድ በመቀመጥና መሳሪያቸውን ላዩ በማንጠልጠል በረከትን የሚፈልጉበት ዛፍ ነበራቸውና በአንዲት ዛፍ ስናልፍ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እነሱ የሚያንጠለጥሉባት ዛፍ እንዳለቻቸው ሁሉ ለኛም ማንጠልጠያ ዛፍ አድርጉልን” አልናቸው፡፡
የአላህ መልዕክተኛም በቁጣ እንዲህ አሉ “አላሁ አክበር! ይህ የተለመደ መንገድ ነው ነፍሴ በእጁ ባለችው እምላለሁ የኢስራኤል ልጆች ለሙሳ እንዲህ ያሉትን አይነት ነው ያላችሁት፡-
اجْعَل لَّنَا إِلَهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ
“ለነርሱ አማልክት እንዳሏቸው ለኛም አምላክን አድርግልን አሉት፤ እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ አላቸው” (አል አዕራፍ)
"ከበስተፊታችሁ የነበረን መንገድ ትከተላላችሁ”
በዚህ ሀዲስ ከዛፍ በረከትን የፈለጉትን ሰዎች ሌላ አምላክ ከፈለጉ ሰዎች ጋር ማመሳሰላቸው የሚያመለክተው ከእንደዚህ አይነት ነገሮች በረከትን መፈለግ ማጋራት እንደሆነ ነው::
http://www.facebook.com/emnetihintebiq