🚫 አይፈቀድም! 🚫
አሳሳቢ መልእክት ለውዷ እህቴ
ሙስሊሟን እንስት ካፊር ወንድ ሊያገባት አይፈቀድም ሃራም ነው የሚለው (የሊቃውንት ድምዳሜ) ምንም ብዥታ የሌለው እውነታ ነው። ለዚህም ቀዳሚው አስረጅ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ
{ ولا تُنكحوا المشركين حتى يؤمنوا }
( البقرة : 221 )
«ለአጋሪዎቹም እስኪያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው።» ያለው ሲሆን፤ ኢማሙ ቁርጡቢ (ረሂመሁላህ) ሲተነትኑት “ አላህ {ولا تنكحوا} አትዳሩላቸው ሲል ሙስሊሟን ሴት በባዕድ አምልኮ ላይ ካለ ወንድ ጋር አታጋቡ ማለቱ ነው። ይህንንም አቋም በተመለከተ ሙስሊሙ ህብረተሰብ አንድ ባዕድ አምልኮ ላይ ያለ ሰው አማኟን እንስት በፍፁም ሊገናኛት እንደማይገባ ተስማምተውበታል። ይህም ኢስላምን ማዋረድ በመሆኑ ነው።” ብለዋል።
【ተፍሲሩ-ቁርጡቢ: 3/72】
ይህንንም ክልከላ አላህ በሱረቱል ሙምተሂናህ ላይ ጠንከር ባለ አገላለፅ ሲገልፅ፤
{لا هنَّ حلٌّ لهم ولا هم يحلون لهن} ( الممتحنة : 10 )
«እነርሱ (ሴቶቹ) ለነሱ (ለከሃዲዎቹ) የተፈቀዱ አይደሉም። እነርሱም (ከሃዲዎቹ ወንዶች) ለነርሱ ለምእመናቱ አይፈቀዱምና።»【አል-ሙምተሂናህ:10】
እንኳንስ ቀድሞውን ሙስሊም የሆነች እንስት ለካፊር መዳር ይቅርና ከባሏ ጋር በኩፍሩ አለም ትኖር የነበረች እንስት ከባሏ ቀድማ ከሰለመች ከካፊሩ ባልዋ ወዲያው ትነጠላለች። ጋብቻዋም ፉርሽ ነው።
ኢማም ቡኻሪ (ረሂመሁላህ) ባዕድ አምልኮ ውስጥ የነበረቿ እንስት ወደ ኢስላም ስትመለስ ማለትም ስትሰልም ወይም በሙስሊም ሀገር ውስጥ በቃል ኪዳን ስምምነት ከሚኖሩ ወይም ከሙስሊሞች ጋር በጦርነት ሁኔታ ባሉ ከሃዲያን ስር የነበረች ክርስቲያን ሴት ስትሰልም ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ስላለው ደንብ ባስቀመጡበት የድርሳናቸው ክፍል እንዲህ ብለዋል☞
«ኢክሪማ ከኢብኑዓባስ (ሪድዋኑላሂ አለይሂም) ሰምቶ ባስተላለፈው መሰረት ክርስቲያኗ ከባሏ በፊት በአንድ ሰዓት እንኳ ቀድማ ከሰለመች በካፊሩ ባሏ ላይ ህርም ትሆናለች።» ብለዋል።
እንዲሁም ሙጃሂድ እንዳሉት ልዕለ ሃያሉ አላህ "ሙስሊሞቹ ሴቶች ለከሃዲያኑ ወንዶች ፍቁድ አይሆኑም። ከሃዲያኑ ወንዶችም ለሙስሊሞቹ ሴቶች አይገቡም" ብሏልና ኢዳዋን ሳትጨርስ እሱም ከሰለመ ዳግም ይጋባሉ”።
ሀሰን እና ቀታዳህ ደግሞ (ረሂመሁሙላህ) እሳት አምላኪያንን (መጁሲዪንን) በተመለከተ እንዳሉት "ባልና ሚስት ባንድ ላይ ከሰለሙ በትዳራቸው ይፀናሉ። እሷ ከባሏ ቀድማ ከሰለመችና እሱ አሻፈረኝ ካለ ግን ከሚስትነቱ ውጭ ትሆናለች። በሷ ላይ መብት የለውምና።" ሰሂሁል ቡኻሪ: "አል-ፈትህ" 9/421ን ይመልከቱ።
ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን
የነቢዩ ﷺ ሴት ልጅ ዘይነብ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በጃሂሊያው ዘመን አቢል-ዓስ ቢን ረቢዕ ከተባለ ግለሰብ ተጋብታ ትኖር ነበር። ስትሰልም ግን በመሃከላቸው የነበረው ኒካህ ፈረሰ። ወደ አባቷ ወደ ነቢዩ ﷺ ዘንድ ሄዳ መኖር ጀመረች። ባሏ እንደሰለመም ነቢዩ ﷺ ወደ ባሏ መለሷት።
ቲርሚዚ: 1143, አቡዳዉድ: 2240, ኢብኑማጃህ: 2009 ዘግበውታል። ኢማሙ አህመድም: 1879 ሰሂህ ብለውታል። ቲርሚዚ ደግሞ ሰነዱ ላይ ችግር የለበትም ብለዋል።
ይህ ለከሃድያን ወንዶች ሙስሊም እንስቶችን አትዳሩ የሚለው መርህ በቀጥታ የሚመለከተው ሃላፊ ቤተሰቦችሽን ቢሆንም አንቺም በሃይማኖትሽ ክልል ውስጥ ከሌለ ወንድ ጋርም ሆነ ከሌላ ባእድ ወንድ ጋር ምንም አይነት ክፉ ቅርርቦሽ እንዳትፈጥሪ ታዘሻል። አስልሜው አገባዋለሁ በሚል የድብብቆሽ ወንጀል ውስጥም ራስሽን እንዳትከቺ ተጠንቀቂ❗
❌ በመሆኑም እኔም በሀይማኖቴ አንተም በእምነትህ የሚባለው ተረትም በኢስላም ቦታ የለውምና እያንዳንዱን የህይወታችንን መስመር ከዲናችን ጋር በተጣጣመ አኳሃን ልንመራው ስለሚገባን እንማር፣ እንጠይቅ፣ እንታረም❗
አላህ መልካሙ መንገድ ላይ ያፅናን
🌴 ⛲ 🌴
ዙል-ሒጅ'ጃ (04/12/1436)
መስከረም (08/01/2015)
Sep (17/09/2015)
ለተጨማሪ ትምህርት ⇣
www.fb.com/tenbihat