Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነወይቱ ኡሰሊ ፈረደ ሰላት __ ረከአተየን _ " የሚለው አባባል ቢድአ ነው።

"ነወይቱ ኡሰሊ ፈረደ ሰላት ______ _____ ረከአተየን _____ " የሚለው አባባል ቢድአ ነው። የንያ ቦታ ቀልብ ነው። ይህን አባባል ከቁርአን፣ ከሱና፣ ከሰሃባዎች አላገኘነውም።
ለሰሃባዎች የበቃቸው ዲን ለእኛም ሊበቃን ይገባል። ቢድአ ለመሆኑ የሚከተለውን ማስረጃ መጥቀሱ ጥሩ ነው።
قُلْ أَتُعَلِّمُونَ اللَّهَ بِدِينِكُمْ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَات
ِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيم
أي أتخبرونه بما في ضمائركم "والله يعلم ما في السموات وما في الأرض" أي لا يخفى عليه مثقال ذرة في الأرض ولا في السماء ولا أصغر من ذلك ولا أكبر "والله بكل شيء عليم".
"አላህ በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ ሲኾን አላህን በሃይማኖታችሁ ታስታውቁታላችሁን?
(በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ለእርሱ ለማሳወቅ ትሞክራላችሁን? ሚስጥር ሁሉ እርሱ ዘንድ ይፉ ሆኖ እያለ)" በላቸው። አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።
አላህ ባወቁት ከሚሰሩት ያድርገን።