Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በልጆቻችሁ ልብ የሰሀቦችን ፍቅር አስርፁ!!



በልጆቻችሁ ልብ የሰሀቦችን ፍቅር አስርፁ!!

#ተንቢሀት_ተርቢያ

አል ኢማም ማሊክ እንዲህ ብለዋል፤
«ሰለፎች ለልጆቻቸው ልክ አንድ የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሯቸው የሁለቱን ሸይኾች አቡበከር እና ኡመርን መውደድን ያስተምሩ ነበር»

روى الإمام البخاري من حديث أنس بن مالك رضي الله عنه « أن رجلا سأل النبي صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلِّم عن الساعة فقال : متى الساعة ؟ فقال النبي صلى الله عليه وسلم : (وماذا أعددت لها) . قال : لا شيء إلا أني أحب الله ورسوله ، فقَال النبي صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلِّم : (أنت مع من أحببت) ، فقال أنس : فما فرحنا بشيء فرحنا بقول النبي صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلِّم أنت مع من أحببت . قال أنس : (فأنا أحب النبي صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلِّم وأبا بكر وعمر وأرجو أن أكون معهم بحبي إياهم وإن لم أعمل بمثل أعمالهم »

ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተዘገበው አንድ ሰው ነብዩን ስለ ትንሳኤ እለት “ቂያማህ” ይጠይቃቸዋል። እርሳቸውም፤ «ለዛ እለት ምን አዘጋጅተሀል?» በማለት ጠየቁት። ሰውየውም፤ «ምንም ያዘጋጀሁት ነገር የለም፤ ነገር ግን አላህን እና መልዕክተኛውን እወዳለሁ።» አላቸው። እርሳቸውም፤ «አንተ ከወደድከው ጋር ነህ» በማለት አበሰሩት። አነስ እንዲህ አሉ፤ «አንተ ከወደድከው ጋር ነህ» የሚለው የነብዩ ع ንግግር ካስደሰተን በበለጠ በምንም ተደስተን አናውቅም። እኔ ነብዩን እወዳለሁ፤ አቡበከር እና ዑመርንም እንዲሁ፤ የነሱ ያክል ስራ ባልሰራም እነርሱን በመውደዴ ምክኒያት ከነሱ ጋር እንደምሆን ተስፋ አደርጋለሁ» [ቡኻሪ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ዘግበውታል]

© ተንቢሀት