በየትኛውም
የአለማችን ክፍል ለሚገኝ የዘመናችን የሙስሊም ወጣት መነቃቃት እርሾዎቹ የሳዑዲ ዑለሞች እንደሆኑ ለማንም
አይሰወርም። የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ አሱሉሥሠላሳህ፣ ኪታቡ ተውሂድ፣ ቀዋዒዱል አርበዕ፣ ከሽፉሽሹቡሃት፣
አሱሉስሲታህ፣…ኪታቦች፣ የሸይኽ ዐብዱርራህማን ኢብኑ ሐሰን ፈትሁል መጂድ፣ የሸይኽ ሰዕዲ ተፍሲር፣ የኢብኑል
ዑሰይሚን የሪያድ ሸርሕ፣ ቀውሉል ሙፊድ፣ የአርበዒን ሸርሕ፣ የዋሲጢያ ሸርሕ፣ መጃሊሱ ረመዷንይያህ፣ የኢስላም
ማዕዘናት ፈትዋዎች… የኢብኑ ባዝ አድዱሩሱል ሙሂማህ ሊዓመቲል ኡማህ፣ መጅሙዑል ፈታዋ፣… የፈውዛን አልኢርሻድ፣ ሚን
ኡሱሊ ዐቂደቲ አህሊስሱንናህ ወልጀማዐህ፣ ኪታቡ ተውሂድ፣ ተንቢሀት፣ የኹጥባ
ኪታብ፣… ያለንኳኩት ጆሮ ያልገቡበት ቤት የለም። በየመሳጂዱ የደርስ ማእድ ላይ ኪትቦቻቸው ይቀራሉ፣ ፈትዋዎቻቸው
ይጣቀሳሉ። በየደዕዋው ላይ ስማቸው ይነሳል። የፊቂህ ምርጫቸው፣ የአቂዳ ትምህርታቸው ከሁሉም ጋር ይደርሳል። በአላህ
ፍቃድ የዒልም ውጤቶቻቸው ብዙዎችን ከሺርክ፣ ከቢድዐህና ከተለያዩ ጥፋቶች መልሰዋል። የነቃ መስሎት ዛሬ በደጋሚ
ምላሶች የተጠለፈው አንዳንድ ወጣት እራሱ በአብዛሃኛው ወደኋላ ተመልሶ ወደ ዲን ያዘነበለበት ዘመኑን ቢመለከት ከፊቱ
የሚመጣው የነዚህ ዑለማዎች ኪታብ ነው።
አንድ ጥርጣሬ
ሐሰን ዑለማዎችን በሚሰቀጥጡ ቃላት በተደጋጋሚ መወረፉን አይተናል። ሆኖም ግን አንድ ነገር እጠረጥራለሁ። ይህንን የዑለማእ ክብር መዳፈሩን “ምሁራዊ ሂስ” የሚል ቀሚስ እንዳያለብሰው ስጋት አለኝ። እርግጥ ነው ዑለማዎች አንዱ በሌላው ላይ ሂስ ይሰነዝራሉ። አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት ጠንካራ ቃላትን ጭምር ይጠቀማሉ። የሐሰንን የማንቋሸሽ ስራ ግን “ምሁራዊ ሂስ” ማለት ለዑለማዎችም ስድብ ነው። ምክንያቱም፦
⒈ ሐሰን በአለም አቀፍ ደረጀ ቀርቶ በሃገር አቀፍ ደረጃም በየትኛውም መመዘኛ ዓሊም ሊሰኝ አይችልም። ስለሆነም ውንጀላውን “ምሁራዊ” ማለት እሱን ያለደረጃው ማስቀመጥ ነው።ይሄ ከማንም በላይ እራሱን ነው የሚጎዳው። ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሀብን “ለአንድ ቀየ (ሰፈር) እንኳን የማይመጥን ዓሊም ነው” የሚል ሰው የዑለማዎች ደረጃ ሲወሳ የት ቦታ እንደሚቀመጥ አንባቢ ይፍረደው።
⒉ ሌላውን ሁሉንም ብንተወው “የነዳጅ በሳውዲ ምድር መገኘት ሸኽ ሙሐመድ ዐብዱልወሃብን ከአንዲት ቀዬ ዳዒነት አውጥቶ ሸይኹል ኢስላም አደረጋቸው” ማለቱና የሳዑዲ ዑለማዎችን “ዑለማዎቻቸው በአብዘሃኛው ምሁራዊ አቋም ለመያዝ ከሚያስችል የኢልም እርከን ላይ የደረሱ ካለመሆናቸው አኳያም አቋሞቻቸው ከጥልቅ ምርምር የመነጩ ናቸው ለማለት ያዳግታል” ማለቱ ያለ አቅሙ የሚንጠራራ ዋልጌ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
[መውሊድ: ታሪክ፤ ግድፈት፤ እርምት ከሚለው የኢብኑ ሙነወር መፅሐፍ ከገፅ 285‐286 የተወሰደ]