Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መውሊድ ሙስሊሞች የዘነጉት ግና ጠላት የተረዳው አደጋ


መውሊድ ውስጥ ከኢስላማዋዊው አስተምህሮት ያፈነገጡ የበእድ አምልኮቶች፣ ጭፈራዎችና አይነታቸው የበዛ ጥፍፋቶች አሉ። እነዚህ አፈንጋጭ ምግባሮችና ነፀብራቆች በኢስላም ስም እየታሰቡ ይቀጥሉ ዘንድ የጋለ ፍላጎት ያላቸው ከሃዲዎች በተለያዩ ጊዜያት ለዚህ መጤ በዓል ድጋፋቸውን ሲሰጡ፣ የጥፋት ቦታዎችን ሲያንፁና መሰረተ‐ልማት ሲዘረጉ ያጋጥማሉ። ለምሳሌ ግብፃዊው የታሪክ ፀሃፊ አልጀበርቲ የፈረንሳዩ መሪ ናፖሊዎን ቦናፓርቴ ግብፅን በተቆጣጠረ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሲተርኩ የ 1213 ዓ.ሂ. ክስተትን እንዲህ ይገልፁታል፦ የጦሩ አዛዥ የነቢዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) መውሊድ እንደልማዳቸው ለምን እንዳላከናወኑት ጠየቀ። ሁኔታዎች እንደቆሙ፣ ነገሮች እንደተራቆቱ፣ ለተለያዩ ወጪዎች የሚውል ገንዘብ እንደሌለም ሸይኽ በክሪ ተናገሩ። ናፖሊዎን “የግድ መዘጋጀት አለበት” በማለት ለዚሁ ተግባር ይታገዙበት ዘንድ ለሸይኽ በክሪ 300 የፈረንሳይ ብር ሰጠ። ከዚህ በኋላ ሻማዎችና ችቦዎች ተለኮሱ። ፈረንሳውያንም ለመውሊድ ተሰባሰቡ። ከበሮዎቻቸውን እየመቱ ጨፈሩ። ትልልቅ ከበሮዎችና የተለያዩ ድምፆችን የሚሰጡ የሙዚቃ መሳሪያዎች ወደ ሸይኽ በክሪ ቤትም ተልከው ሌት ከቀን ተደለቀ። ሌሊቱን ጧፍ ሲቀጣጠልና ርችቶች ወደ ሰማይ ሲለቀቁ አደረ። [መዝህሩ አትተቅዲስ: 47]
ጄ ክርስቶፎር ሄሮልድም እንዲሁ ተመሳሳይ ታሪክ ያወሳል። እንዲህ በማለት፦
“የካይሮ ታዋቂ ሰዎች በዓሉን የሚያከብሩ አይመስሉም። ስለሆነም ናፖሊዎን ቦታውንም በጀቱንም በመፍቀድ አበረታታቸው። ካይሮ በዓሉን ለሶስት ቀናት አከበረች። ሱፊዮች በድካም እስከሚወድቁ ድረስ በጎዳናዎች ወጥተው ደነሱ። የፈረንሳይ ወታደሮችም የሙዚቃ ትርኢት አሳዩ፣ እሳት አቀጣጠሉ። በዚህ ጊዜ በናፖርቴ የሸይኽ በክሪ እንግዳ ነበር። እስከ አንገቱ በተቆለፈው ጥቁር የደንብ ልብስ፣ የበዓል ገመዶችንና ጥምጣሞችን አድርገው የቁርአን አንቀፆችን ከሚያነበንቡትና ዶቃዎችን ከሚስቡት ሸይኾች ጋር ልዩ ገፅታ ነበር።” [Herold, J. C. Bonaparete in Egypt, Published in 1962]
ምናልባት “እንዲህ አይነቱን የቢድዓ ድግስ በመደገፍ ፈረንሳውያኑ ምን ያተርፋሉ? ” የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። የመውሊድ ደጋፊዎች “ጠላት ከህዝብ ልብ ውስጥ ለመግባት ያደረገው ነው። ልክ ሌሎች ዲናዊ ጉዳዮችን ለመፈፀም ጠላት ቢያግዘን እነዚያን ጉዳዮች በክፉ ልንመለከት ነው ወይ?” እንደሚሉ ይጠበቃል። እውነት መውሊድ በዚህ መልኩ የሚታይ ነው? መልሱን በወቅቱ ለነበሩት የታሪክ ፀሐፊው አልጀበርቲ እንልቀቅ። እንዲህ ነበር ያሉት፦ “ፈረንሳውያኑ ይህን ለሰዎች የፈቀዱበት ምክንያት በውስጡ ከሸሪዐዊ አስተምህሮቶች ማፈንገጥ፣ የሴቶች መሰባሰብ፣ ስሜቶችን መከተል፣ አጉል ዛዛታና ሐራም የሆኑ ድርጊቶች ስላሉበት ነው።” [ዐጃኢቡል ኣሣር: 2/306]
[መውሊድ፡ ታሪክ፤ ግድፈት፤ እርምት ከሚለው የኢብኑ ሙነወር መፅሀፍ ከገፅ 217 ‐218 የተወሰደ]