Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሁላችንም ስውር ወንጀሎችን እንጠንቀቅ!! (Alert)

ሁላችንም ስውር ወንጀሎችን እንጠንቀቅ!! (Alert)
በግልፅ በሚታዩ አምልኮዎች ለአላህ እጅ እንደሰጠን ሁሉ በድብቅ ወደ አላህ የሚያቃርቡን መልካም ስራዎች ይኑሩን። በገሀድ ወንጀሎችን እንደማንዳፈር ሁሉ በድብቅም አላህን እንፍራ። የፍጡራን እይታ ከመጥፎ ስራ ካቀበን አላህ እንደሚያየን በማሰብ ወንጀሎችን አረንጠንቀቅ። ባለንበት ወቅት ወንጀልን ለመፈፀም ነገሮች ቢመቻቹ፤ ፈተናችን እየበረታ ነውና አንዘናጋ!!
ድብቅ ወንጀሎችን መላመድ የቀልብ ሞትን ታስከትላል። የምናመልከው፤ ግልፁንም ድብቁንም ስራችንን የሚያውቀውን አላህን ነው። በገሀድ ወንጀሎችን ከመዳፈር ጥንቃቄ እንደምናደርፍ ሁሉ በድብቅም ትእዛዛትን አንጣስ የተከለከሉ ነገሮችንም አንዳፈር። ሰሚ ተመልካችነቱን፣ ውስጥ አዋቂ መሆኑን የሚገልፁ ስያሜዎችን የማመናችን ፍሬ ይህ ሊሆን ይገባል።
☞ የዲን ተማሪዎች ሆይ... ስውር ወንጀሎችን ተጠንቀቁ!!
☞ ኡስታዞችና ታዋቂነትን ያገኛችሁ ዳኢዎች ሆይ... ስውር ወንጀሎችን ተጠንቀቁ!!
☞ ቁርአን የሀፈዛችሁ ወንድምና እህቶች... ስውር ወንጀሎችን ተጠንቀቁ!!
☞ ቤተሰቦችሽ እምነት የጣሉብሽ እህታችን... ስውር ወንጀሎችን ተጠንቀቁ!!
☞ አላህ ሁሉ ነገር አሟልቶልህ በበጎ ተግባር የታወቅከው ወንድም ሆይ... ስውር ወንጀሎችን ተጠንቀቁ!!
ዘወትር ይህንን ሀዲስ እናጢነው፤ ሰውባን እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «ከኔ ህዝቦች፤ በእለተ ትንሳኤ ንፃታቸው ቲሀማ የተባለውን ተራራ የሚመስሉ መልካም ስራዎች የሚኖሯቸውን ሰዎች አውቃለሁ፤ አላህ ስራቸውን የተበተነ ትቢያ ያደርገዋል።» ሰውባንም፤ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ባለማወቅ ከነሱ እንዳንሆን ማንነታቸውን ግልፅ ያድርጉልን" አሏቸው። እሳቸውም፤ «እነዚህ ሰዎች ከናንተው የሆኑ ወንድሞቻችሁ ናቸው፤ እናንተ የለሊት ስግደት እንደምትሰግዱ እነሱም ይሰግዳሉ። ነገር ግን እነዚህ ጭፍሮች ከሰዎች ሲገለሉ አላህ እርም ያደረጋቸውን ነገሮች ይዳፈራሉ»
ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ ብለውታል
عَنْ ثَوْبَانَ رضي الله عنه ، عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ : [لَأَعْلَمَنَّ أَقْوَامًا مِنْ أُمَّتِي يَأْتُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِحَسَنَاتٍ أَمْثَالِ جِبَالِ تِهَامَةَ بِيضًا فَيَجْعَلُهَا اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ هَبَاءً مَنْثُورًا قَالَ ثَوْبَانُ يَا رَسُولَ اللَّهِ صِفْهُمْ لَنَا جَلِّهِمْ لَنَا أَنْ لَا نَكُونَ مِنْهُمْ وَنَحْنُ لَا نَعْلَمُ قَالَ أَمَا إِنَّهُمْ إِخْوَانُكُمْ وَمِنْ جِلْدَتِكُمْ وَيَأْخُذُونَ مِنْ اللَّيْلِ كَمَا تَأْخُذُونَ وَلَكِنَّهُمْ أَقْوَامٌ إِذَا خَلَوْا بِمَحَارِمِ اللَّهِ انْتَهَكُوهَا] رواه ابن ماجة (4245) وصححه الألباني .
አላህ ሆይ! ጥንካሬን ለግሰህ ከጥፋቶች ሁሉ ጠብቀን!!
እንደጥፋታችን እና መዳፈራችን ሳይሆን እንደ እዝነትና ችሮታህ ገር የሆነን መተሳሰብ ተሳሰበን!!

© ተንቢሀት