የአልረሕማንን ባሮች እወቋቸው
የሱረቱል ፉርቃን መደምደሚያ አንቀፆች (ሱረቱል ፉርቃን 63–77)

{وَعِبَادُ الرَّحْمَٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا (63)
የአልረሕማን ባሮች፤
እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱ፣ ባለጌዎች በክፉ ባነጋገሩዋቸውም ጊዜ መልካምን የሚመልሱ ናቸው።
وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا (64)
እነዚያም፦ ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው።
وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا اصْرِفْ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَ ۖ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا (65)
እነዚያም፦ ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከኛ ላይ መልስልን፤ ቅጣቷ የማያልቅ ነውና፤ የሚሉት ናቸው።
إِنَّهَا سَاءَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا (66)
እርሷ ለመርጊያና ለመኖሪያነት የከፋች ናት! (ይላሉ)።
وَالَّذِينَ إِذَا أَنفَقُوا لَمْ يُسْرِفُوا وَلَمْ يَقْتُرُوا وَكَانَ بَيْنَ ذَٰلِكَ قَوَامًا (67)
እነዚያም፤በለገሱ ጊዜ የማያባክኑት፣ በስስት የማይቆጥቡትም ሲሆኑ፤ በዚህ መካከል (ልግስናቸው) ሚዛናዊ ነው።
وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا (68)
እነዚያም፣ ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማያመልኩት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፤ የማያመነዝሩትም ናቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል።
يُضَاعَفْ لَهُ الْعَذَابُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِ مُهَانًا (69)
በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ በርሱ ላይ ይደራረባል፤ በርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል።
إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا (70)
ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፤
እነዚያን አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፤ አላህም እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው።
وَمَن تَابَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَإِنَّهُ يَتُوبُ إِلَى اللَّهِ مَتَابًا (71)
ተጸጽቶ የተመለሰ አና መልካምንም የሠራ፤ እርሱ ትክክለኛን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል።
وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا (72)
እነዚያም፣ እብለትን የማይመሰክሩ፤ ውድቅ ቃልም (በሚገሩ ሰዎች አጠገብ) ባለፉ ጊዜ፤ ክብራቸውን በመጠበቅ የሚያልፉት ናቸው።
وَالَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ لَمْ يَخِرُّوا عَلَيْهَا صُمًّا وَعُمْيَانًا (73)
እነዚያም፣ በጌታቸው አንቀጾች በተገሠጹ ጊዜ፣ (ሀቅን የተረዱ ተቀባዮች ሆነው እንጂ) ደንቆሮዎችና ዕውሮች የሆኑ ያህል (በክህደት) በርሷ ላይ የማይደፉት ናቸው።
وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا (74)
እነዚያም ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለኛ ስጠን፤ አላህን ለሚፈሩት መሪ አድርገን፤ የሚሉት ናቸው።
أُولَٰئِكَ يُجْزَوْنَ الْغُرْفَةَ بِمَا صَبَرُوا وَيُلَقَّوْنَ فِيهَا تَحِيَّةً وَسَلَامًا (75)
እነዚያ በመታገሣቸው የገነትን ሠገነቶች ይመነዳሉ፤ በርሷም ውስጥ ውዳሴንና ሰላምታን ይስሰጣሉ።
خَالِدِينَ فِيهَا ۚ حَسُنَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا (76)
በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ይሆናሉ፤ መርጊያና መኖሪያነቷ አማረች፡፡ (76)
قُلْ مَا يَعْبَأُ بِكُمْ رَبِّي لَوْلَا دُعَاؤُكُمْ ۖ فَقَدْ كَذَّبْتُمْ فَسَوْفَ يَكُونُ لِزَامًا (77)}
ጸሎታችሁ ባልነበረ ኖሮ፤ ጌታዬ እናንተን ከምንም አይቆጥራችሁም ነበር፤ « (ከሀዲያን ሆይ!) በእርግጥም አስተባበላችሁ፤ ወደ ፊትም (ቅጣቱ) የሚይዛችሁ ይኾናል» በላቸው።
-------------////---------------
አላህ ሆይ!
እኔ ዘንድ ኢማንን የተወደደ አድርገው፤
በልቤ ውስጥም ስፍራ ስጥው፤
እውነተኛ አማኝም አድርገኝ!!
አሚን!!