Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የመፋቂያ ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች



የመፋቂያ ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች
www.facebook.com/easyfiqh

♻ መፋቂያ... ተወደጅ ሱና!

✔ መፋቂያ መጠቀም በየትኛውም ወቅት ሱና (የተወደደ) ነው፡፡

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "السواك مطهرة للفم، مرضاة للرب" علقه البخاري في صحيحه، وإسناده صحيح (الإرواء 1/105).

ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:- “መፋቂያ አፍን የሚያፀዳና አላህንም የሚያስወድድ ነው፡፡” ቡኻሪ ሙዓለቅ አድርገው ዘግበውታል። “ሰነዱ ሰሂህ ነው።” አልባኒ አልـኢርዋእ 1/105

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : " لولا أن أشق على أمتي لأمرتهم بالسواك عند كل صلاة" رواه البخاري ومسلم. وفي رواية للبخاري: "عند كل وضوء".

እንዲህም ብለዋል:- “ለህዝቦቼ ማስቸገር ባይሆንብኝ ለእያንዳንዱ ሰላት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር፡፡” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሌላኛው የቡኻሪ ዘገባ «በየውዱእ ወቅቱ» ይላል።

✔ አል ኢማም አነወዎይ መፋቂያ ሱና ለመሆኑ የኢስላም ሊቃውንትን የአንድነት አቋም በማሰባሰብ "ኢጅማዕ" እንዳለበት ገልጸዋል።

♻ ጥርስን መፋቅ ይበልጥ የሚወደድባቸው ወቅቶች፤
✔ በየትኛውም ወቅት መፋቂያን መጠቀም የተወደደ ሱና ነው፡፡ ✔ፆመኛም ጠዋትም ይሁን ከቀትር በኋላ ጥርሱን ቢፍቅ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) ጥርስ መፋቅን ሲያስተምሩ አንዱን ወቅት ከሌላው አልለዩም፡፡

✅ ይሁንና መፋቂያን መጠቀም በተለይ በነዚህ ወቅቶች ይበልጥ የተወደደ ነው፡፡

☞ ውዱእ በሚደረግበት ጊዜ፣
☞ የአፍ ጠረን ሲለወጥ፣
☞ ቁርአን ለመቅራትና ዚክር ለማድረግ ሲፈልግ፣
☞ ሰላት ለመስገድ፣
☞ መስጂድ ሲገባ፣
☞ ወደቤት ሲገባ፤ለዚህም መረጃው፤

ثبت من حديث عائشة رضي الله عنها أنها سئلت : بأي شيء يبدأ رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا دخل بيته ، قالت : "كان إذا دخل بيته بدأ بالسواك" رواه مسلم

✓ ሚቅዳም ኢብኑ ሹረይህ እንዳስተላለፈው አባቱ ነብዩ (ﷺ) ቤት ሲገቡ በምን እንደሚጀምሩ ዓኢሻን ጠይቋቸው ሲመልሱ፤ “ጥርሳቸውን በመፋቅ፡፡” ብለዋል:: (ሙስሊም ዘግበውታል)

☞ ለረዥም ሰዓት በዝምታ ሲቆይና ጥርስ ሲበልዝም ይበልጥ ይወደዳል፤

☞ ለሊት ከእንቅልፍ ሲነቁ፤

عن حذيفة بن اليمان رضي الله عنه قال: كان النبي ﷺ إذا قام من الليل يشوص فاه بالسواك" رواه البخاري ومسلم

✓ “ነብዩ(ﷺ) ሌሊት ሲነሱ አፋቸውን በመፋቂያ ያፀዱ ነበር”(ሙስሊም ዘግበውታል)

☞ ወደ አምልኮ ሲገባና ወደ አላህ ሲቃረብ በፀዳና ባማረ ሁኔታ መገኘት ይጠበቅበታል፡፡

▶ አላህ በትምህርቱ የምንጠቀምና እየተረሳ ያለውን የጠበቀ የነብዩ (ﷺ)ሱናህ የምንተገብር ያድርገን።
አሚን!!

☞ ውድ አንባቢ! አንባቢ ብቻ ሳይሆን ተሳታፊም ይሆኑ ዘንድ መፋቂያ (ሲዋክ) መጠቀም ከሚወደድባቸው ወቅቶች መካከል ቢያንስ አንዱን ይጥቀሱ::

〰〰✔✔〰〰

ዓላማችን የፊቅህ ትምህርትን ቀለል ባለ አቀራረብ ማስተማር ነው::

SHARE SHARE

nesiha.com