Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወንድ ሴትን መጨበጥ ሴትም ወንድን መጨበጥ በእስልምናችን እንዴት ይታያል?

ወንድ ሴትን መጨበጥ ሴትም ወንድን መጨበጥ
በእስልምናችን እንዴት ይታያል?
ነብያችን (ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ) በዚህ ዙሪያ ምን እንደተናገሩ እንመልከት:-
" ﻷﻥ ﻳﻄﻌﻦ ﻓﻲ ﺭﺃﺱ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﺑﻤﺨﻴﻂ ﻣﻦ ﺣﺪﻳﺪ ﺧﻴﺮ
ﻟﻪ ﻣﻦ ﺃﻥ ﻳﻤﺲ ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻻ ﺗﺤﻞ ﻟﻪ "

"የማትፈቀድለትን ሴት ከሚነካ የአንደኛችሁ ጭንቅላት
በብረት መርፌ ቢወጋ ይሻለዋል።" (ጦበራኒ ዘግበውታል)
ነገር ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ቡዙ መስሊም ወንዶችና
ሴቶች የማይፈቀድላቸውን ሰዎች በመጨበጥ እራሳቸውን
እየበደሉ ይገኛሉ። አልፎ ተርፎም ከወንጀሉ የበለጠ የሚያስጠሉ ምክንያቶችን ይደረድራሉ ለናሙና ያህል:-
* "ልባችን ንፁህ ናት" ይላሉ! የነዚህ ሰዎች ልብ ከነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ልብ የበለጠ ንፁህ ናትን? ለመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ ከነቢዩ(ﷺ) የበለጠ ልቡ ንፁህ የሆነ ሰው አለ? ከርሳቸው በላይ ልቡ መልካም ነገር የሚያስብ ሰው አለን?
* "ይህንን መተው ለኛ ሀገር ይከብዳል" ይላሉ እስልምና የመጣው ነብያችንም (ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ) የተላኩት ለዓለም እንጂ ለሳውዲ፣ ለኢትዮጲያ፣ ለዓረብ፣ ለፈረንጅ፣ ለጥቁር ለሀብታም፣ ለድሀ ብለው በመለየት አይደለም አላህ እንዲህ ይላል:-
ﻭﻣﺎ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎﻙ ﺇﻻ ﺭﺣﻤﺔ ﻟﻠﻌﺎﻟﻤﻴﻦ
"ለዓለማት እዝነት ቢሆን እንጂ አላክንህም"
ስለዚህ ሸሪዓችን ማንንም ሳይለይ ሁሉንም ይመለከታል! እስቲ ሁላችንም አንዴ ቆም ብለን እናስተውል በሚስማር ጭንቅላታችን ተወግቶ በአንድ ጎን ገብቶ በሌላ ጎን ቀዶ
መውጣቱ የማትፈቀድን ሴት ከመጨበጥ ይሻላል መባሉ
አያሰደነግጥምን? አላህ እርሱን የሚፈራ ልብ ይስጠን!!!
በመጀመርያ ደረጃ መጨበጥ የተፈቀዱ ዘመዶች እንመልከት
ውድ ወንድሜ
እናትህ፣ እህትህ፣ የወንድምህ ልጅ፣ የእህትህ ልጅ፣ ሚስትህ፣ ልጅህ፣ አክስትህ፣ የሚስትህ እናት ለአንተ እንድትጨብጥ የተፈቀዱ ናቸው።
ውዷ እህቴ
አባትሽ፣ ወንድምሽ፣ አጎትሽ፣ ባልሽ፣ ልጅሽ፣ የወንድምሽ ልጅ፣ የእህትሽ ልጅ፣ የባልሽ አባት እነዚህ መጨበጥ የተፈቀዱልሽ የቤተሰብ አባላት ናቸው።
ውድ ወንድሜ መጨበጥ የተከለከሉ ዘመዶችህ እወቃቸው
የአጎትህ ልጅ (በእናትም በአባትም)
የአክስትህ ልጅ (በእናትም በአባትም)
የወንድምህ ሚስት
የሚስትህ እህት
👉እነዚህ ሴቶችና ሌሎችም ልትጨብጣቸው አልተፈቀደልህም! እነዚህ ካልተፈቀዱልህ ከነዚህ የራቁት ደግሞ የባሰ ነው።
እህቴ ሆይ! መጨበጥ የተከለከሉ ዘመዶችሽ እወቂያቸው
የአጎትሽ ልጅ (በእናትም በአባትም)
የአክስትሽ ልጅ (በእናትም በአባትም)
የባልሽ ወንድም
የእህትሽ ባል
👉እነዚህና ሌሎችም ወንዶች ልትጨብጫቸው
አልተፈቀደልሽም! እነዚህ ካልተፈቀዱልሽ ከነዚህ የራቁት ደግሞ የባሰ ነው።
ወንድምና እህቶቼ ሆይ! ይህ በወንጀል ላይ ችክ ማለታችን
እስከመቼ ነው? ቀብር እስክንገባ? የሰዎችን ወሬ እየፈራን! ከሰዎች እናፍራለን ከአለማቱ ጌታ ያለን ፍራቻ የታል? ከሰዎች እያፈርን ከሰዎች ጌታ አናፍርምን? አላህ እርሱንና መልክተኛውን ከሚታዘዙት መልካም ባሮቹ ይጨምረን !!! አሚን